Get Mystery Box with random crypto!

ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ የሚያደርግ አካል ከራሺያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ይገጥማል | SMN TV1

ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ የሚያደርግ አካል ከራሺያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ይገጥማል ሲሉ አስጠነቀቁ

የራሺያው ፕረዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው መልዕክታቸው እንዳሉት በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ እቀባ(No Fly Zone) የመጣል እቅድ ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ካልሆነ ግን በጦርነቱ ቀጥታ እየተሳተፉ መሆናቸውን ይወቁ ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የዩክሬን ባለስልጣናት ኔቶ በዩክሬን ከበረራ ነፃ ቀጠና እንዲፈጥር መወትወታቸው ከተሰማ በኋላ ነዉ። ምንም እንኳን የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በዩክሬን የበረራ እቀባ መጣል ማለት የራሺያን የጦር ጄቶች በቀጥታ መትቶ መጣል እንደማለት ስለሆነ ይህን ማድረግ ጉዳዩን ያወሳስበዋል በማለት ይህንን እንደማያደርጉ ቢገልፁም።ዘገባው የዘ ቴሌግራፍ ነዉ
@SidaamaMediaNetwork

@SidaamaMediaNetwork