Get Mystery Box with random crypto!

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የሰርጥ አድራሻ: @seanlph
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-08-03 16:49:15 ሰላም የፍቅር ዳማከሴ እስኪ ሀሳባችሁን አካፍሉኝ በጣም የምወደው ፍቅረኛ አለኝ እሱም በጣም ይወደኛል እኔ ግን በጣም እቀናለሁ የብቻዬ እንዲሆን ነው እምፈልገው እንኩአን በሴት በወንድ ጓደኞቹ እቀናለው አብዛኛውን ግዜ ለኔ ነው እሚሰጠኝ ግን እነሱ ጋር ነኝ ካለኝ በጣም ይከፋኛል ብቸኝነት ይሰማኛል እኔ ሌላ ጓደኛ የለኝም ሂወቴ ውስጥ ያለው እንዲኖርም እምፈልገውም እሱን ነው ስራ ከዛ እኔ እንዲ እንዲሆን ነው እምፈልገው ከዚ በፊት ሴት ጓደኞቹ ምሳ ያመጡለታል ተደጋጋሚ ይደውሉለታል ሌላ ነገር እንዳላስብ አብሬያቸው እሆናለው ደግሞም ያገቡ እና ፍቅረኛ ያላቸው ናቸው ቢሆንም ግን በስንት ክርክር አስተውኳቸው ይበልጥ ይሄ ስሜት እንዲሰማኝ ያደረጉት ደሞ እነሱም ስለማይወዱኝ ነዉ እሚያሳዩኝ ነገር ደስ አይለኝም ከእሷ ጋር ነኝ ካላቸው ይደብራቸዋል እሱን ግን በጣም ይወዱታል አብሬያቸው ስሆን እንጠጣ እናምሽ ሲሉ እሺ አልልም እና ደግሞ አብረን ሆነን እሚያወሩትንም አንሰማም በራሳችን መንገድ ነው እምንሆነው እሱን እሚወዱት አይመስለኝም አሁን ላይ ደግሞ አብሬያቸውም ብሆን እሚያሳዩኝ ፊት ደስ አይለኝም ምን ላድርግ ግራ ገባኝ እኔም እነሱም አንፈላለግም
4.0K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 16:32:04 https://vm.tiktok.com/ZMNb1hjyk/?k=1
3.7K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 16:24:45
1.4K views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 18:59:30 https://www.tiktok.com/@shenpoems/video/7120999848270220549?_r=1&u_code=e05jm13b8ea273&preview_pb=0&language=en&_d=e08kb64lda0ka4&share_item_id=7120999848270220549&source=h5_m&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7115653163968907014&share_link_id=c68fa9f4-efbd-4eb1-a9c5-1b3b31897ac4&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
1.8K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:17:33
"እናትም አባትም"
ልብ ታድለሀል የናትም ያባትም
አንተን የመሰለ ለኔ የለም የትም
ማድ ባይቀርብ እንኳ ባይከፈት ሞሰብ
ፈገግ ካልክ አንተ ይበቃል ለመጥገብ
አንተ የኔ ባትሆን በደም ባንጣመር
ልጅህ በሆነው ሰው እቀናበት ነበር
.. ለምን ይመስልሀል..
የማይዘመረው ስምህ ገኖ እንደናት
ከቃል ልቆኮ ነው የመውደደህ ፅናት
#አባትነት
#ሼን
2.1K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:16:33
"ይቆጭሀል ሸጋው"
መለየት ካማረህ ..
አብሮነቱን ንደህ..
መሄዱን ሂድ ዛሬ ..
ግን ልንገርህ ፍቅሬ ..
ስትንቃት አክብራ ጠልተሀት የምቶድ
ስትርቃት የምትቀርብ ገፍተሀት የማቴድ
አንተው ባጠፋኸው እሷ ምታባብል
እንከንህን ችላ እንኑር የምትል
ደከመኝ የማታውቅ ሳቅህን ለመፍጠር
እራሷን የጣለች አንተን ለማጠንከር
ፈልገህ ስታጣ የመሰለች እኔን
ዳግም ትሽዋለህ የተውከውን ጎኔን
አዎን ያንን ጊዜ
ሰስላንተ የሆንኩት የገባህ ለት ዋጋው
በእርግጥ ልማልልህ ይቆጭሀል ሸጋው
#ሼን
2.0K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:15:08
"አንቺ የደሴ ልጅ"
አንቺ የደሴ ልጅ የወሎዋ ሸጋ
እሺ በይ ቅጠሪኝ ልቤ ይረጋጋ
ይሁን እንዴ ሰኞ ፣ ወይስ ባድራ ግቢ
ሳላይሽ ይሻላል ፣ ወይ መርሆ ግቢ
ንገሪኝ አለሜ የት እንቀጣጠር ?
ዲቪዥን ላይ ይሁን ፣ ከፍ ብሎ ሸዋበር
አይ ካልሽም አራዳ ፣ አለ ሸርፍ ተራ
እዛም ካልተመቸሽ ፣ እናድርገው ሙጋድ
የት ነው የምትቀጥሪኝ አንቺ የልቤ ጋርድ ?
ፒያሳም ካልሽ እንዳሻሽ ፣ወይ መንበረ ፀሀይ
ሜጠሮ ኡራኤል ፣ የት ጋር እንተያይ
አረብ ገንዳ ይሁን ፣ ታቹን ጮርቃ መንደር
ንገሪኝ ዉዴዋ ፣ ቄራም ካልሽ ልንደርደር
እዛም ካልተመቸሽ ፣ጠጋ ልበል ሆጤ
ብቻ አንቺ ቅጠሪኝ ፣ደስ ይበለው ውስጤ
አገር ግዛት ልምጣ ፣ካልቻልሽ መላኩ
አሬራም አይርቀኝ፣ ይመቸኛል ተቋም
የት ጋር ተገናኝተን ፣ እንባባል ሰላም
ቢዘንብም ቅጠሪኝ፣ አልፈራም በረዶ
ላዩን መድሀኒያለም፣ መናፈሻ ዳውዶ
አንቺ የትም ብትይ፣ ሮቢት ጎንደር በር
አፍታም አላረፍድም፣ እመጣለሁ ስበር
ይህም አይሆንም ካልሽ ፣ላቅና ሳማ ሰፈር
ተራብኩሽ ናፈኩሽ ፣እንደ'ህል እንደ'ውሀ
በቃ አይንሽን ልየው፣ ዶልፊን ወይ ቧንቧሀ
ግብርናና ኬላም ፣ ና በዪኝ አልደክምም
የትም ይሁን ዉዴ ፣ ቅጠሪኝ አልቀርም
ማሪያም ከፍ ልበል ፣ ልውረድ ሳጥን ተራ
አይጠየፍ ግድም ፣ ወይ መንገሻ ጎራ
የት ጋር ይመችሻል ፣ ገብሬል ካራጉቱ
ወይስ እራስ አገዝ ፣ ንገሪኝ ሸጊቱ
ሼል መናሀሪያ ፣ ካልሆን መናፈሻ
የት ጋር ይመችሻል፣ ንገሪኝ አድራሻ
አንቺ የደሴ ልጅ እሺ በይ ቅጠሪኝ
ለናፍቆትሽ ህመም ስጪኝ ማስታገሻ
#ሼን
____
የደሴ ልጆች ግጥሙ ውስጥ ያልተጠቀሱ የሰፈር ስሞችን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ
@seanlph
2.0K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:27:53 በአሁኑ ሰአት አርባ ምንጭ የምትኖሩ ካላችሁ እስኪ @gitmsetim ላይ አሳውቁኝ ፈልጊያችሁ ነው
3.9K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:27:09 https://vm.tiktok.com/ZMND9aCCP/?k=1
3.8K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:16:46 እሺ የፍቅር ዳማከሴ ዛሬ ደሞ በኔ የፍቅር ታሪክ ዙሪያ ሀሳብ ስጡኝ ፣ ልጁን ያወኩት ከ 5 አመት በፊት ነበረ ልክ እንዳየሁት ነበረ የወደድኩት ከጊዜ ወደጊዜ አፈቀርኩት። አብረን መሆን እንደማንችል አዉቃለሁ በሱ በጣም ተጎድቻለሁ ብዙ ነገርም ሆኛለሁ። ብዙ ጊዜ እራሴን ለማጥፋትም ሞክሪያለሁ ያለሱ ህይወት የሚኖረኝ አይመስለኝም ነበረ።እና ደሞ በቃ እሱን ለመርሳትም ሌሎች r/ship ጀምሬ ነበር ግን ትርፉ መጎዳዳት ነበር። ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ደህና በመሆኑ ደስተኛ ነበርኩኝ አሁን ግን ደህና አይደለም ሱሰኛ ሆኗል almost 2 አመት ይሆነዋል ከጀመረ አብረውት የጀመሩት ጓደኞቹ እንኳን ሲሻሻሉ እሱ ግን ባሰበት መዉጫዉ ጠፋው።ያ ውበቱ ዛሬ እረግፏል አይኑ ጥርሱ ከንፈሩ ኡፍፍፍ ብቻ ግን እንዴት ልረዳው የሱስ ነገር ጭራሽ እንዲነሳበት አይፈልግም ። አፈቅረዋለሁ ግን ፍላጎቴ አብሮኝ እንዲሆን ሳይሆን ህይወት ኖሮት አላማ ተስፋ ኖሮት ወጣትነቱን ሲያጣጥም ማየት ነው ። ስለሱ ሳስብ ሰላሜን አጣለሁ እባካቹህ እርዱኝ እንዴት ልርዳው??
3.7K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ