Get Mystery Box with random crypto!

የጠፋሁበት ምክንያት ምኞቴ ተሳክቶ ፍሬ አፍርቶ ላይ ነው.... ይሄ የምትመለከቱት ቤተ ክ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የጠፋሁበት ምክንያት

ምኞቴ ተሳክቶ ፍሬ አፍርቶ ላይ ነው....


ይሄ የምትመለከቱት ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሐገረ ስብከት በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወራዳ ሐብትዪ ቀበሌ የምትገኝ የቅድስት በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ነው!

ተአምረኛው የሸንኮራ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የምትገኝ ሲሆን መኪና ስለማይገባባት ብዙም ገቢም ሆነ ቱሪስት ማገኘት አልቻለችም ካህናቱም የሚተዳደሩት በግብርና ነው!(የተወሰነ ነው ሚከፈለው እሱም ከተገኘ በ6 ወር ካልተገኘ 1 አመት) ሆኖም እንዲህ ሆኖ ሳል ይቺን ቤተ ክርስቲያን የተከሏት መምሬ ሽመልስ ይባላሉ እና እሳቸው እርዳታህን እፈልጋለሁ ብለውኝ በዓልን አጣጥሜ ሳልበላ ተጠርቼ ሄድኩ ቦታውንም አየሁት ወደድኩት ከዛ ምን አስበው ነው ስላቸው አንድ ነገር አጫወቱኝ! አርጅተዋል እና ከመሞቴ በፊት ሁል ጊዜ አንድ ነገር እመኛለሁም እጸልያለሁም እና በዓታ ለማርያም ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ስትገባ ቅዱስ ፋኑኤል ነው የመገባት እና በንግሥ ሰዓት ብቻዋን ከምትወጣ አብረው ቢሆኑ የእርሱን አዲስ ጽላት (ታቦት) አስገብቼ ባስገባሁም እለት ከነ ባለቤቴ ቆርቤ ብሞት ምንም አይቆጨኝ! እናም ምን ታስባለህ? ሲያወሩ ፊታቸው ላይ የነበረው ፈገግታ ፍጹም ከፊቴ አይጠፋም! ደስ ነው ሚለኝ አልኳቸው ከዛ ደብዳቤ ምናምን ተዘጋጀ ወዘተ.... ያለው ሁኔታ በሙሉ ከሰፈሩ ሰው ከካህናት ጋር ውይይት ተደረገ ተስማሙ ከዛ ለሊቀ ጳጳሱ ተላለፈ ፈቀዱ! እና የፊታችን ግንቦት 1 ቀን የቅዱስ ፋኑኤል ታቦት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይገባል ! ይከብራል እሳቸውም ይቆርባሉ!

እናም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እነሱ ጋር ነበረ ያረፍኩት እና የተለያዩ የድሮ መጻህፍት አስነበቡኝ መጽሐፈ ብርሃን የሚባል ከየት እንዳመጡት አላውቅም አስነበቡኝ የሚገርም ነገር ምስጢርንም ነገሩኝ! ከዛ ከሆነች መጽሐፍ ላይ ስለ 8ተኛው ሺ ሲነግሩኝ እያነበቡ ሲያስረዱኝ በቃ ዛሬ ነው ዳግም ምጽአት ብዪ የወሰንኩት እናም ግን ገና ነው እያሉ እያንዳንዱን ነገር ነገሩኝ! ለህይወቴ የሚጠቅመኝን ምክር ማር በሚያፈልቀው አፋቸው እየነገሩኝ መገቡኝ!

በተረፈ አሁን ሁሉም ነገር ተጠናቆ ወደ ቀደመ ክብሬ ተመልሻለሁ!

ግንቦት አንድ ቀን ምንጃር ሸንኮራ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን እንገናኝ!

ለዚህ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እገዛ ማድረግ የሚፈልግ ካለ በማንኛውም ሰዓት ሊያናግረኝ ይችላል! @fekrAbe @fekrAbe @fekrAbe


መልካም ምሽት


አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join