Get Mystery Box with random crypto!

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የሰርጥ አድራሻ: @seanlph
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-29 14:49:04
" ለምን ይመስልሀል "
ችላ እንዳልካት በድርጊቶችህ ደጋግመህ እያሳየሀት ፣ አብዝተህ ስሜቷን እየጎዳኸዉ እንደሆነ ልቦናዋ እያወቀ እንኳ ዛሬም ጎንህ ያለችው ፣ ያንተን ነገር ከውስጧ ለማጥፍት አቅም ያጣችው ፣ አንተን ከመርሳት ይልቅ ማስታወሱ የሚቀላት ፣ አንተን እርግፍ አድርጋ ትታ ከሌላ ሰው ጋር ሂዎትን ማሰብ ገደል መስሎ የሚታያት ፣ያን ሁሉ ነገር እያደረካት እንኳ ስምህን በክፉ ለማንሳት የማትደፍረው አንተ ማንም ስለሆንክ አልያም ከሌላው ወንድ የተለየ ነገር ኖሮህ አይደለም እውነታው እሷ የምር ከልቧ አፍቃሪ ሴት ስለሆነች ነው ።
አየህ የዚች አይነት አፍቃሪ ሴት ስትወድ በሙሉ ልቧ ስለሆነ ዛሬን ብቻ ሳይሆን እሩቅ ነው ህልሟ፣ ግዙፍ ነው ምኞቷ በዛም ምክኒያት ሁሉነገሯን ለአብሮነቱ ሳትሰስት ስለምትሰጥ አየተበደለችም ፍቅሯን በቀላሉ ከደሟ ውስጥ ቶሎ ማውጣቱ አይቻላትም ...የኖረችው ትዝታም እንዲህ በቀላሉ በአእምሮዋ መመላለሱን አያቆምም አየህ በቃ ለዛ ነው ከድግምግም ጥፋትህ ይልቅ ትንሽየዋ መልካም ነገርህ ለአይኗ የሚጎላው በተሳሳተ ሚዛን እራስህን እየመዘንክ አጉል አትቆለል ያቺ ሴት እንዲህ የመሆኗ ሚስጥር አንተ ትክክለኛ ሰው ሁነህ ሳይሆን እሷ ወረትን የማታውቅ ትክክለኛና ልባም አፍቃሪ ሴት ስለሆነች ብቻና ብቻ ነው
" ይልቅ ሳይረፍድ አትነቃም ወይ"
#ሼን
132 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:48:33
አንዳንድ ሴት የምታወራትን ቶሎ የማትቀበልህ በተፈጥሮዋ ተጠራጣሪ ሁና አይደለም ትናንት ያረፈበት የክህደት ብትር ዛሬም ድረስ ጠባሳው ከልቧ ላይ ስላለ ነው
አንዳንድ ሴት አብሮነትን ፡መቃረብን የምትሸሸው አንተ እንደምታስበው ጉረኛ ሁና አይደለም ተላምዶ መለያየትን አብዝታ ስለምትፈራ ነው እሷ ያለፈችበትን ትናንትና በውል አታውቅምና በዛሬዋ ልትፈርድባት አትቸኩል ይልቅ ከቻልክ ህመሟን አብረህ አስታምና የድሮ ጠባሳዋን ፍቃ አዲስ ሴት ትሆን ዘንድ እገዛት
#እኔ_ሴቶችን_እወዳቸዋለሁ
#ሼን
133 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:48:06
" ዋጋህን እወቅ "
የቱንም ያክል ከነሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስታ ቢሰጥህም እነሱ ካንሀ ጋር መሆኑ ምቾት የሚነሳቸው ከሆነ አታግኛቸው
የቱንም ያክል ድምፃቸውን መስማት ቢያጓጓህም እነሱ ሊያወሩህ ካልፈለጉ አትደውልላቸው
የቱንም ያክል ብትወዳቸውም በነሱ ያለመፈለግ ስሜት ከተሰማህ ግን ተዋቸው
የቱንም ያክል ለነሱ የገዘፈ ቦታ ቢኖርህም የማያከብሩህ ከሆነ ፣ለስሜትህ የማይጨነቁ ከሆነ የሚንቁህ ከሆነ ተዋቸው
136 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:47:40
አንዳንዴ ......
የራስህ ልታደርጋቸው በብዙው ከጣርክላቸው፣ ዕልፍ ጊዜ ከደከምክላቸው ፣ራስህን አሳልፈህ ከሰጠሀቸው አንዳንድ ሰዎች በተሻለ መልኩ ድንገት በሆነ አጋጣሚ ምንም ሳትጠብቀው ወደ ህይወትህ ብቅ የሚሉ ሰዎች የ "ሰውነትን " ትርጉም ኑረው ያሳዩሀል፣ ልባዊ መውደድንና የማይዛነፋ መልካምነትን ፣ ምላሽ ሳያሰሉ ያለወረት ማፍቀርን በውስጥህ ዘርተው ጠወለገ ያልከውን ህይወትህን ዳግም ያለመልሙልሀል
#ሼን
152 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:47:12
አየሽ አይደል እኔ
ትናንት
መለየትን ማሰብ _ መሮሽ ሁኖ እንዳሞት
ያለነሱ መኖር _ ሁኖብሽ የቁም ሞት
ከጎንሽ ከሌሉ _ ቀኑ የሚጨልም
እቅድና ተስፋሽ _ የሚተን እንደጉም
በሂወት መቆምሽ _ የሚያጣብሽ ትርጉም
የመሰለሽ ትናንት_ ሳለሽ ባብሮነቱ
ይሄውና አሁን _ ሌላ ነው እውነቱ
እነሱ ባይኖሩም _ ቢሄዱም እርቀው
እንባ ቢያስነቡሽም _ ያን ሳቅሽን ሰርቀው
ሁለተኛ አልቆምም _ አልሺርም እስክትይ
ብዙ ብትደሚም _ ብትገፊም ስቃይ
ቀን በቀን ሲተካ _ ወቅት ነግቶ ሲመሽ
ቀስ ቀስ እያለ _ ያንቺም ህመም ሲሸሽ
ከመቆየት ብዛት _ ቁስልም ተወግዶ
ሰነባብቶ ከርሞ _ ጎንሽም ሰው ለምዶ
ዛሬ እየኖርሽ ነው _ አለሽ ያው እንደቆምሽ
በተሻለ ተስፋ _ ነገሽን እያለምሽ
ለካ .....
ሰው ተለየኝ ብሎ _ ከመኖር መቆሙ
ሞኝነት ብቻ ነው _ ሲፈታ ትርጉሙ
#ሼን
165 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:46:37
" አዎን አንቺ "
ታውቂያለሽ ..... ወደ ሂወትሽ እየገቡ የሚወጡት ሰዎች ብዙ አስተማሩሽ መሰል የሚያስታውቅ የባህሪ ለውጥ እያየሁብሽ ነው በትንሽ ትልቁ መናደድ ትተሻል ፣ለራስሽ ጊዜ እየሰጠሽ ነው ፣ ሳቅና ደስታሽን ከሌላ መጠበቅን አቁመሻል ፣ የኔ የምትያቸውን ሰዎች ማኩረፍ አቁመሻል ፣ ነገሮችን ችላ ብሎ ማሳለፍ፣ ሰዎችን ሲሄዱ መሸኘትና ሲመጡ መቀበል ጀምረሻል ማንንም ለምን እንዴት ብለሽ መጠየቅም ትተሻል ፣ ላንቺው አንቺው መቆም እንዳለብሽ በደንብ ገብቶሻል .... ልክ ነኝ አይደል
178 views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 15:43:57 #አንተ_በሂወት_እያለህ_አባትህ_የሚለብሰው_ቸግሮት_ሲበርደው_ብታይ_ምን_ታደርጋለህ
ከጧቱ 4: 00 ሰአት አከባቢ ዝናብ እያካፋ ነው  ከጓደኛዬ  ጋር ከአንድ መንገድ ዳር ካለ የጀበና ቡና መሸጫ ቦታ ተቀምጠን ቡና እየጠጣን ነው ።ቦታው ላይ ሌሎች ሰዎችም እንደኛ ለቡና ተቀምጠዋል ድንገት አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ወደኛ ጠጋ ብለው እጃቸውን ለምፅዋት  ዘረጉ በዛ ካፊያና ብርድ የለበሱት
ቁራጭ ልብስ እንኳን ከብርዱ ሊያድናቸው ይቅርና ሰውነታቸውን እንኳ በቅጡ አይሸፍንም ፋዘር ቡና ይጠጣሉ ብለን ጠየቅናቸው እሳቸውም መጠጣት እንደሚፈልጉ አሳውቀዉን ወንበር ስበንላቸው ጎናችን ኩርምት ብለው ተቀመጡ ...ለቡና ቀጂዋ እንድትቀዳላቸው አዘናት ወደራሳችን ጨዋታ ተመልሰናል በዚህ መሀል ነበር ታዲያ  "የኔ ልጅ" የሚለው የአዛውንቱ ድምፅ በወሬያችን መሀል የገባው እኔና ጓደኛዬን ጨምሮ  ከኛ ትይዩ የተቀመጠ አንድ ወጣት ልጅ እኩል ወደሰውየው ፊታችንን አዞርን ከሶስታችንም ለሰውየው ቅርብ የነበርኩት እኔ ነበርኩና እይታቸውን እኔ ላይ አድርገው "እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ" አሉኝ  እኔም እሺ ፍዘር ጠይቁኝ ምንድን ነው  አልኳቸው ለመስማት እየተጣደፍኩ እንደው እዚች ምድር ላይ ከሁሉ  አብልጠህ የምትወደው ማንን ነው  አሉኝ ?
እኔም ምድር ላይ ከሁሉ አብልጬ የምወደው ሰው አባቴ እንደሆነ መለስኩላቸው ፡ አስከትለው እንዲያ የምትወደው አባትህ አንተ በሂወት እያለህ የሚለብሰው አጥቶ ሲበርደው ብታይ ምን ታደርጋለህ አሉኝ በሰአቱ ጥያቄው አስደንግጦኝ ነበር... እኔ እርቃኔንም ቢሆን እሄዳለሁ እንጂ አባቴንማ እንደዛ ሁኖ ማየት አልፈልግም  ስል መልስ ሰጠዃቸው አተኩረው እያዩኝ አየህ እኔ እንዲህ የሚለኝ ልጅ የለኝም ግን "በርዶኛል" አሉኝ ሰውነቴን ውርር ነበር ያደረገኝ አስቡት በዛ አይነት ሁኔታ  እንደዛ ብትባሉ ሊሰማችሁ የሚችለውን ስሜት በጣም ልብ ይነካል .... ወዲያው ግን ደስ የሚል አጋጣሚ ተፈጠረ እዛው ከኛ ጎን ለቡና ተቀምጦ የሰውየውን ንግግር እየሰማ የነበረ አንድ ወጣት አባቱ ካረፉ ስድስት ወራት እንዳለፋቸውና የአባቱ ብዙ አልባሳት ስላለ ለአዛውንቱ ሊሰጣቸው እንደሚችል አበሰረን  በሀዘን ክስም ያለው ፊቴ  በወጣቱ ልጅ ሀሳብ ፍክት አለ
ወዲያው ራይድ ጠርተን አዛውንቱን ይዘን ወደልጁ ቤት አመራን ፡ ከቆይታ በዃላ ከወጣቱ ቤት ደርሰን  ካፖርትና ሱፍን ጨምሮ ሌሎች ብዙ አልባሳትን አውጥቶ  ሰጣቸው
በሰአቱ አዛውንቱ ፊት ላይ ያስተዋልኩትን ፈገግታ እንዲህ ብሎ በቃላት ለማስቀመጥ ይቸግራል የምርቃት አይነት አዘነቡብን በመጨረሻም በደስታ ወሬ የታጀበ ምሳ አብረን በልተን ተለያየን ።  እኔ ግን ከአዛውንቱ ጋር ከተለያየን በዃላ አንድ ንግግራቸው  ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ  "ፈጣሪ እናንተን ባይጥልልኝ ኖሮ የጥቅምትን ብርድ እንዴት እችለው ነበር "
የአዛውንቱ አይነት  ልብስ የሚያስፈልጋቸው ስንት ችግረኞች በየቦታው ይኖሩ ይሆን ስል አሰብኩኝ በዛ ላይ በዚህ የብርድ ወቅት
በዛው ቅፅበት አንድን ሀሳብ አሰብኩኝ  ሁላችንምኮ ረዝሞን ወይ አጥሮን አልያም ፋሽኑ አልፎበታል ብለን የማንለብሰው እንዲሁ የተቀመጠ አልባሳት በየቤታችን አለን  ለምን እኒያን አልባሳት ሰብስበን ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች አናለብሳቸውም ይህን ሀሳብ የዛኑ ቀን ማታ ላይ የአዛውንቱን ገጠመኝ ጠቅሼ አዲስ አበባ ላይ ይህን ስራ አብረን እንስራው ስል ቲክቶክ ላይ ቪዲዮ ሰርቼ ለቀኩኝ ። የሰራሁት ቪዲዬ ላይ ስልክ አስቀምጬ ስለነበር ብዙ ሰዎች እየደወሉ አብረውኝ ሊሰሩ ፍቃጀኛ እንደሆኑ አሳወቁኝ አንዳንዶች ደግሞ አልባሳቶችን ያለንበት ድረስ እያመጡልን በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን
ይህን ፅሁፍ ያነበባችሁ አዲስ አበባ የምትኖሩ በዚህ ስራ ላይ አብራችሁን ለመስራት ከፈለጋችሁ አልያም አልባሳትን ለመስጠት የምትፈልጉ ከስር ባለው ስልክ ቁጥር  ልትደውሉልን ትችላላችሁ
09 39 00 64  88
#ለእኛ_ትርፍ_የሆነው_ለሌሎች_ዋናቸው_ነው
2.6K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 15:43:53
2.3K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:26:04
አዲስ አበባ ያላችሁ ይህን ቪዲዮ ትሰሙት ዘንድ በፈጣሪ ስም አጥብቄ እጠይቃችዃለሁ ከሰማችሁት በዃላ በዚህ ስራ አብራችሁ መስራት የምትፈልጉ 0939006488 ላይ ደውላችሁ አሳውቁኝ
2.8K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 21:23:36
2.8K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ