Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት ሸይኽ አብዱልወሀብ (ረሂመሁሏህ) ከትላልቅ ኡለማች ጋር ሁነው ወደ ሂጃዝ ፊሰቢሊሏህ | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

በአንድ ወቅት ሸይኽ አብዱልወሀብ (ረሂመሁሏህ) ከትላልቅ ኡለማች ጋር ሁነው ወደ ሂጃዝ ፊሰቢሊሏህ ይወጣሉ። ከሳቸውም ጋር ከነበሩት ዐሊም መካከል ሙፍቲ ዘይኑል ዓቢዲን (ረሂመሁሏህ) ይገኙበት ነበር።

እኝህም ሙፍቲ ሸይኽ አብዱልወሀብን እንዲህ በማለት ጠየቋቸው፦"ለምንድን ነው ግን ሰዎች አንተ ጋር ሚሰባሰቡትና የሚወዱክ አንተ ከትላልቅ ኡለሞች አይደለህም ምንድን ነው ሚስጥሩ" አሏቸው ሸይኽ አብዱልወሀብም በዛን ወቅት ምንም መልስ ሳይመልሱ ቀሩ።

ዳዕዋቸውን ጨርሰው ወደ ላሆር ሲመለሱ ኤርፓርቱ ውጭ እነሱን የሚጠብቁ ሁለት መኪኖች ቁመዋል ሙፍቲ ዘይኑል ዐቢዲን ወደ ቤታቸው ሚወስዳቸው መኪና ውስጥ ሲገቡ ሸይኽ አብዱልወሀብ ግን ወደ ራይዎንድ መርከዝ ሚወስዳቸው መኪና ውስጥ ገቡ። ሸይኽ አብዱልወሀብም በመስኮት በኩል ለሙፍቲ ዘይኑል ዐቢዲን እንዲህ አሏቸው፦"ወዴት ነው ምትሄደው" አሏቸው።? "ወደ ቤቴ" አሉ ሙፍቲ ዘይኑል ዐቢዲን
ሸይኽ አብዱልወሀብም "እኔስ ወዴት ነው የምሄደው"? አሏቸው ሙፍቲም ወደ ራይዎንድ መርከዝ አሏቸው በቃ ባለፈው በዳዕዋ የጠየቁኝ ጥያቄ መልስ ይህ ነው አሏቸው"።

https://t.me/sufiyahlesuna