Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ ንግ | SMN TV1

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ

ንግድ ባንክ " መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም " ብሏል።

ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም #ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።

የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውን እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ብሏል ባንኩ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለው ትክክል እንዳልሆነ ባንኩ ገልጿል።

አክሎም " ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ " ሲል ማሳወቁን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ ደንበኞቹ እስከ መጋቢት 2 ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ ከመጋቢት 2 በኃላ ግን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ እንዲሁም የATM እና የፖስ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ብሎ እንደነበር አይዘነጋም።
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork