Get Mystery Box with random crypto!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ! የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን እሁድ የሚጠናቀቅ ሲሆን ማን | SMN TV1

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ !

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን እሁድ የሚጠናቀቅ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል የውድድሩ አሸናፊ የመሆን እድል ያላቸው ሲሆን ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የሚችለው ከታች በተዘረዘሩት መንገዶች ነው ።

ሊቨርፑል ዎልቨስን አሸንፎ ማንችስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ነጥብ ከጣለ ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የሚያሸንፍ ይሆናል ።

ሊቨርፑል ከ ዎልቨስ ጋር ነጥብ ከተጋራ እና ማንችስተር ሲቲ በ አስቶን ቪላ በስድስት ግቦች ልዩነት ከተሸነፈ ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ እንደሚያነሳ ተገልጿል ።

ማንችስተር ሲቲ በ አስቶን ቪላ 6 - 0 በሆነ ውጤት ከተሸነፈ እና ሊቨርፑል ከ ዎልቨስ ጋር 5 - 5 በሆነ ውጤት ከተለያየ የሊጉ የዋንጫ አሸናፊ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንደሚለይ ተዘግቧል ።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork