Get Mystery Box with random crypto!

በሌላ አባት ወይም በሌላ ዘር መጠራት ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ በሃገራችን በተለያዩ መነሻዎ | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

በሌላ አባት ወይም በሌላ ዘር መጠራት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በሃገራችን በተለያዩ መነሻዎች ያለ አባታቸው የሚጠሩ ሰዎች አሉ። ለምሳሌ ወላጆች በግጭት ሲለያዩ ልጅ ካላቸው ልጁን የሚያሳድጉ ሰዎች ለአባቱ ባላቸው ጥላቻ የተነሳ በራሳቸው ቤተሰብ ስም ሲጠሩ ያጋጥማሉ።
ልክ እንዲሁ ያለ ዘራቸው በሌላ ዘር ወይም በሌላ ብሄር እራሳቸውን የሚገልፁም በጣም ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ዐረብ ሳይሆኑ ዐረብነትን የሚሞግቱ ቁጥር ስፍር የላቸውም። ልክ አይሁድ ሳይሆኑ "አይሁድ ነን"፣ "የሰለሞን ዘር ነን" እንደሚሉት።
ሃገር ውስጥ ካሉ ብሄሮች ሆነውም ብሄራቸውን ደብቀው ያልሆኑትን በሌላ ብሄር የሚጠሩና የሚታወቁም በጣም ብዙ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በማስተባበልም ሆነ በማስጠጋት ቢፈፀሙ ከባድ ጥፋቶች ናቸው።
★ በማስተባበል ማለት: – የራሱን መካድ፣ መደበቅ፣ የሆነውን እንዳልሆነ መሞገት፣ አባቱን፣ ዘሩን፣ ብሄሩን መካድ፣ ማስተባበል።
★ በማስጠጋት ማለት:– እራሱን በሃሰት ወደሌላ ሰው፣ ወደሌላ ዘር፣ ወደሌላ ብሄር ማስጠጋት፣ በሃሰት በሌላ መግለፅ።
በሁለቱም በኩል ቢፈፀም ከከባባድ ጥፋቶች (ከከባኢር) ነው። ቀድሞ ባለማወቅ ተፈፅሞ ከሆነ ስህተቱን ወይም ችግሩን የተረዳ ሰው ሊያስተካክል ይገባል።
ከአቡ ዘር ረዲየሏ፞ሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

"لَيْسَ مِنْ رَجُلٍ ادَّعَى لِغَيْرِ أَبِيهِ، وَهُوَ يَعْلَمُهُ، إِلَّا كَفَرَ. وَمَنِ ادَّعَى قَوْمًا لَيْسَ لَهُ فِيهِمْ فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ".
"እያወቀ ያለ አባቱ ሌላን የሚሞግት (በሌላ የሚጠራ) ሰው አይኖርም፣ የካደ ቢሆንጂ።
ከነሱ ሳይሆን ወደሆኑ ወገኖች እራሱን በማስጠጋት የሞገተ መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

በተጨማሪም ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"إِنَّ مِنْ أَعْظَمِ الْفِرَى أَنْ يَدَّعِيَ الرَّجُلُ إِلَى غَيْرِ أَبِيهِ".
"ከከባባድ ቅጥፈቶች ውስጥ አንዱ አንድ ሰው አባቱ ወዳልሆነ ሰው መሞገቱ (እራሱን ማስጠጋቱ) ነው።" [ቡኻሪ: 3509]

"مَنِ ادَّعَى إِلَى غَيْرِ أَبِيهِ، وَهُوَ يَعْلَمُ فَالْجَنَّةُ عَلَيْهِ حَرَامٌ ".
"እያወቀ ከአባቱ ውጭ ወደሌላ ሰው የሞገተ ሰው ጀነት በሱ ላይ እርም ነች!!" [ቡኻሪና ሙስሊም]

የቴሌግራም አድራሻ:-
https://t.me/IbnuMunewor