2023-04-19 09:57:21
ሐዋርያው ጳውሎስን ክፍ ባለጀርነት መልካሙን ያጠፍዋል ይለናል
ሔዋን የእባብን ጓደኝነት መርጣ ከእግዚአብሔር እቅፍ ከገነት ስትባረር አይተናል
መልካም ባለጀራ ጥበበኛው ሰሎሞን ብረት ብርሃን ይስላል ሰውም ባለጀራውን ይስላል እንዲል
የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ለቅጽበትም ቢሆን አእምሮው ሊረሳውና ሊያቋርጠው የማይችለው ነገር ምን እንደሆነ አስባችሁት ታውቃላችሁ? ሰውነቱ በእንቅልፍ ተሸንፎ እንኳን ቢተኛም እያንቀላፋ አስታውሶ የሚያደርገው ክንውን የትኛው እንደሆነ አስተውላችኋል? እንደው አይሆንም እንጂ ሆኖለት ለደቂቃዎች ሰውነቱ ይህንን ተግባር በመርሳት ባያከናውነው ሕልውናው አጠያያቂ ሁኔታ ውስጥ ይወድቃል፡፡ ይህ ሰውነታችን ልምድ ያደረገውና ለአፍታ እንኳን መቋረጥ የማይፈልገው ተግባር አየር ማስገባትና ማስወጣት ወይም መተንፈስ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጸሎትን እንደ ነፍስ እስትንፋስ ይቆጥሯታል፡፡ አየር ያጠረው ወይም ወደ ሰውነቱ የማያስገባ ሰው በሕይወት የመቆየት ዕድሉ ጠባብ እንደሆነ ፤ እንዲሁ ከጸሎት የተለየች ነፍስም ወደ ሞት መንደር የመውረዷ ነገር የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ነፍሳችን ሕያዊት የምትሰኘው በአረጋዊ መንፈሳዊ መጽሐፍ ላይ ‹የነፍሴ ነፍሷ› ተብሎ ከተጠራው መንፈስ ቅዱስ ጋር በጸሎት ትስስርን ስትመሰርት ነው፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙም እንደሚያስተምረው ሰው ከእስትንፋሱ የበለጠ ዘወትር ፈጣሪውን በጸሎት ሊያስታውስ ይገባዋል፡፡
ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ‹ጸሎትስ ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ነገር ናት› ሲሉ የጸሎትን ትርጉም ይነግሩናል፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በልዩ ልዩ አይነት መንገድ ሊያናግራቸው ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በራእይ በመገለጥ ወይም ቅዱስ ዳዊት ‹እግዚአብሔር ለሕዝቡ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል› ሲል እንደ ዘመረው በመጽሐፍ በኩል ማናገር ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከፈጣሪያቸው ጋር የሚነጋገሩት ጸሎት በተባለ ድልድይ አማካኝነት ያነጋግሩታል፡፡
መተንፈስ ለሥጋዊው አካላችን የዕለት ተዕለት የማይቋረጥ ሥራው እንደሆነ ሁሉ የነፍስ እስትንፋስ የተባለች ጸሎትም ለክርስቲያን የየዕለት መንፈሳዊ ተግባር ናት፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹ሳታቋርጡ ጸልዩ› በማለት የሚመክረን (1ኛ ተሰ 5፡17)
አጠቃላይ አባታችን አባ ገብረ ኪዳን ስተምሩ አለመጸለይ ማለት እኔ እራሴ በራሴ የመኖር ሀይል(ስልጣን) አለኝ የእግዚአብሔር ጥበቃ አያስፈልገኝም እንደ ማለት ነው ።
ከስህተቴ እማራለው
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አዘጋጅ ጸሐፊ ሜሮን
መጠየቂያ
@Men_Lerdawobot
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
@seratebtkrstian
አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ በዚህ በኩል ያናግሩን!
@Men_Lerdawobot
1.5K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited 06:57