Get Mystery Box with random crypto!

የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ selefiyya — የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ selefiyya — የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @selefiyya
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85
የሰርጥ መግለጫ

ኑ እንማር، የተፈጠርንለትን አላማ እንወቅ!!!!
ይህ ግሩፕ በምስራቅ እስቴ ወረዳ ያሉ በማወቅም ይሁን በቸልተኝነት በሽርክና በቢድዓ የተዘፈቁ ወንድም እህቶችን ከሽርክና ከቢድዓ በማላቀቅ በአሏህ እገዛ ወደ ተውሂድ እና ሱና ለማምጣተ የተከፈተ ቻናል ነው።።
ቻናሉን ከወደዱት
ለአስተያየት ፣እርማትና ጥቆማ
👇👇👇👇👇
@discussbot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-20 18:08:37
አላህ ብሄርና ጎሳን እንድንተዋወቅበት እንጂ እንድንናናቅበት እና እንድንተናነቅበት አላደረገም።
ከእኛ ውስጥ በላጩ አላህን ይበልጥ ፈሪው ነው።
50 viewsአቡ ሐናን, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 07:53:59 ሙመይዓ ማለት ምን ማለት ነው
<========================>
ሙመይዓ ማለት {ኢስመል ፋኢል} ሲሆን ፡–
[ማዓ የሚዑ ተምይዓን]
ፈሁወ ሙመይዕ ከሚለው ቃል የተያዘ ሲሆን አሟሚ አቅላጭ ማለት ነው።

ይህ ስምም በሰለፊያ ስም ሰርገው ለገቡ አንዲሁም የሰለፍያ ደዕዋ በሂማ በነሻጣ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርጉ ተፍረክርከው የሚያፍረከርኩ የዘቀጡ የቀለጡ ሀቅ ስትናገር
ኡስሉብ የለውም የሚሉ እና አንተንም ሊያቀልጡ የሚፈልጉ ዕራሳቸውን የሰለፊያ ልብስ ያለበሱ ድብቅ{ሙተሰቲር} ኢኸዋኒይ
ሱሩሪዮች ናቸው።

ከባህሪወቻቸው ውስጥ
1 ሲናገሩ ኢጅማል ማድረግ{በድፍኑ መናገር}

2 በ አህለል ቢድአ ላይ ዘምተኛ ናቸው ብሎም ሌሎችን ዝም የሚያሰኙ ናቸው {ዐሳኪቱ ወል ሙሰኪት}

3 ለአህለል ቢድዓወች ከለላ ማድረግ

አሁን ላይ እነዚህ ባህሪወች ያሉበት አካል ማንም ይሁን ማን በፊት የሰለፊያ ዳዒም ይሁን መሪ አሁን ላይ ይህ ባህሪ ካለበት
አትጠራጠር ይህ ሰው ''ጠማማ'' ነው ጠሞ አጥማሚ ነው።
ልንጠነቀቀው ይገባል
ካልሆነ ግን ይህ በሽታ ይጋባብህና ያደናግርሀል
ጠንቀቅ ማለት ይጠበቅብሀል
ይህንን ለማወቅ ደግሞ የሰውየውን የበፊት አቋም እና አሁን ያለበትን ብትመዝነው ግልፅ ይሆንልሀል።
አ ስ ተ ው ል
53 viewsአቡ ሐናን, 04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-18 21:34:41 በሌላ አባት ወይም በሌላ ዘር መጠራት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በሃገራችን በተለያዩ መነሻዎች ያለ አባታቸው የሚጠሩ ሰዎች አሉ። ለምሳሌ ወላጆች በግጭት ሲለያዩ ልጅ ካላቸው ልጁን የሚያሳድጉ ሰዎች ለአባቱ ባላቸው ጥላቻ የተነሳ በራሳቸው ቤተሰብ ስም ሲጠሩ ያጋጥማሉ።
ልክ እንዲሁ ያለ ዘራቸው በሌላ ዘር ወይም በሌላ ብሄር እራሳቸውን የሚገልፁም በጣም ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ዐረብ ሳይሆኑ ዐረብነትን የሚሞግቱ ቁጥር ስፍር የላቸውም። ልክ አይሁድ ሳይሆኑ "አይሁድ ነን"፣ "የሰለሞን ዘር ነን" እንደሚሉት።
ሃገር ውስጥ ካሉ ብሄሮች ሆነውም ብሄራቸውን ደብቀው ያልሆኑትን በሌላ ብሄር የሚጠሩና የሚታወቁም በጣም ብዙ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በማስተባበልም ሆነ በማስጠጋት ቢፈፀሙ ከባድ ጥፋቶች ናቸው።
★ በማስተባበል ማለት: – የራሱን መካድ፣ መደበቅ፣ የሆነውን እንዳልሆነ መሞገት፣ አባቱን፣ ዘሩን፣ ብሄሩን መካድ፣ ማስተባበል።
★ በማስጠጋት ማለት:– እራሱን በሃሰት ወደሌላ ሰው፣ ወደሌላ ዘር፣ ወደሌላ ብሄር ማስጠጋት፣ በሃሰት በሌላ መግለፅ።
በሁለቱም በኩል ቢፈፀም ከከባባድ ጥፋቶች (ከከባኢር) ነው። ቀድሞ ባለማወቅ ተፈፅሞ ከሆነ ስህተቱን ወይም ችግሩን የተረዳ ሰው ሊያስተካክል ይገባል።
ከአቡ ዘር ረዲየሏ፞ሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

"لَيْسَ مِنْ رَجُلٍ ادَّعَى لِغَيْرِ أَبِيهِ، وَهُوَ يَعْلَمُهُ، إِلَّا كَفَرَ. وَمَنِ ادَّعَى قَوْمًا لَيْسَ لَهُ فِيهِمْ فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ".
"እያወቀ ያለ አባቱ ሌላን የሚሞግት (በሌላ የሚጠራ) ሰው አይኖርም፣ የካደ ቢሆንጂ።
ከነሱ ሳይሆን ወደሆኑ ወገኖች እራሱን በማስጠጋት የሞገተ መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

በተጨማሪም ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"إِنَّ مِنْ أَعْظَمِ الْفِرَى أَنْ يَدَّعِيَ الرَّجُلُ إِلَى غَيْرِ أَبِيهِ".
"ከከባባድ ቅጥፈቶች ውስጥ አንዱ አንድ ሰው አባቱ ወዳልሆነ ሰው መሞገቱ (እራሱን ማስጠጋቱ) ነው።" [ቡኻሪ: 3509]

"مَنِ ادَّعَى إِلَى غَيْرِ أَبِيهِ، وَهُوَ يَعْلَمُ فَالْجَنَّةُ عَلَيْهِ حَرَامٌ ".
"እያወቀ ከአባቱ ውጭ ወደሌላ ሰው የሞገተ ሰው ጀነት በሱ ላይ እርም ነች!!" [ቡኻሪና ሙስሊም]

የቴሌግራም አድራሻ:-
https://t.me/IbnuMunewor
46 viewsአቡ ሐናን, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 15:49:58 ነብዩ ዐለይሂሠላም እንዲህ ይላሉ፡-
“የፈለግከውን ያክል ብትኖር ትሞታለህ!
የፈለግከውን ብትወድ ትለየዋለህ!
የፈለግከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ!
እወቅ! የሙእሚን ክብሩ የሌሊት ሶላት መስገዱ፣ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው፡፡”
(ሐኪም ዘግበውታል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)

https://telegram.me/IbnuMunewor
46 viewsአቡ ሐናን, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-08 20:51:12
ይድረስ ዊግን ለምትጠቀሙ ሴቶች!!

"ጸጉር ቀጣይ የሆነችንና ጸጉር አስቀጣይ/የምታስቀጥል የሆነችን ሴት አላህ ረግሟታል" ብለዋል ሐቢቡና صلى الله عليه وسلم

ምንጭ. [ رواه البخاري ومسلم]

አሏህ በሰጠሽ ፀጉር ተብቃቂ!!

ጌታሽ ሙሉ አድርጎ ፈጥሮሻል ሰርቶሻል!!

አርቲፊሻል ያንቺ ማንነት አይደለም።


➝አላህ በሰጣችሁ ጸጉር ባለመብቃቃት በአርቲፊሻል ጸጉር/ በሌላ ሰው ጸጉር ለመዋብ ለምታስቡ ሴቶችና በጸጉር ቤት ተቀጥራችሁ አልያም ባለ ሃብት ሁናችሁ አርቲፊሻልን ጸጉርን የምትቀጥሉ ሴቶችም ሆናችሁ ወንዶች ይህ ከላይ የሰፈረው ሐድስ የሚመለከተው እናንተኑ ነውና ልትቆጠቡ ወደ አላህ ልትመለሱ ይገባችኋል ።
' ➝አይ' አንመለስም ካላችሁ የሚጠብቃችሁ የአላህ እርግማን መሆኑን አበስራችኋለሁ።

https://t.me/joinchat/AAAAAEyk1nbb8W4stY5TSA
70 viewsያ ሌላ ይኸ ሌላ, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 13:33:43 ልብ አድርግልኝ!! እያወራሁ ያለሁት ሃላፊነት የማይሰማው ደዩስ ባል እንደሚያደርገው እንድትሆን አይደለም፡፡ ምን ለበሰች? አይገደውም፡፡ ማን ጋ ዋለች? አይደንቀውም፡፡ የት አመሸች? አይሞቀውም፡፡ ይሄ ደዩስ ነው! ከርፋፋ ነገር፡፡ ደይዩስነት ከእንስሳትም አሳማዎች ጋር ነው በስፋት የሚንፀባረቀው፡፡ የወንድ አልጫ ማለት ይሄ ነው፡፡ እራሱ ኃላፊነቱን ጥሎ ጠፍቶ የሚያጠፋ እንከፍ፡፡ እንጂ ወንድ ማለት “ወጥ ቀጠነ” ብሎ አቧራ የሚያስነሳ፣ ምግብ ላይ የሆነ ጉድፍ አገኘሁ ብሎ አገር የሚበጠብጥ አይደለም፡፡ ቢገባህ ነብዩ ﷺ የቀረበላቸው ምግብ ከተመቻቸው ይበሉታል፡፡ ካልሆነ ግን አቃቂር እያወጡ ነገር አይሰነጥቁም፣ በነገር አይሸነቁጡም፡፡ ታዲያ አርአያህ ማን እንዲሆን ነው የምትፈልገው? ጌታችን (ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልእክተኛ ላይ መልካም ምሳሌ አለላችሁ!!) ይላል፡፡ [አሕዛብ፡ 21]
ወንድሜ የሚስትህን ነውር ለማንም አታውራ፡፡ ማንም ቢሆን የሚስትህን ያክል ቅርብ አይደለም፡፡ አንተን ባል ብላ ለእናት ለአባቷ የማትገልጠውን ገላዋን ላንተ ነፃ አድርጋለች፡፡ ልብስ እንደሆንክላት ልብስህ ሆናልሃለች፡፡ አዎ ሚስትህ ከየትኛውም አልባሳት የበለጠች ምቾትን የምትሰጥህ፣ ነውርህን የምትሸፍንልህ ቆንጆ ልብስህ ናት፡፡ ልብስህን እየገሸለጥክ የራስህን ነውር ባደባባይ አታስጣ፡፡ ሌላው ቀርቶ ብትፈታት እንኳን ነውሯን አትዝራ፡፡ ከሰለፎች አንዱ ከሚስቱ ጋር የሆነ ክፍተት ይኖርበታል፡፡ “ምንድነው ችግሩ?” ቢሉት “እንዴ! እንዴት ብየ የሚስቴን ነውር አወጣለሁ?” አላቸው፡፡ ከሚስቱ ጋር ሲለያይ ጊዜ “እሺ አሁንስ ምን ነበር ችግሯ? ንገረን” አሉት፡፡ “እንዴ! እኔ ምን አግብቶኝ ነው የሌላ ሰው ነውር የማወጣው?” አላቸው፡፡ እኛ ግን አብረንም ሆነን ከሰው ሁሉ ለአካላችን ቅርብ የሆነች ሚስታችንን ነውር የሷን ያክል ለማይቀርበን ምናልባትም ይሄ ነው የሚባል ቅርበት ለሌለን ሰው እንዘከዝካለን፡፡ ከተለያየንማ ጭራሽ የሌለውንም ጭምር እንቀደዳለን፡፡ አንዳንዱማ የራሱን ነውር ለመሸፈን በሌለችበት የሚወነጅል አለ!! አላሁል ሙስተዓን!! ያለባትን ብናወራ ያገጠጠ ሃሜት ነው፣ በህይወት አጋራችን ላይ የሚፈፀም ክህደት!! የሌለባትን ብናወራ አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፣ ድንገት ያስተዋሉ እለት ህሊናን የሚጠዘጥዝ ውርደት!!
ወንድሜ! ካለልህ ለሚስትህ ደግ ሁን፡፡ ባል እንጂ ደባል አትሁን፡፡ ስትመጣ ተፍለቅልቃ በደስታ የምትቀበልህ እንጂ ገና መምጫህ ሲቃረብ ልቧ የሚጨነቅ የሚጠበብ፣ ድምፅህ ሲሰማ አመዷ የሚቦን አታድርጋት፡፡ ከቻልክ በመልካም ተኗኗር፡፡ ካልሆነልህ በመልካም ተለያይ፡፡ አለቀ፡፡ (በመልካም መያዝ፤ ካልሆነ በበጎ መለያየት) ይላል ቁርኣኑ፡፡ [አልበቀራህ፡ 229] አስተውል! ብትለያዩም ሙስሊማ እህትህ እንጂ ጠላትህ አይደለችም፡፡ በተለይ ደግሞ ልጆች ካሏችሁ የግፍ ሰንሰለትህን እያረዘምክ ከጓዳህ ጠላት አታፍራ፡፡ ምንም አይነት ቂምና በቀል አያስፈልግም፡፡ በጣም የሚገርመው በሰላሙ ጊዜ ስንት ህይወት እንዳላሳለፉ፣ ስንት መከራ አብረው እንዳልገፉ፣… እህል ውሃቸው አልቆ መለያየት ሲመጣ ጊዜ ለመስማት የሚሰቀጥጡ፣ ለማየት የሚያንቀጠቅጡ ግፎች ሲፈፀሙ ይታያል፡፡ አንዳንዱ ጨቅላ ልጇን ከላዩዋ ላይ የሚመነጭቅ አለ፡፡ ሌላው ድሮ ያልሰጣትን መህሯን የሚክድ አለ፡፡ ዐጂብ የሆነ መውረድ!! ሌላው ከሷ አልፎ ቤተሰቧን ጭምር አበሳ የሚያሳይ አለ፡፡ ሌላው “እስኪ ከዚህ በኋላ የሚያገባትን አየዋለሁ” አይነት የሚፎክር አለ፡፡ አንዴ ከተለያየ በኋላ ከሚያገባት ሰው ጋር መቀያየም ግፋ ሲልም መደባደብ ምን የሚሉት እብሪት ነው?! ሱብሓነላህ! እስኪ ይህን በጉልበት የሚታሰብበት የጃሂሊያህ ሱና ተመልከቱ፡፡ እስኪ እንዲህ አይነቱን ቂላቂል የራሱ ጠላት ታዘቡ፡፡ ይሄ ድሮም ሲበድል እንደኖረ፣ ሲለያይም በሰላም እንዳልተለያየ በግልፅ እያመላከተ ነው፡፡
እስኪ አሁን ጨቅላ ህፃንን ከእናት እቅፍ በመመንጨቅ የፈታትን ሚስት መበቀል ምን የሚሉት አረመኔነት ነው? አቤት የሰው ልጅ ገልቱነት! አቤት የሰው ልጅ ጭካኔ!! በርግጠኝነት ይህን የሚያደርገው ለልጁ ተቆርቁሮ አይደለም፡፡ ተምሳሌት የሆነ ልዩ የእናትነት ፍቅሯን፣ በርህራሄ የሚንሰፈሰፍ አንጀቷን አይቶ በልጇ የሚበቀል ወንድ ያለጥርጥር ወንዶች በወንድነታቸው እንዲያፍሩ፣ ሴቶች ወንዶችን ጭራቅ አድርገው እንዲስሉ የሚያደርግ ሲበዛ ርካሽ የሆነ ምግባር ነው!!
አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/2008)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
48 viewsያ ሌላ ይኸ ሌላ, 10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 13:33:31 “አዋጅ! በሴቶች ላይ መልካምን ዋሉ አደራ!”
~ ~~~~ ~~~~ ~~~~ ~~~
እርግጥ ነው ትዳር በራሱ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ነገር ግን ትዳር ሃላፊነት በጎደለው መልኩ ባልና ሚስት እንደ አቡሽ እና እንደ ሚጣ የሚነፋረቁበት ወይም የሚቦርቁበት መዋእለ ህፃናት አይደለም፡፡ አዎ በአንድ ጎጆ ውስጥ የሚኖር ሰው ቀርቶ በሆነ አጋጣሚ የተገናኘም ሰው ሊገፋፋና ሊጋጭ ይችላል፡፡ ይሄ በዱንያ ውስጥ ከምንፈተንባቸው ነገሮች አንዱ እንደመሆኑ በጥንቃቄ ልንጓዝ ይገባናል፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
(وَجَعَلۡنَا بَعۡضَكُمۡ لِبَعۡضࣲ فِتۡنَةً أَتَصۡبِرُونَۗ )
“ከፊላችሁንም ለከፊላችሁ ፈተና አድርገናል፡፡ ትታገሳላችሁን?” [አልፉርቃን፡ 20]
በትዳር ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ እጅግ የበዙ ግፎችን ስመለከት እና ስሰማ የራሴ ሁኔታ ያስፈራኛል፡፡ ብዙ ሰው የትዳር ሰሞን “አበድኩልሽ ከነፍኩልሽ” እንዳላለ በእጁ ማስገባቱን ባረጋገጠ ማግስት ነገሮች መቀየር ይጀምራሉ፡፡ እዚህ ግባ በማይባሉ ምክንያቶች “አይንሽን ላፈር” የሚለውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡ አንዳንዱ ለአስቤዛ መቶ ሰጥቶ የሁለት መቶ መስተንግዶ የሚጠብቅ አለ፡፡ ሌላው ለውጭ ሰው ተጨዋች፣ ተግባቢ፣ ሳቂታ፣ ገራገር ነው፡፡ ከቤቱ ሲገባ ግን ልጆቹ “መጣ መጣ” እያሉ በፍርሃት የሚያንሾካሹኩበት፣ ሚስት ካሁን አሁን “ምን ይል ይሆን?” እያለች በስጋት የምትዋጥበት አራስ ነብር ይሆናል፣ ግስላ፡፡ “የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ” ይሏል እንዲህ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ ግን “ከአማኞች ኢማኑ የተሟላው ስነ ምግባሩ ያማረው ነው፡፡ ከናንተ በላጫቻችሁ ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው” ብለው ነበር፡፡ [አሶሒሐህ፡ 284] ሌላው ሚስቱን፣ የልጆቹን እናት ከጭቃ የጠፈጠፋት ይመስል እንዳሰኘው ያደርጋታል፡፡ ከልጆቿ ፊት ያዋርዳታል፡፡ በዚህም ወይ እናት በልጆቿ እንድትናቅ በር ይከፍታል፤ አለያ ደግሞ ከተበዳይ እናታቸው ወግነው አባታቸውን እንደ ጠላት እንዲያዩ ያስገድዳል፡፡
መልእክተኛው ﷺ “በሴቶች ጉዳይ አደራችሁን” ብለው ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] እጅግ ብዙ ወንድ ግን “ሴትና ጫማ ከአልጋ ስር” ነው ፖሊሲው፡፡ ሁሌ እሷን ካላሸማቀቀ፣ ሁሌ እሷን ካላዋረደ ወንድ የሆነ አይመስለውም፡፡ ወንድሜ ከሚስትህ የሆነ የማትወደው ባህሪ ሊኖር ይችላል፡፡ ሰው ነችና ይሄ የሚጠበቅ ነው፡፡ ግን ስላንተስ ማን ያውራ? አንተስ የሚጠላ ጎን አይኖርህምን? ምነውሳ ታዲያ የራስህንም ብታይ? ምነው በጎ ጎኖቿንም ብትመለከት? ምንም ጥሩ ነገር ሳታይባት ነው ለትዳር የመረጥካት? ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ሙእሚን ወንድ አንዷን ሙእሚናህ ሴት (ሚስቱን) አይጥላ፡፡ ከሷ የሆነን ባህሪ ቢጠላ ሌላ የሚወደው አለውና፡፡” [ሙስሊም]
አንተ ያማረህን ከውጭ እየሰለቀጥክ ቤትህን የምትዘነጋ ከሆንክ ማሰቢያ የቀለለህ ገልቱ ነህ!! አንተ “እኔ ነኝ ያለ” እያማረጥክ እየለበስክ ሚስትህን የምትረሳ ከሆንክ ቀላል ነህ፣ ኪሎህ ቢከብድም ዋጋህ የወረደ!! ለመሆኑ ሚስትህን አንተ ካልፈቀድካት ማን ይፍቀዳት? ቤተሰቦቿማ አንተን ሰው ብለው፣ አንተን ባል ብለው አደራ ሰጥተውሃል!! ታዲያ ምነው አደራ በላ ትሆናለህ? አንተ በሚስትህ ላይ የምትሰራውን በእናትህ፣ በእህትህ፣ በሴት ልጅህ ላይ ሲፈፀም ብታየው ያስደስትሃልን? ይሄው ውዱ ነብይ ﷺ “ከምትበሉት አብሏቸው፡፡ ከምትለብሱትም አልብሷቸው፡፡ አትምቷቸውም፡፡ ...” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1861] እስኪ ይህን ሐዲሥ እንደ መነሻ ይዘን እራሳችንን እንፈትሽ፡፡
አንዳንዱ አቅሙ ሳይኖረው ሁለተኛ ያገባና ቤቱን የጦርነት አውድማ ያደርገዋል፡፡ እራሱም ቤተሰቡም የሰቀቀን ህይወት እንዲገፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ሌላው ሁለተኛ ባገባ ማግስት የመጀመሪያዋን ከነመኖሯም ይረሳታል፡፡ ጌታችን (አለማስተካከልንም ከፈራችሁ አንዲትን ብቻ ያዙ…) ሲል ነበር ያዘዘው፡፡ [አኒሳእ፡ 3] እሱ ግን “ትዳር አላት” እንዳይባል እርግፍ አድርጎ ትቷታል፡፡ “ትዳር የላትም” እንዳይባል ኒካሑ እንዳለ ነው፡፡ ((በአየር ላይ) እንደተጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደ ወደዳችኋት) መዘንበልን ሁሉ አትዘንበሉ) ብሎ ነበር ጠቢቡ ጌታ፡፡ [አኒሳእ፡ 129] ልብ በል! ነብዩ ﷺ “ሁለት ሚስት ኖሮት ወደ አንዷ ያጋደለ ሰው ነገ በቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የወደቀ ሆኖ ይመጣል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ መዋሪዲ ዞምኣን፡ 1089] ታዲያ መጨረሻህ ይህ እንዲሆን ነው የምትፈልገው? ወንድሜ የበደልካት ሚስትህን ሞት ሳይቀድምህ በፊት በጊዜ “ዐፍው” አስብላት፡፡ ያለበለዚያ ነብዩ ﷺ እንዳሉት “ግፍ ነገ የቂያማ ቀን የጨለማ ንብርብር ነው፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] በየጓዳው በበዳይ ባሎቻቸው ግፍ ሳቢያ ደም እንባ የሚያነቡትን ሴቶች ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ ወላሂ ወንድነትህን ተጠቅመህ በደካማዋ ሴት ላይ የምትፈፅመው ግፍ እሷ ላይ ከደረሰው የከፋ ያስከፍልሃል፡፡ “የተበዳይን እርግማን ተጠንቀቅ፡፡ በሷና በአላህ መካከል መጋረጃ የለምና!!” ይላሉ ከልብ ወለድ የማይናገሩት ነብይ ﷺ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] የስሙን መጠሪያ የዐይን ማረፊያ ልጆቹን ከሷ አግኝቶ፣ ስሜቱን በሷ ላይ አርክቶ፣ ህይወቱን በሷ ላይ መስርቶ፣ የቤት ጣጣውን ሁሉ ከሷ ላይ ጥሎ፣ … ከዚያም አለጠም ጣፈጠ ያለፈውን ሁሉ በመዘንጋት ምንም ዋጋ እንደ ሌላት ልክ እንደ ቆሻሻ፣ እንደ ቆረቆንዳ መወርወር ምን የሚሉት ኢ-ሰብኣዊነት ነው?! ምን የሚሉትስ ገልቱነት ነው?! በእናትህ፣ በልጅህ፣ በእህትህ ላይ እንዲህ ቢፈፀም ደስ ይልሃልን? አትጠራጠር! የእጅህን ታፍሳለህ! የዘራሃውን ታጭዳለህ! “አልጀዛኡ ሚን ጂንሲል ዐመል” ይላሉ አበው፡፡ “ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው” እንደማለት፡፡
አትዘንጋ!! ልክ አንተ በሚስትህ ላይ ሐቅ እንዳለህ ሁሉ ሚስትህም ባንተ ላይ ሐቅ አላት፡፡ ሃይማኖታችን እንዲህ ነው የሚያዘው፡-
- (وَلَهُنَّ مِثۡلُ ٱلَّذِی عَلَیۡهِنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ)
(ለእነሱም (ለሴቶቹ) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ሃላፊነት) አምሳያ (ሐቅ በባሎቻቸው ላይ) አላቸው፡፡” [አልበቀራህ፡ 228]
- (وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ)
(በመልካም ተኗኗረዋቸው፡፡) [አኒሳእ፡ 19]
- “አዋጅ! ለናንተ በሴቶቻችሁ ላይ ሐቅ አላችሁ፡፡ ለሴቶቻችሁም በናንተ ላይ ሐቅ አላቸው፡፡” [ሶሒሑልጃሚዕ፡ 7880]
- “ለቤተሰብህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ እያንዳንዱን ባለ ሐቅ ሐቁን ስጥ!” [ቡኻሪ]
- “ለሚስትህ ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይልቅ ቂል አትሁን፡፡ ለሚስትህ/ቾህ፣ ለልጆችህ ደግ፣ ምቹ ሁንና ቤትህን ምድራዊ ጀነት አድርገው፡፡ ብቻ አንተ ቻልበት፡፡ ከጅምሩ ሷሊሐዋን ምረጥ፡፡ ወይም ሷሊሐ እንድትሆን ጣር፡፡ ያኔ ገና ስታያት ትረካለህ፡፡ በልጆችህ አስተዳደግ ትረካለህ፡፡ ላንተ ባላት መቆርቆር ትረካለህ፡፡ በጨዋነቷ፣ በቁጥብነቷ ትረካለህ፡፡ ዱንያ ላይ ከዚህ በላይ ምን ድሎት አለ?! ነብዩ ﷺ “ዱንያ መጣቀሚያ ነች፡፡ ከመጣቀሚያዎቿ ሁሉ በላጩ ደግ (ሷሊሐህ) የሆነች ሴት ናት” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
42 viewsያ ሌላ ይኸ ሌላ, 10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-06 14:35:46 “በገንዘቦቻችሁ እና በነፍሶቻችሁ በርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከነዚያም ከናንተ በፊት መፅሀፍን ከተሰጡትና ከነዚያ ከሚያጋሩትም ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡”
አዎ የሚደርስብን የደረሰባቸው ነው፡፡ ካለንበት ለመውጣት የታዘዝንበት ብልሃትም የታዘዙበት ነው፡፡
(وَإِن تَصۡبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ذَ ٰ⁠لِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ)
“ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው” ብሎናል፡፡ [አሊ ዒምራን፡ 186]
ፈተናው ሊከብድ ስቃዩ ሊጨምር ይችላል፡፡ ግና መለኮታዊ አዋጁን እንስማ፡
(أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُوا۟ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا یَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِینَ خَلَوۡا۟ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَاۤءُ وَٱلضَّرَّاۤءُ وَزُلۡزِلُوا۟ حَتَّىٰ یَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَاۤ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِیبࣱ)
“በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእመናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልእክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፣ ተርበደበዱም፡፡ 'ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው' (ተባሉም፡፡)” [አልበቀራ፡ 214]
አዎ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው፡፡ ግና የአላህን ትእዛዝ ማክበር ይጠይቃል፡፡ ፈረጃው ይፈጥን ዘንድ የአላህን ህግጋት እንጠብቅ፡፡ ጌታችን “አላህን ብትረዱ ይረዳችኋል” ይላል፡፡ አላህን መርዳት ማለት ትእዛዙን መጠበቅ እና ክልከላውን መራቅ ነው። ለውጥ ከፈለግን እራሳችንን እንለውጥ፡፡
(إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُغَیِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ یُغَیِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ)
“በርግጥም አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን (ገፅታ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚቀይሩ ድረስ አይለውጥም፡፡) [አረዕድ፡ 11]
“እስከመቼ” አትበለኝ፡፡ “የአላህ ውሳኔ እስከሚመጣ ድረስ” እልሃለሁ፡፡ ለመሆኑ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እስከመቼ ነው ፊርዐውንን የታገሱት? ነብዩ ﷺ እስከመቼ ነው ደናቁራን አጋሪዎችን የታገሱት? ረጋ ብለህ አስተውል፡፡ የያኔው ሰቀቀን ከዛሬ እጥፍ ድርብ የከፋ ሰቀቀን ነው፡፡ የያኔው መፍተሄ የዛሬም መፍተሄ ነው፡፡ ይልቅ እወቅ! “አላህን ጠብቅ ይጠብቅሃል፡፡ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህን ታገኘዋለህ፡፡ ስትለምን አላህን ለምን፡፡ ስትታገዝ በአላህ ታገዝ፡፡ እወቅ! ህዝቦች በሙሉ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ እንጂ አይጠቅሙህም፡፡ በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው እንጂ አይጎዱህም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦቹም ደርቀዋል፡፡” “እወቅ! የሳተህ ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ያገኘህም ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ እወቅ!!! ድል ከትእግስት ጋር ነው። ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው። ከከባድም ነገር ጋር ገር ነገር አለ።” ወሶለላሁ ዐላ ነቢይና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 28/2007)
(ተነካክቶ በድጋሚ የተለጠፈ)
የቴሌግራም አድራሻ፦ https://t.me/IbnuMunewor
45 viewsያ ሌላ ይኸ ሌላ, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-06 14:35:45 የመከራውን ጎርፍ በትእግስት ጀልባ እናቋርጠው!
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~~~ ~ ~ ~
ፈተና የአላህ ሱና ነው። መልኩ ቢለያይም ደረጃው ቢፈራረቅም ማንም የማያመልጥበት የሆነ ወጥመድ። ጌታችን አላህ "ሰዎች አመንን ስላሉ ብቻ ሳይፈተኑ ሊተው ያስባሉን?" ሲል እስትንፋሳችን ዱንያን እስከምትሰናበት ድረስ ከፈተና እንደማናመልጥ እቅጫችንን ነግሮናል። ኧረ እንዲያውም “ከፍርሃትና ከረሃብም በሆነ ነገር፤ ከገንዘቦች፣ ከነፍሶችና ከፍሬዎች በመቀነስም በእርግጥም እንፈትናችኋለን” ሲል አስረግጦ ነግሮናል፡፡ ታዲያ ብልጦቹ ይታገሳሉ፡፡ ሽልማታቸውንም ያፍሳሉ፡፡ ቂሎቹ ደግሞ ይወራጫሉ፣ ምንም ጠብ ላያደርጉ የትእግስትን እድል በማሳለፍ ከሁለት ያጣ ይሆናሉ፡፡
በርግጥ የዋሆች ባያስተውሉትም ፈተና ማለት ቅስማችንን የሚሰብረን ነገር ብቻ አይደለም፡፡ ፈተና ስቃይ እንግልቱ፣ መከራው መአቱ ብቻ ሳይሆን ድሎት ምቾቱም፣ ሁሉም የአላህ ፈተና ነው። ታዲያስ "ከዚያም ከ(ተዋለላችሁ) ፀጋዎች ሁሉ በርግጥም ትጠየቃላችሁ" ማለቱ ምንድን ነው የሚያመላክተን? እንዲያውም ነብዩ ﷺ ከማጣት ይልቅ የማገኘትን ፈተና ሰግተውልናል። ጌታችን በክፉ ከተፈተነው ትእግስትን፤ በበጎ ከተፈተነው ምስጋናን ይጠብቃል። የኛ ነገር ግን ሲበዛ ግራ ነው። ብናገኝ ጥጋባችን መከራ። ብናጣ ምሬታችን ፈተና። ቢደላን ምስጋናውን አናውቅበት፡፡ ቢከፋን ትእግስቱን አንችልበት።
በህይወታችን ላይ የሚያጋጥመን እያንዳንዱ ነገር ቢከፋም ቢለማም ሁሉም ከአላህ ነው። ይሄ ከስድስቱ የኢማን ምሰሶዎች የአንዱ መሰረታዊ መልእክት ነው፣ ቀደር። በቀደር ማመን በመርህ ደረጃ ከማስተጋባት ባለፈ በተጨባጭ በህይወታችን ላይ ልናስገኘው የሚገባ አንኳር የሙእሚን መለያ ነው። በቀደር ማመን አማኞችን ጀግና ያደርጋል። "አላህ ከወሰነው ውጭ ምንም አይደርስብኝም" ብሎ የቂን ብሎ የሚያምን አካል የፍጡራን ሴራ አያሸብረውም። ሞራሉንም አይሰብረውም፡፡ የዘወትር መፈክሩ "አላህ ለኛ የፃፈብን እንጂ ፈፅሞ አያገኘንም" የሚለው መለኮታዊ ቃል ነው። በቀደር ስታምን ሰው ጂኑ ከጥንት እስከ ዛሬ ባንድ አብረው ቢዘምቱ አላህ ከፃፈብህ ውጭ ቅንጣት ታክል ምንም እንደማያደርሱብህ ስለምታምን በፍጡር አትሸበርም፣ ከፍጡር አትከጅልም። በቀደር ስታምን አንዴ በተከሰተ ነገር በከንቱ አትብከነከንም፣ በባዶ አትቆዝምም። የሆነውን ላትቀይር ነገር "እንዲህ አድርጌ ቢሆን ኖሮ" እያልክ የቂል ፀፀት ውስጥ አትገባም። ለምን ቢባል "ቢሆን ኖሮ" ነብዩ ﷺ እንዳሉት “የሸይጧንን ስራ ትከፍታለችና፡፡” አላህ አለምን ከመፍጠሩ ከሃምሳ ሺ አመት በፊት የወሰነውን ውሳኔ በቢሆን ኖሮ አትቀይረውምና ለአላህ እጅ ስጥ። “አላህ ቀደረው፣ የሻውንም ፈፀመ” በል። የሙእሚን መታወቂያው ይሄው ነው፡፡ “የሙእሚን ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉ ለሱ መልካም ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለአማኝ እንጂ ለማንም አይደለም፡፡ (ሙእሚን) አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል ይህ ለሱ መልካም ነገር ነው፡፡ ጎጂ ነገርም ቢያገኘው ይታገሳል ይህም ለሱ መልካም ነገር ነው” ይላሉ ውዱ ﷺ፡፡ [ሙስሊም]
ነብዩ ﷺ የሚወዱትን ነገር ሲመለከቱ "ምስጋና ለአላህ ይሁን በፀጋው በጎ ነገሮች ይፈፀማሉ" ሲሉ "የሚጠሉትን ሲመለከቱ ደግሞ "በማንኛውም ሁኔታ ምስጋና ለአላህ ይሁን" ይሉ ነበር። እኛ ግን በሚደርሱብን ነገሮች ከትእግስት ይልቅ ብስጭትን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ቀንን መራገምን ምርጫችን የምናደርገው ቀላል አይደለንም፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ አላህን እስከማማረር አልፎም እስከመሳደብ የሚደርሱም አሉ፡፡ ሱብሓነላህ! ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እስኪ የነብዩን ﷺ ታሪክ እናስታውስ። ገና በናታቸው መሀፀን ሳሉ አባታቸውን አጡ። ይቺን ምድር ሲቀላቀሉ አባት አልባ የቲም ነበሩ። ገና የልጅነት ጊዜያቸውን ቦርቀው ሳይጨርሱ እናታቸውን አጡ። እዚህ ላይ ወላጅ አልባውን ሙሐመድን ﷺ አስቡ። አስር አመት እንኳ ሳይሞላቸው አሳዳጊ አያታቸውን አጡ። ትዳር ይዘው ሲኖሩ የጠላት ፈተና እጅጉን በከበደበት ጊዜ መከታ የሆነላቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብን እና ብርታት የሆነቻቸውን ውድ ባለቤታቸው ኸዲጃን በሞት አጡ። ከሰባት ልጆቻቸው ውስጥ ስድስቱ እሳቸው በህይወት እያሉ ነው የሞቱባቸው። ምን ያክል የሀዘን መከራ እንደተፈራረቀባቸው ተመልከቱ። ከሶሐቦቻቸውም ውስጥ እነ ሐምዛን፣ ሙስዐብን፣ ጀዕፈርን፣ ዐብደላህ ብኑ ረዋሐን፣ ሰዕድ ብኑ ሙዓዝን፣ ... በስንቱ ሃዘን ተጎድተዋል? እስቲ ለአፍታ መካ ላይ፣ ጧኢፍ ላይ በሙሽሪኮች የደረሰባቸውን አስቡ። ለመቋቋም በሚከብድ ሁኔታ ክብራቸው ተጠልሽቷል። አካላቸው ተደብድቧል። የሸተተ እንግዴ ልጅ ላያቸው ላይ ተጥሎባቸዋል። ድፍን ሃገር አድሞ ከነቤተሰባቸው በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል። ለስደት ሲወጡ የታወጀባቸውን ዘመቻ አስታውሱ። መዲና ላይ በሙናፊቆችና በየሁዶች፣ የኡሑድ ዘመቻ ላይ ጥርሳቸው መሰበሩን፣ እራሳቸው መድማቱን እናስታውስ እስኪ፡፡ አለም ከተፈጠረች ጀምሮ ካለፉ ፍጡሮች ሁሉ የምርጦች ሁሉ ምርጥ፣ የታላቆች ሁሉ ታላቅ ከመሆናቸው ጋር፣ ከአላህ ዘንድ ከየትኛውም ፍጡር በተለየና በበለጠ የተወደዱ ከመሆናቸው ጋር ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ አስተናግደዋል። ደረጃችንን ከደረጃቸው ፈተናችንን ከፈተናቸው ጋር እናነፃፀር እስቲ! እዚህ ግባ የሚባል ደረጃ አለን? ከዚህ ሁሉ ፈተና አንፃር የኛ ፈተና ምን አለው ወገኖቼ?
ወገኔ ሆይ! ምንም ቢደርስ ታገስ! እርግጠኛ ሁን በትእግስት ምንም የምታጣው ነገር የለም፡፡ እንዲያውም ትእግስቱን ከቻልክበት ካሰብከው ትደርሳለህ፡፡ ያለምከውን ታሳካለህ፡፡ ድል ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስ፡፡ “እወቅ ድል ከትእግስት ጋር ነው” ብለውሃል ነብዩ ﷺ፡፡ እርዳታ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስና ወደ ጌታህ ተመለስ፡፡
(وَٱسۡتَعِینُوا۟ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ)
“በትእግስትና በሶላት ታገዙ” እያለ ነው ጌታህ፡፡ [አልበቀራህ፡ 45]
ካለህበት ጭንቅ መውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስ፡፡ ይበልጥ በተጨነቅክ ቁጥር ይበልጥ ፍጡርን እየተወክ ይበልጥ በጌታህ ላይ ተስፋህን እየጣልክ ትመጣለህ፡፡ ያኔ እፎይታን ታገኛለህ፡፡ “እፎይታ ወይም ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው” ይላሉ መልእክተኛው ﷺ፡፡ ታገስ! በትእግስት የጠላት ውስብስብ ሴራዎች ይበጣጠሳሉ፡፡ ታገስ! በትእግስት እብሪተኛ አንባገነኖች ይፈራርሳሉ፡፡ ታገስ! በትእግስት ደካሞች ድሎትን ይጎናፀፋሉ፡፡ ወገኔ ሆይ እወቅ! በፈተና እኛ የመጀመሪያዎች አይደለንም፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀዋል፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ አይናቸው እያየ ከሚንቀለቀል እሳት ውስጥ ተማግደዋል፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ ከፈላ ዘይት ውስጥ ተነክረዋል፡፡ ቀደምቶች ነፍሳቸው እያለ በስለት ተዘልዝለዋል፣ ተመትረዋል፡፡ ቆስለዋል ደምተዋል፡፡ ይሄ ወደፊትም የማይቋረጥ የጌታችን ሱና ነው፡፡ ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
(لَتُبۡلَوُنَّ فِیۤ أَمۡوَ ٰ⁠لِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ وَلَتَسۡمَعُنَّ مِنَ ٱلَّذِینَ أُوتُوا۟ ٱلۡكِتَـٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَمِنَ ٱلَّذِینَ أَشۡرَكُوۤا۟ أَذࣰى كَثِیرࣰاۚ)
39 viewsያ ሌላ ይኸ ሌላ, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ