2023-04-17 21:18:10
ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ይገባዋል?
ክፍል አንድ
በወጣትነት ወራት ሰለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር
ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራቢያ አካላቸውን በመነካካት
ጾታዊ ሰሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር
ሴጋ ወይም ግለ ወሲብ በመባል ይታወቃል።
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሰለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን
የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን
ጥያቄ ለመመለስ ነው። ተወዳጆች እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ
የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን
ቪዲዮ ሰለፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ወይም ከሴት ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማያውቅ
ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን ሰለፈጸመ
ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ነው። እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት
ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው
ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንድ ጋር በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን
ፈጽሚያለሁ ድንግል ልባል እችላለሁ ለደናግላን የሚፈጸመው ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ
ልፈጸምልኝ ይችላል? የሚለው ዋነኛ ነው።
ይህ ጥያቄ በራሱ ተገቢነት የሌለው ትሕትና በማጣት ዲያቢሎስ እየፈተነን መሆኑ ማስረጃ
ነው። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ከማንኛውም የዝሙት ተግባር እርቆ ከኖረ በኋላ ተክሊል
ሊፈጽምለት ሲል አረ አይገባኝም በማለት ራሱን ዝቅ ያደርጋል። ከዚህ በተቃራኒ ራስን በራስ
የማርካት የዝሙት ኃጢአት የኖረ ሰው ተክሊል ይገባሃል ቢባል እንኳን አረ እኔ አይገባኝም
ብሎ በተሰበረ ልብ ሊርቅ ሲገባው በማስተርቤሽን ኃጢአት የዝሙትን ተግባር ሲፈጽም ከኖረ
በኋላ ተክሊል ይገባኛል ብሎ መጠየቅ ልባችን በፈጸምነው ኃጢአት አለመሰበሩን ማረጋገጫ
ነው።
አንዲት ሴት ራሷን የዝሙትን የኃጢአት እርካታ የመራቢያ አካሏን በመነካካት እያረካች
ከኖረች በኋላ እንዴት ባለ ድፍረት ነው ተክሊል ይገባኛል ብላ የምትጠይቀው? ይቺ ሴት
ከወንድ የምታገኘውን የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ከራሷ እያገኘች ከሆነ ከጋብቻ ውጭ ከወንድ
ጋር ዝሙት ከሰሩት ሴቶች በምን ትለያለች? ምንም ከወንድ ጋር በምንጣፋ አንድ ባትሆን
በሕሊናዋ ወንድ ከማሰብ አልፋ በፈቃዷ አፈ ማኅፀኗን እየነካካች የዝሙትን ተግባር
ሰለፈጸመች ድንግል ተብላም አትጠራም።
በሉቃስ ወንጌል ላይ የሚገኝ አንድ ታሪክ አለ። ይህ ሕያው ታሪክ ከአባቱ ተለይቶ የኮበለለው
ልጅ ሕይወትን ያስነብበናል።ይህ ልጅ ከአባቱ ለመለየት መወሰኑ ስህተት መሆኑ ገብቶታል።
ሰለዚህም የሰራውን ስህተት ለማረም ሲነሳ ወደ አባቱ ለመመለስም ሲወስን እንዲህ ብሎ
ነው ያሰበው " ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና አባቴ ሆይ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ወደ
ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።" (የሉቃስ
ወንጌል 15:18-19 ) ይሄ ልጅ በአባቱ ላይ ማመጹ ኃጢአት መስራቱ ፈጽሞ እንደጸጸተው
የምንረዳው " ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም" በሚለው ንግግሩ ነው። ወደ አባቱ ቤት
ሲመለስ ሰለመብቱ እያሰበ አልነበረም በልጅነት ክብር መጠራት እንደማይገባው አምኖል
ወደ አባቱ ቤት የተመለሰው በአባቱ ቤት ከሚሰሩት ሙያተኞች መካከል እንደ አንዱ ሁኖ
በባርነት ለማገልገል ነበር። ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ወደ
እግዚአብሔር ሲመለስ ድንግል ልባል የደናግልና ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል
የተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል የትዕቢት ሐሳብ በልቡ ከያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ
ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ማሽተርቤሽን ቪዲዮ ሴክስ ፎን ሴክስ ከፈጸሙ በኋላ " በአካል
ከተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነት አላደረኩም ተክሊል መፈጸም ይፈቅድልኛል?" የሚል ጥያቄ
በአእምሮቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው።
ምክንያቱም ማሽተርቤሽን ቪዲዮ ሴክስ ፏን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅብረ ዝሙት እየፈጸምን
ያሳሰበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት
አስተሳሰብ " የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።
ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈትታ የኮበለለች ሴት ናት።
ከሄደችበትም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት
ጊዜ የነበራት ምቾትና ክብር ነው። አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም።
ማለትም ኃጢአት ሠርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀምኩት እያለ ስለ በደሉ ያለቅስ
ነበረ እንጂ የገነት ተድላ ደስታ ቀረብኝ እያለ ስላጣው ነገር አያዝንም ነበር። " አልቦቱ ካልዕ
ሕሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ ሰለ ኃጢአቱ ከማልቀስ በቀር ለአዳም ዘእንበለ
ብካይ አልነበረውም። የተባለው ሰለዚህ ነው።
እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተስነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን? ተክሊልስ
ይገባኛል? " እያለ ያጣውንና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ " አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም
ክፋትን አደረግሁ ።" (መዝሙረ ዳዊት 51: 4) ማለት ኃጢአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ
አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ይባላል።
ይቀጥላል.....
አዘጋጅ
ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
@seratebtkrstian
join
2.9K viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 18:18