Get Mystery Box with random crypto!

SMN TV1

የቴሌግራም ቻናል አርማ sidaamamedianetwork — SMN TV1 S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sidaamamedianetwork — SMN TV1
የሰርጥ አድራሻ: @sidaamamedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.34K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @smnminebot
.
.
.
.
.
.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 20:09:40 በመጪው የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ በሕግ ያስጠይቃል

ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያ እንዳይጠይቁ የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳሰበ።

የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት ከመመሪያው ውጭ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ እዳያደርጉ ያዛል።

ነገር ግን መመሪያውን በመጣስ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች አስቀድመው በደብዳቤና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለወላጆች መልዕክት እያስተላለፉ መሆኑ ተደርሶበታል ብለዋል።

መመሪያውን በሚጥሱ ትምህርት ቤቶች ላይ ፈቃድ የመሰረዝና በሕግ የማስጠየቅ እርምጃዎች እንደሚወስድ ከወዲሁ አሳስበዋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
3.7K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:42:22 የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴው ስራ መጀመሩን አስታወቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድን ሁሴን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በኩል እንዳስታወቁት፥የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሂዷል።

ኮሚቴው በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት የራሱን የአሰራርና ሥነምግባር አካሄድ ተወያይቶ መወሰኑንም አምባሳደር ሬድዋን ጠቁመዋል፡፡

አብይ ኮሚቴው በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጃትም ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር የሰላም አማራጮች እንዲታዩ እና የፌደራል መንግስቱን ወክለው በሰላም ውይይቱ ላይ የሚሳተፉ አባላት መመደባቸው ይታወሳል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
634 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 10:22:08
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ !

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን እሁድ የሚጠናቀቅ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል የውድድሩ አሸናፊ የመሆን እድል ያላቸው ሲሆን ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የሚችለው ከታች በተዘረዘሩት መንገዶች ነው ።

ሊቨርፑል ዎልቨስን አሸንፎ ማንችስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ነጥብ ከጣለ ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የሚያሸንፍ ይሆናል ።

ሊቨርፑል ከ ዎልቨስ ጋር ነጥብ ከተጋራ እና ማንችስተር ሲቲ በ አስቶን ቪላ በስድስት ግቦች ልዩነት ከተሸነፈ ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ እንደሚያነሳ ተገልጿል ።

ማንችስተር ሲቲ በ አስቶን ቪላ 6 - 0 በሆነ ውጤት ከተሸነፈ እና ሊቨርፑል ከ ዎልቨስ ጋር 5 - 5 በሆነ ውጤት ከተለያየ የሊጉ የዋንጫ አሸናፊ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንደሚለይ ተዘግቧል ።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.0K viewsedited  07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 20:20:31 የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
3.5K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 21:14:57 ኢትዮጵያ በይፋ የ5G ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረች

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የ5G ኔትወርክን በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በይፋ አስጀምረዋል።

ይህ አገልግሎት ደበኞች ባንዴ ብዙ የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጥ እና ከመደበኛው የኔትወርክ አገልግሎት 20 እጥፍ አገልግሎት ይሰጣል። ዛሬ የተጀመረው ይህ የ5G ኔትወርክ በቻይናው ህዋዌ የቴሌኮም ኩባንያ እንደተገነባ ተገልጿል። የሰዎችን ከማሽን ጋር እንዲሁም ማሽኖችን ከሰዎች ጋር በቀላሉ በማገናኘት ምርትማነትን ያቀላጥፋል። የ5G ኔትወርክ አገልግሎት አሰራሮችን በቀላሉ እንዲቀላጠፉ የሰውን ልጅ ህይወት ቀላል ያደርጋልም ተብሏል።

የ5G ኔትወርክ ደንበኞች በሰከንድ እስከ 10 ጊጋ ባይት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙም እንደሚያደርግም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል። ይህ አዲስ አገልግሎት በተለይም አገልግሎቶችን በርቀት በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ እንዲሰጡ ያደርጋሉም ተብሏል።

ይህ የ5G ኔትወርክ በአዲስ አበባ የተመረጡ ቦታዎች ለደንበኞች ክፍት የሆኑ ሲሆን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 150 የ5G ኔትወርክ ቀጠናዎች ይከፈታሉ ሲል ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልጸዋል።የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው በመርሐ ግብሩ የተገለጸው፡፡
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
3.9K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 22:51:13 የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወርም በነበረበት እንዲቀጥል ተወሰነ

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወርም በነበረበት እንዲቀጥል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

መንግስት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል በሚያዚያ ወር/2014 ዓ.ም የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር/2014 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ ያለምንም ለውጥ በነበረበት እንዲቀጥል ወስኗል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
5.6K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 09:08:01
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል

ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገሩት ፦

የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።

ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ ፤ ፈተናው በማን እንደሚዘጋጅ ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ምላሽ የሚሰጥ የድርጊት መርሃግብር ተዘጋጅቷል።

የመውጫ ፈተና ሌላ ከውጪ የሚጫን ፈተና አይደለም። በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የተቀመጡትን የምሩቃኑን ፕሮፋይል መሳካት አለመሳካቱን ፤ መጨበጥ አለመጨበጡን የሚያረጋግጥ ነው። "
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
5.3K viewsedited  06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 21:15:27 የሩሲያ ጦር ከ 50 በላይ የዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎችን “መታሁ” አለች

የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የሀገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሸንኮቭ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሀገራቸው ጦር 51 ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ገልጸዋል፡፡ ጦሩ በሁለት የከባድ መሳሪያ ክላስተር እና ብዙ በሚተፋ ተወንጫፊ ሮኬት ሲስተም ላይ የተሳካ ጥቃት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

ኢላማዎቹን የመታው የሩሲያ የኤሮስፔስ ኃይል መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ በዩክሬን ወታደራዊ መሳሪያዎች ላይ ኪሳራ ደርሷልም ብለዋል፡፡ የሩሲያ ጦር በባሕር እና በአየር ጥቃት በመታገዝ በፈጸመው ጥቃት የዘይት ማጣሪያ እንዲሁም ሶስት የነዳጅ ዲፖዎችን አጥቅቷል ብለዋል፡፡

ጥቃት የተፈጸመባቸው ዲፖዎች ለዩክሬን ወታደሮች ነዳጅ የሚቀርብባቸውና የሚቀዳባቸው መሆናቸውን የሩሲያ መንግስት ዜና አገልግሎት ታስ ዘግቧል፡፡ በዚህም መሰረት የነዳጅና የዘይት ዲፖዎቹ ሙሉ ለሙሉ ተወግደዋል ነው የተባለው፡፡ ሩሲያ በዩክሬን “ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረችበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ጦሯ 125 የጦር አውሮፕላኖች፣ 88 ሂሊኮፍተሮች፣ 383 ድሮኖች ከጥቅም ውጭ ማድረጉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ 1 ሺ 903 ታንኮችን፣ 207 ተወንጫፊ ሮኬቶችን፣ 1 ሺ 781 ልዩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ 221 ሚሳኤሎችን፣ 805 የመስክ ከባድ መሳሪያዎችና ሞርታሮችን ከጥቅም ውጭ አድርጋለች ተብሏል፡፡ ዛሬም የዩክሬን ኤሮስፔስ ሁለት ድሮኖችን መቶ መጣሉ ተገልጿል፡፡ሩሲያ እና ዩክሬን አሁንም ውጊያ ላይ ቢሆኑም ድርድር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.1K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 20:58:32 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ

ንግድ ባንክ " መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም " ብሏል።

ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም #ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።

የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውን እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ብሏል ባንኩ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለው ትክክል እንዳልሆነ ባንኩ ገልጿል።

አክሎም " ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ " ሲል ማሳወቁን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ ደንበኞቹ እስከ መጋቢት 2 ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ ከመጋቢት 2 በኃላ ግን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ እንዲሁም የATM እና የፖስ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ብሎ እንደነበር አይዘነጋም።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
5.6K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:49:14 ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ የሚያደርግ አካል ከራሺያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ይገጥማል ሲሉ አስጠነቀቁ

የራሺያው ፕረዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው መልዕክታቸው እንዳሉት በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ እቀባ(No Fly Zone) የመጣል እቅድ ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ካልሆነ ግን በጦርነቱ ቀጥታ እየተሳተፉ መሆናቸውን ይወቁ ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የዩክሬን ባለስልጣናት ኔቶ በዩክሬን ከበረራ ነፃ ቀጠና እንዲፈጥር መወትወታቸው ከተሰማ በኋላ ነዉ። ምንም እንኳን የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በዩክሬን የበረራ እቀባ መጣል ማለት የራሺያን የጦር ጄቶች በቀጥታ መትቶ መጣል እንደማለት ስለሆነ ይህን ማድረግ ጉዳዩን ያወሳስበዋል በማለት ይህንን እንደማያደርጉ ቢገልፁም።ዘገባው የዘ ቴሌግራፍ ነዉ
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
5.1K views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ