Get Mystery Box with random crypto!

“በገንዘቦቻችሁ እና በነፍሶቻችሁ በርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከነዚያም ከናንተ በፊት መፅሀፍን ከተሰጡት | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

“በገንዘቦቻችሁ እና በነፍሶቻችሁ በርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከነዚያም ከናንተ በፊት መፅሀፍን ከተሰጡትና ከነዚያ ከሚያጋሩትም ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡”
አዎ የሚደርስብን የደረሰባቸው ነው፡፡ ካለንበት ለመውጣት የታዘዝንበት ብልሃትም የታዘዙበት ነው፡፡
(وَإِن تَصۡبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ذَ ٰ⁠لِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ)
“ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው” ብሎናል፡፡ [አሊ ዒምራን፡ 186]
ፈተናው ሊከብድ ስቃዩ ሊጨምር ይችላል፡፡ ግና መለኮታዊ አዋጁን እንስማ፡
(أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُوا۟ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا یَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِینَ خَلَوۡا۟ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَاۤءُ وَٱلضَّرَّاۤءُ وَزُلۡزِلُوا۟ حَتَّىٰ یَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَاۤ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِیبࣱ)
“በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእመናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልእክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፣ ተርበደበዱም፡፡ 'ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው' (ተባሉም፡፡)” [አልበቀራ፡ 214]
አዎ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው፡፡ ግና የአላህን ትእዛዝ ማክበር ይጠይቃል፡፡ ፈረጃው ይፈጥን ዘንድ የአላህን ህግጋት እንጠብቅ፡፡ ጌታችን “አላህን ብትረዱ ይረዳችኋል” ይላል፡፡ አላህን መርዳት ማለት ትእዛዙን መጠበቅ እና ክልከላውን መራቅ ነው። ለውጥ ከፈለግን እራሳችንን እንለውጥ፡፡
(إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُغَیِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ یُغَیِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ)
“በርግጥም አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን (ገፅታ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚቀይሩ ድረስ አይለውጥም፡፡) [አረዕድ፡ 11]
“እስከመቼ” አትበለኝ፡፡ “የአላህ ውሳኔ እስከሚመጣ ድረስ” እልሃለሁ፡፡ ለመሆኑ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እስከመቼ ነው ፊርዐውንን የታገሱት? ነብዩ ﷺ እስከመቼ ነው ደናቁራን አጋሪዎችን የታገሱት? ረጋ ብለህ አስተውል፡፡ የያኔው ሰቀቀን ከዛሬ እጥፍ ድርብ የከፋ ሰቀቀን ነው፡፡ የያኔው መፍተሄ የዛሬም መፍተሄ ነው፡፡ ይልቅ እወቅ! “አላህን ጠብቅ ይጠብቅሃል፡፡ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህን ታገኘዋለህ፡፡ ስትለምን አላህን ለምን፡፡ ስትታገዝ በአላህ ታገዝ፡፡ እወቅ! ህዝቦች በሙሉ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ እንጂ አይጠቅሙህም፡፡ በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው እንጂ አይጎዱህም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦቹም ደርቀዋል፡፡” “እወቅ! የሳተህ ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ያገኘህም ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ እወቅ!!! ድል ከትእግስት ጋር ነው። ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው። ከከባድም ነገር ጋር ገር ነገር አለ።” ወሶለላሁ ዐላ ነቢይና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 28/2007)
(ተነካክቶ በድጋሚ የተለጠፈ)
የቴሌግራም አድራሻ፦ https://t.me/IbnuMunewor