Get Mystery Box with random crypto!

ፌስቡክ ሪልስ የተባለ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ይፋ አደረገ!! ፌስቡክ አጫጭር ቪዲዮችን | SMN TV1

ፌስቡክ ሪልስ የተባለ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ይፋ አደረገ!!

ፌስቡክ አጫጭር ቪዲዮችን ማጋራት የሚያስችል
ሪልስ የተባለ አዲስ አገልግሎት ይዞ ብቅ ማለቱን በትናትናው እለት አስታውቋል።

አዲሱ
ሪልስ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በ150 ሀገራት ላይ መለቀቁንም ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ አስታውቋል። ሪልስ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ ከቲክቶክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑ ታውቋል።

ፌስቡክ ይህንን የቪዲዮ አገልግሎት ይዞ ብቅ ያለው በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ እየሆነ የመጣውን የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ ቲክቶክን ለመገዳደር እንደሆነም ታውቋል። የሜታ መስራች እና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፤ አዲሱ የሪል የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎት ከትናንት ምሽት ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በፌስቡክ ላይ መለቀቁን አስታውቋል።

አዲሱ የሪል አገልግሎት ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ እየቀረጹ በሚጭኗቸው ቪዲዮዎች ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉም ነው የተነገረው። በተጨማሪም በቪዲዮዎቹ መካከል ማስታወቂያዎች በማስገባት የቪዲዮዎቹ ባለቤቶች ገቢ ማግኘት የሚችሉበት አስራር እንዳለውም ታወቋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork