Get Mystery Box with random crypto!

#ሱፊዮች ■ ኢማም አብዱል ቃሂር አል በጝዳዲ (429 ሂጅራ ያረፉ)- ታላቁ ኢማም ፣ የነገረ እም | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

#ሱፊዮች
■ ኢማም አብዱል ቃሂር አል በጝዳዲ (429 ሂጅራ ያረፉ)-

ታላቁ ኢማም ፣ የነገረ እምነት ምሁራን ማስረጃ ፣ አብዱል ቃሒር አል በጝዳዲ ፣ አላህ ይዘንላቸው ፣ በ“الفرق بين الفرق” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ ((በዚህ ክፍል ምዕራፎች የመጀመሪያ ምዕራፍ የአህል አል-ሱና ወል-ጀማዓህ ምድቦችን ያብራራል) እንዲህ ይላሉ፦

አህሉ-ሱና ወል-ጀማዓህ-ስምንት ምድብ እንዳላቸው ሊታወቅ ይገባል! ስድስተኛው- መደብ ውስጥ እነዚያ (የዱንያ ምንነት)ተገልጦላቸው የተቆጠቡና ከዓለማዊ ህይወት የራቁ ሱፊዮች ናቸው እነርሱ፦ በተነገራቸው ጊዜ አገናዘቡ ፣ አላህ የወሰነውን ወደው ተቀበሉ ፣ በአነስተኛ ነገር የተብቃቁ ፥ መስሚያ ፣ ማያና ቀልብ እነዚህ ሁሉ(ባለቤታቸው) በበጎም በክፉ በነዚህ ተጠያቂ መሆኑን ያወቁና በብናኝ ክብደት ሚተሳሰቡ መሆኑን የተገነዘቡ ፣ ለቀጠሮውም ቀን መልካም መሰናዶን የተሰናዱ ፣ ንግግራቸው አታላይን ወሬ ከሚገዙ ሰዎች ፍፁም የራቀና በታማኝ ሰዎች የንግግር መስመር በውስጣዊ ገለፃ እና በዒሻራ መንገድ የሚገለፅ ፣ ለይዩልኝ ብለው መልካም ስራ አይሰሩም ፣ በይሉኝታም አይተውም ፣ ሃይማኖታቸው ተውሂድ(አሃዳዊነት) እና ተሽቢህ(ማመሳሰልን) ማስዋሸት ነው ፣ መዝሀባቸውም ወደ አላህ ማስጠጋት፣ በርሱ መመካት እና ለትእዛዙ ተገዢ መሆን ነው - በተሰጣቸው ነገር የረ'ኩና ከመቃወም የራቁ ናቸው 【ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።】