Get Mystery Box with random crypto!

የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተ | SMN TV1

የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ለመግቢያነት ከሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶች በአጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% (ግማሽ) እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ከ1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በተፈተኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 141 ተማሪዎች የፈተና ደንብ ጥሰት በመፈፀማቸው ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲል ኤጀንሲው ገልጿል።

የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነቶች ውጤት በተገመገመበት ሂደት የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር (ሲቪክስ) ትምህርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት የታየበት በመሆኑ ውጤቱ ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት እንደሚገለፅ ኤጄንሲው ገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት
(result.neaea.gov.et)፣
በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት (result.ethernet.edu.et)
እንዲሁም በቴሌግራም ቦት (@moestudentbot)
ላይ በመግባት Exam Result የሚለውን በመንካት ውጤት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በ9444 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በመላክ ዉጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ኤጀንሲው አስታውቋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork