Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ በሕግ ያስጠይቃል ትምህር | SMN TV1

በመጪው የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ በሕግ ያስጠይቃል

ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ከመመሪያው ውጭ ወርሃዊ የክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያ እንዳይጠይቁ የአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳሰበ።

የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት ከመመሪያው ውጭ የክፍያ ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ እዳያደርጉ ያዛል።

ነገር ግን መመሪያውን በመጣስ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች አስቀድመው በደብዳቤና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለወላጆች መልዕክት እያስተላለፉ መሆኑ ተደርሶበታል ብለዋል።

መመሪያውን በሚጥሱ ትምህርት ቤቶች ላይ ፈቃድ የመሰረዝና በሕግ የማስጠየቅ እርምጃዎች እንደሚወስድ ከወዲሁ አሳስበዋል።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork