Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ seratebtkrstian — ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube
የሰርጥ አድራሻ: @seratebtkrstian
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.08K
የሰርጥ መግለጫ

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-17 19:55:50 ጥያቄ እና መልሱ ፋንታ ረጅም ጊዜ ሲጠበቅ እና በጣም ብዙ ሰዎች ሲጠይቁት ለነበሩ መልስ ቢሰጥ የሚሻል ይመስለኛል! የእናንተን ሐሳብ ባላውቅም ! ጥያቄውም ግብረ አውናን (ማስተርቤሽን)((ሴጋ)) የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል ወይስ አይገባውም? የሚለውን ብንመልስ የተሻለ ይመስለኛል ! ይሄ ቀርቶ normal ጥያቄ እና መልሱ ይሻላል? ወይስ ጥያቄ እና መልሱ ቀርቶ ይሄ ማብራሪያ ቢሰጥ ይሻላል? ምረጡ እስኪ ቶሎ በሉ!
2.7K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 22:37:59 በዓል ልዩ ነበር በስመ አብ ግን እንዴት አሳለፍክ ብላችሁ እንዳጠይቁኝ (ንጉሱ የጻፍኩት ጻፍኩ እንዳለው) ባሳለፍኩት አሳልፌያለሁ ! እጅጉን ደስ ብሎኛል ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን ክብሩ ይስፋ ጸጋው አይጓደል! እናንተም ደስ የሚል በዓል እንደምታሳልፉ ተስፋ አደርጋለሁ! እና መልካም በዓል! እግዚአብሔር ከፈቀደ ነገ ሙሉ አገልግሎት (ጥያቄ እና መልስ 250 ላይ ነበር ያቆምነው እንቀጥላለን) ሠላም አደሩልኝ!
781 viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 20:58:41
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!!
መልካም የትንሣኤ በዓል

ከትንሳኤ በኋላ ያለው ሳምንት ሰባቱም ቀን እያንዳንዱ ትርጉም አለው ትርጉሙን ለማወቅ

https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
https://t.me/+RkglPUfilfs4MDFk
1.2K viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:21:39 ከሆሳዕና ጀምሮ እያንዳንዱን ሥርዓት ከዜማ ጋር እያዋኻድኩኝ ሳቀርብላችሁ የቆየሁት እኔ ዲ/ን ፍቅረ አብ እባላለሁ! እንኳን አደረሰህ? መልካም በዓል አትሉኝም?
2.0K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:27:15 ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሠላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሃ ወሰላም!

የክርስቶስ ሰላም ከእኔ እና ከእናንተ ጋራ ይሁን!

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል ከቤተሰብዎ ጋር።

Happy Easter to our Lord and Savior Jesus Christ. Happy Holidays with your family






አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join
3.5K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, edited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:49:13 #ምስባክ ዘትንሣኤ (ዘማሕሌት)

መዝ 77÷65
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም።
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን።
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።


ድምጽ ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ወቲዩብ

@seratebtkrstian
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ
2.7K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:46:53 # ዕለተ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ ዘቅዳሴ

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን ቆሮ15÷20-41
ን/ዲ 1ጴጥ 1÷1-13
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 2÷22-37

፡#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 117÷24
ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ።
ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ።
ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።


#ትርጒም፦
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት።ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን።አቤቱ እባክህ አሁን አድን።

#የዕለቱ_ወንጌል፦

ዮሐ፥20 ÷1- 19

ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian


join
2.2K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:46:53 ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ #ትንሣኤ

ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ከዛሙ ሙሉ የዮሐንስ ወንጌል ይነበባል! ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።

"ተፈሥሂ #ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል : መልክዐ ስዕል ግን ዛሬን ጨምሮ እስከ በዓለ ፶ ፍጻሜ ድረስ አይባልም። ከእላይ አለላቹ ፈልጉ ወደ እላይ ለቅቄላችኋለሁ!

ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል : ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና አራቱም ወንጌላት ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።

ይ.ዲ #ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ #እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

#አርያም
ሃሌ ሉያ #ለአብ : ሃሌ ሉያ #ለወልድ : ሃሌ ሉያ #ወለመንፈስ_ቅዱስ : ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ ዛቲ #ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ #ለአብ : ሃሌ ሉያ #ለወልድ : ሃሌ ሉያ #ወለመንፈስ_ቅዱስ : ይገብሩ በዓለ ደመናት : ወምድርኒ ትገብር #ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

#ምልጣን
ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ #ክርስቶስ እሙታን : ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ : አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።

#እስመ_ለዓለም
ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።

ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ "ይእቲ #ማርያም" የሚለው የኪዳን መግቢያ ይዘመማል ፣ ይመረገዳል።

#መዝሙር
ትትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር : ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ : ወይበውኡ አድባር ወአውግር : ወኲሉ ዕፀወ ገዳም : ወዮምሰ አባይ ፍሥሃ በሰማያት : ወምድርኒ ትገብር #ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።

#ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ : ተካፈሉ አልባሲሁ : ሐራ ሰገራት ወኮርዕዎ ርእሶ በሐሰት : ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት : ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት : ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት ለአሕዛብ ወለበሐውርት።

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian


join
1.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:46:53 ተፈሥሒ ማርያም ዘሰንበት ዘበዓለ ሃምሳ (ከትንሳኤ እስከ በዓለ ሃምሳ የሚባል መልክአ ሥዕል)

ሰላም ለማርያም አጽፈ ወልድ ዋህድ ወመንበረ ሕያው ነድ፣ ለድንግልናሃ ይደሉ ሰጊድ ለማርያም ዘይቤ ኢይሰግድ፣ ሞጸፈ መብረቅ በሊህ በርእሱ ለይረድ።

ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ፣ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ፣ እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ፣ በወርኃ ዕብሬትኪ እግዝእትየ ዘኢይትረከብ ከማሁ፣ መኑ ዘይቴክዝ ወመኑ ዘይላሁ።

ተፈሥሒ ማርያም ወለተ አሮን ወሙሴ፣ ዘትትቄጸሊ አብያዘ ወትሴአኒ ብናሴ፣ ለኃይለ ተአምርኪ ዝንቱ ሶበ ናቄርብ ውዳሴ፣ ኅትሚ ፍጽመ ዚአየ በማኅተመ ቅድስት ሥላሴ፣ አርእስተ አቃርብት ንኪድ ወንቀጥቅጥ ከይሴ።

ተፈሥሒ ማርያም ወለተ ዳዊት ወወልዱ፣ ጽጌ መዓዛ ዘዐርገ ለአብርሃም እምሥርወ ጕንዱ፣ ያስተፌሥሐኒ ጥቀ ዜና ተአምርኪ ለለአሀዱ፣ አይሁድሰ ሶበ መንክራተኪ ክህዱ፣ ሕያዋኒሆሙ ሲኦለ ወረዱ።

አአኵተኪ ማርያም ወሀቢተ ጸጋ በከንቱ፣ እስመ አልዓልክኒ ሊተ እመሬተ ምድር እስከነ ታሕቱ፣ አንሥኦተ ነዳይሰ ወዓልዕሎ ምስኪን ጊዜ ድቀቱ፣ እወ እወ ለልብኪ ከመ ከማሁ ሥምረቱ፣ እወ ለዘኒ ፈቀድኪ ታሤንዪ ሎቱ።

ነአኵተኪ ማርያም ወንሴብሐኪ ወትረ፣ ሠርከ ወነግሀ ኵሎ አሚረ፣ ለኃይለ ተአምርኪ ዝንቱ ሶበ ንሬኢ ኅቡረ፣ ለልበ ጠቢባን መላእክት ዘያረስዖሙ ምክረ፣ ወለሐፃናት ይከሥት ሥውረ።

ጽብዒ ማርያም ለእለ ይጸብዑኒ በተሀብሎ፣ ወግፍዒ ካዕበ ለእለ ይገፍዑኒ ኵሎ፣ ተአምረኪ ታርኢ ወለወልድኪ በቀሎ፣ ይብል ዓብድ አኮኑ እግዚአብሔር ኢሀሎ፣ ሶበ ላዕሌሁ ፍጡነ ኢያርአየ ኃይሎ።

ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ መዋዒ፣ ከመ ታውድቂ ፍጡነ ርእሰ ፀር ወጸላኢ፣ እስመ ፈታሒት አንቲ ማዕከለ ግፉዕ ወገፋዒ፣ ብጹዕ ብእሲ ድቀተ ፀሩ ዘይሬኢ፣ ወብጹዕ ካዕበ ፍትሐኪ ሰማዒ።

ዝ ውእቱ እድሜ ሣህልኪ ወዘተአምርኪ ጊዜ፣ ማርያም ድንግል ምልዕተ ምሕረት ከመ ተከዜ፣ እስከ ማእዜኑ እሄሉ ማዕከለ ብካይ ወእንባዜ፣ ኦ ናዛዚት እንተ ወለድኪ ናዛዜ፣ ኦ ንግሥት በቋዒት ብቊዕኒ ይእዜ።

ሙሴ ነቢይ አመ ሕዘቢሁ ቆስሉ፣ ተአምረ ገብረ ለአርዌ ብርት በምስሉ፣ እምዝኒ የዐቢ ኃይለ ተአምርኪ ንግሥተ ኵሉ፣ ወኀበ ተተክለ ለዋህድኪ መስቀሉ፣ ሠራዊተ ደዌ ወሞት ቀሪበ ኢይክሉ።

ፈሪሆትኪ ማርያም ቀዳሜ ኵሉ ተዐውቆ፣ ወአፍቅሮትኪ ካዕበ መሠረተ ጥበብ ወአጠይቆ፣ ተአምረኪ እሴብሕ በቃለ መዝሙር ወመሰንቆ፣ በውስተ ተአምርኪ እግዝእትየ ለዘአብአ ናፍቆ፣ አፍቲዎ መዊተ ወሲኦለ አጽሐቆ።

ምንተ ረከቡ ካህናተ ሀሊባ ወሐላ፣ መንክራተ አምላክ ዘርእዩ እምሰኪኖን እስከ ገልገላ፣ ካህናተ ቤትኪሰ ማርያም ርግበ ገሊላ፣ እንዘ ይትአመኑ ለተአምርኪ ኃይላ፣ ያፈልሱ ደብረ ወይመልሑ ሰግላ።

ይቴክዝ ዓብድ ሶበ ልበ ጥበብ ውህዶ፣ በኢያእምሮቱ አብዝኀ ሕማመ ዘይፈድፍዶ፣ ፍሡሕሰ ለፍቅርኪ ዘይፀመዶ፣ በቅድመ ሥዕልኪ እግዝእትየ ለለጊዜ ያነሥእ እዶ፣ ተስፋሁ ይረክብ ወይፌጽም መፍቅዶ።
ዕቀብኒ በተአምርኪ ወአድኅንኒ እምማቴ፣ በከመ አድኃኖ ወልድኪ ለዮናስ ወልደ አማቴ፣ መዋዕለ ዕረፍት ❖አንቲ ማርያም ጰንጠቆስቴ፣ እምኃይለ ድካም ያጸንዕ መዋቴ፣ ኅብስት ስብሐትኪ ወፍቅርኪ ስቴ።

ሴስይኒ ማርያም ለጸማድኪ አሳብ፣ ኅብስተ አእምሮ ሠናየ ወወይነ ጥበብ፣ እመኒ ፈድፈደ ኃጢአትየ እምሕዝብ፣ ተዘከሪ እግዝእትየ በርኅራኄኪ ዕጹብ፣ ከመ አስተኪዮ ማየ ለጽሙእ ከልብ።

ኦ ፍጡነ ረድኤት ለጽኑዕ ወለድኩም፣ ወለነፍሰ ኵሉ ቃውም፣ ጊዮርጊስ የዋህ እንበለ መስፈርት ወዓቅም፣ ከመ እግዝእትከ ቡርክት ማርያም፣ እስመ ርኅሩኀ ልብ አንተ እምበቀል ወቂም።

ኦ ፍጡነ ረድኤት በብዙኅ ፆታ፣ ከመ እግዝእትከ ርግበ ኤፍራታ፣ በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታሕታ፣ አምሕለከ ጊዮርጊስ በስመ እምከ ቴዎብስታ፣ ሞገሰ ስምከ ተሀበኒ ከመ ስምከ መንታ።

ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጸተ ነፋስ ወዓውሎ፣ ለዘይጼውዐከ በተወክሎ፣ ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ፣ ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራህየ ኵሎ፣ እስመ ልበ አምላከ ርኅሩኅ በኀቤከ ሀሎ።

አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ ምንዳቤ ወዓጸባ፣ ለዓይን እምቀራንባ፣ አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፣ በኵሉ ኅሊናሃ ወበኵሉ አልባባ፣ ዘኢታፈቅረኪ ነፍስ ትሠሮ እምሕዝባ።

ለዘኢያፈቅረኪ እግዝእትየ ማርያም ውኩፈ ኢይኩን ጸሎቱ፣ ይትገዘም ኑኃ ዓመቱ ወይጥፋእ በከንቱ፣ በአፈ መላእክት ወሰብእ ይትረገም ለለዕለቱ፣ ዘአስተማሰሎ በተውኔት ለማኅሌተ ስምኪ ዝንቱ፣ ጌጋዩ ወኃጢአቱ ኢይትኃደግ ሎቱ።

እሰግድ ቅድመ ማርያም ለዝክረ ስምኪ በጽዋዔ፣ ወእሰግድ ካዕበ ለድንግልናኪ ክልኤ፣ ወእሰግድ ሥልሰ ለሥዕልኪ ቅድመ ጉባኤ፣ ዘኢሰገደሰ ለሥዕልኪ አስሪፆ ምምኤ፣ በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሣኤ።

ምንተኑ አዓሥየኪ ዕሤተ፣ በእንተ ኵሉ ዘገበርኪ ሊተ፣ ማርያም ሠናይት ዘታፈቅሪ ምሕረተ፣ ሶበሰ ተትዓቀቢ ዘዚአየ ኃጢአተ፣ እምኢሐዮኩ አሐተ ሰዓተ።

በሰላመ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣ ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ፣ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ፣ ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ፣ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ።
ከዚህ ቀጥሎ
ተአምረ ማርያምና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል።

ከዛ ምስባክ!


አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian


join
1.7K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:46:53 ሓተታ ዘትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ?


አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ወቲዩብ


«ትንሣኤ»
የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
አከፋፈል
አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡

ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡

ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡

አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የእርሰ ትምህርታችንም መሠረት ይኸው እንደሆነ ይታወሳል፡፡

አምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

#የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ» ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ #መሥዋዕት፣ #መሻገር #መሸጋገር ማለት ነው፡፡

#ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡

#ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ #ከኀጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር = ከውርደት ወደክብር፣#ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ #ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ #ከአደፈ፣ #ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡

#ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡
#ባህሉስ
ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡፡

አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!!


https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian


join
1.8K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ