Get Mystery Box with random crypto!

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወርም በነበረበት እንዲቀጥል ተወሰነ | SMN TV1

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወርም በነበረበት እንዲቀጥል ተወሰነ

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወርም በነበረበት እንዲቀጥል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢቲቪ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

መንግስት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል በሚያዚያ ወር/2014 ዓ.ም የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር/2014 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ ያለምንም ለውጥ በነበረበት እንዲቀጥል ወስኗል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork