Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታወቀ መንግስት | SMN TV1

መንግስት የነዳጅ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታወቀ

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው።

ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን የጠቆመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላትጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ በላከው መግለጫ አሳስቧል።

@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork