Get Mystery Box with random crypto!

SMN TV1

የቴሌግራም ቻናል አርማ sidaamamedianetwork — SMN TV1 S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sidaamamedianetwork — SMN TV1
የሰርጥ አድራሻ: @sidaamamedianetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.34K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @smnminebot
.
.
.
.
.
.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-05 21:37:57
4.6K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:25:10 ሩሲያ በከበባዋ ስር ባሉ 2 ከተሞች ላይ የተኩስ አቁም አወጀች

የሩሲያ ጦር ኃይል በሁለት የዩክሬን ከተሞች ላይ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን የገለጸ ሲሆን የዩክሬን ባለሥልጣናትም ይህንን አረጋግጠዋል።

በሩሲያ ሠራዊት ከበባ ውስጥ የሚገኙት የማሪዮፖል እና የቮልኖቫክሃ ከተሞች ነዋሪዎች ከከተሞቹ መውጫ ሰብአዊ መተላላፊያ እንደሚከፍት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ይህ የተኩስ አቁም ተግባራዊ የሆነው ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ ላይ ሲሆን፣ በከተሞቹ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ እድል ለመስጠት የተደረሰ ስምምነት መሆኑን የሩሲያ የመከካከያ ሚኒስር አመልክቷል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.4K viewsedited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 00:34:41 ሩብል

የምዕራባውያን ማዕቀብ እጅጉን የበረታባት ሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሷል።

አሁን ላይ 1 የሩስያ ሩብል $0.0085 ከ1 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወይም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እየተመነዘረ ነው።

አንድ የአሜሪካ ዶላር በሩስያ ሩብል ሲመነዘር ፦

• ከአንድ ወር በፊት : 76.2 ሩብል
• ከአንድ ሳምንት በፊት : 81.4 ሩብል
• ከአንድ ቀን በፊት : 108.5 ሩብል
• አሁን : 117.18 ሩብል

ምዕራባውያን አንዳንድ የሩሲያ ባንኮች #ስዊፍት የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስርዓትን እንዳይጠቀሙ አግደዋቸዋል።

እገዳውን ተከትሎ ነው የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው የወረደው።

ምዕራባውያን በሩስያ ባንኮች ላይ ጠንካራ የሆኑ ማዕቀቦችን ጥለዋል ፤ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክም 630 ቢሊዮን ዶላር ከማንቀሳቀስ ታግዷል።

አሁንም የምዕራባውያኑ ሀገራት በሩስያ ላይ እየጣሉት ያለው ጠንካራ ማዕቀብ የሩስያን ኢኮኖሚ እንደሚያሽመደምደው እና ከዓለም አቀፉ ስርዓት እንደሚገፋው ተንታኞች እየተናገሩ ነው።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.3K views21:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 22:05:51 ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል።

አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል።

የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.6K views19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 21:55:04 መንግስት የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታወቀ

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላትጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ በላከው መግለጫ አሳስቧል።

@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.5K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 19:12:14 የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ለመግቢያነት ከሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶች በአጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% (ግማሽ) እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ከ1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በተፈተኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 141 ተማሪዎች የፈተና ደንብ ጥሰት በመፈፀማቸው ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲል ኤጀንሲው ገልጿል።

የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነቶች ውጤት በተገመገመበት ሂደት የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር (ሲቪክስ) ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት የታየበት በመሆኑ ውጤቱ ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት እንደሚገለፅ ኤጄንሲው ገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት
(result.neaea.gov.et)፣
በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት (result.ethernet.edu.et)
እንዲሁም በቴሌግራም ቦት (@moestudentbot)
ላይ በመግባት Exam Result የሚለውን በመንካት ውጤት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በ9444 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በመላክ ዉጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ኤጀንሲው አስታውቋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.5K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 19:11:21 ፌስቡክ ሪልስ የተባለ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ይፋ አደረገ!!

ፌስቡክ አጫጭር ቪዲዮችን ማጋራት የሚያስችል
ሪልስ የተባለ አዲስ አገልግሎት ይዞ ብቅ ማለቱን በትናትናው እለት አስታውቋል።

አዲሱ
ሪልስ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በ150 ሀገራት ላይ መለቀቁንም ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ አስታውቋል። ሪልስ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ ከቲክቶክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑ ታውቋል።

ፌስቡክ ይህንን የቪዲዮ አገልግሎት ይዞ ብቅ ያለው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ እየሆነ የመጣውን የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ ቲክቶክን ለመገዳደር እንደሆነም ታውቋል። የሜታ መስራች እና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፤ አዲሱ የሪል የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ከትናንት ምሽት ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በፌስቡክ ላይ መለቀቁን አስታውቋል።

አዲሱ የሪል አገልግሎት ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ እየቀረጹ በሚጭኗቸው ቪዲዮዎች ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉም ነው የተነገረው። በተጨማሪም በቪዲዮዎቹ መካከል ማስታወቂያዎች በማስገባት የቪዲዮዎቹ ባለቤቶች ገቢ ማግኘት የሚችሉበት አስራር እንዳለውም ታወቋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
4.1K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 21:20:49
የገና ሥጦታ ሎተሪ !

የገና ሥጦታ ሎተሪ ሀሙስ ታህሳስ 28/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል።

1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 1977732

2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0341880

3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0929042

4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1357756

5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1288620

6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0614488

7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 20,000 ብር የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 18052

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 05609

9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 4599

10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 6941

11ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 883

12ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 904

13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 22

14ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 4 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
6.5K viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 12:21:21 እንኳን አደረሳችሁ!
@SidaamaMediaNetwork
5.1K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 16:56:26
የሲዳማ ክልል ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን እንቅስቃሴዎችና ክልከላዎችን ይፋ አደረገ

የሲዳማ ክልል አምስት ማዕከላት ያሉት ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ ስራ መጀመሩን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተናግርዋል። ሀዋሳ ፣ለኩ፣ ይርጋለም ፣አለታ ጩኮ ና በንሳ ከተሞችን ማዕከላት ባደረገው ኮማንድ ፖስት በአንድ ሳምንት ውስጥ 83 ግለሰቦች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ሆነዋል። በተጨማሪም በአለታ…
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork
9.4K viewsedited  13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ