Get Mystery Box with random crypto!

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የቴሌግራም ቻናል አርማ seanlph — የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥
የሰርጥ አድራሻ: @seanlph
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.81K
የሰርጥ መግለጫ

በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-29 14:54:38
አንዳንድ ሰው ደህና ነኝ የሚለው የእውነት ደህና ስለሆነ ሳይሆን አሞኛል ቢልም ህመሙን የሚረዳለት ሰው ስለሌለው ነው ..... አንዳንድ ሰው ዝም የሚለው የሚያወራው ስለሌለው ሳይሆን የሚያወራለት ሰው ስላጣ ነው ..... አንዳንድ ሰው ብቸኝነትን የሚመርጠው ሰው ጠፍቶ ሳይሆን ለእርሱ ልክ የሚሆን እርሱን በእርሱነቱ የሚቀበለውና የሚረዳው ሰው ስላጣ ነው ......
100 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:53:49
አልነግርህም እንጂ በከፋህ ሰአትና ባመመህ ጊዜ ለኔ ያድርገው እያልኩ ለሊቱን ሙሉ እፀልይ ነበር .... አልነግርህም እንጂ ጥሩ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ምነው ለእሱ በሆነ ብዬም ደጋግሜ እመኝ ነበር ....አልነግርህም እንጂ እያስለቀስከኝ እንኳ ፊትህ ላይ ሳቅህን ነበር እፈልግ የነበረው .... አልነግርህም እንጂ ማፍቀሬ እንዳነሰብህ በድርጊቶችህ እያሳየኸኝ እንኳ እኔ ግን ስለወደፊታችን አልም ነበር ....
አልነግርህም እንጂ ስትዋሸኝ እውነታውን አውቅ ነበር .... አልነግርህም እንጂ እኔ ላንተ ብዙ ብዙ ነበርኩ .....
#ሼን
99 views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:53:10
" በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ሁሌም ጥፋተኛዋ አንቺ ነሽ "
ጥፋታቸውንና በደላቸውን ሆነ ብለሽ አውቀሽ እንዳላወቀ ስታልፊ ሞኝ አድርገው ያስቡሻል ፣ መሳሳታቸውን ስትነግሪያቸው ደግሞ ተጨቃጫቂ ያደርጉሻል ፣ አብረሻቸው መሆንን በፈለግሽበት ሰአት ቢዚ እንደሆኑ ነግረውሽ ለራስሽ ጊዜ መስጠት ስትጀምሪ ተለውጠሻል ምን አግኝተሽ ነው ይሉሻል፣ አንሱው እንድትርቂ ምክኒያት ሁነው ከአይናቸው ዘወር ስትይ ተውሽን ብለው ሊወቅሱሽ ይዳዳሉ በቃ ምንም አይጨበጡም እነሱው አስለቅሰውሽ እነሱው ካላባበልንሽ ይላሉ እነሱው ሳቅሽን ሰርቀው እነሱው አኩራፊ ይሉሻል ፣ እነሱ ያሻቸውን ተናግረውሽ ቆየት ብለው አፌ ነው እንጂ ሆዴኮ ባዶ ነው ብለው ይሸነግሉሻል አንቺ ተስቶሽ የተናገርሻትን አንድ ቃል ግን ሁሌ እያነሱ ሊያሸማቅቁሽ ይሞክራሉ ..... በቃ በአንዳንዶች ዘንድ አንቺ መቸም ልክ አትሆኚም
#ሼን
99 views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:52:36
"እየነገርኩሽ ነው "
አንዳንዴ ሰዎችን ከሂዎትሽ የምታስወጫቸው ስለማትወጃቸው ብቻ አይደለም የሚገባሽን ቦታና ክብር ሳይሰጡሽ ሲቀሩም ነው አየሽ አብዝተሽ ስለወደድሻቸው ብቻ የትም አትሄድም በሚል የጂል ተረት እንዳሻቸው እየሆኑ ስሜትሽን ሲጎዱትና ክብርሽን ዝቅ ሲያደርጉት ደጋግመሽ እያየሽ አሁንም እዛው ቦታ ላይ መገኜት ትእግስት ሳይሆን "ሞኝነት" ነው ስለዚህ ዋጋሽን ጠንቅቀሽ እወቂ እነሱን ካጣሁ በዃላ ምን እሆናለሁ ከሚል አጉል ፍራቻ ውጪ እነሱን ካጣሽ በዃላ ትክክለኛዋን አንቺን ነው የምታገኚው ...
101 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:52:07
"የዝምታ_ህመም"
ምንም እንዳልሆኑ _ ደህና እየመሰሉ
ውጋትን ደብቀው _ እንዲህ ነኝ ሳይሉ
ዝም ፀጥ ብሎ _ ሁሌ መሰቃዬት
ቀን የይምሰል ስቆ _ ማንባት ጠብቆ ሌት
ከባድ ነው ህመሙ _ ያቅታል ለማንም
ትንሽ ሰው ብቻ ነው _ ለዚህ ያለው አቅም
#ሼን
102 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:51:38
"አንቺ ጀግና ሴት ነሽ"
አንቺ ጀግና ሴት ነሽ _ ፍፁም የበረታሽ
ውስጥሽ ያለን ህመም _ ለብቻሽ የረታሽ
ለሌላ ማይገባ _ ከሰው ያልደረሰ
ስቃይ ቁስል አዝለሽ _ ልብሽን ያራሰ
እጅሺን ያልሰጠሽ _ ለሂዎት ፈተና
ዕልፍ እሾህ ተሻግረሽ
ከዛሬ የደረሽ _ አዎ አንቺ ነሽ ጀግና
ሰው ቀርቦ ቢሸሽሽ _ እምነትሽን ቢያጓል
የነገው ሂዎትሽ _ የማይስተጓጎል
አጨለምናት ሲሉ _ ፈክተሽ የምትደምቂ
አስለቀስናት ሲሉ _ ንቀሽ የምትስቂ
ማለፍ የምታውቂ _ሁሉን ፈገግ ብለሽ
አንቺ ጀግና ሴት ነሽ
#ሼን
103 views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:51:11
....... የኛ ነገር .......
ተዋወቅን _ ተሳሳቅን
ተጣበቅን _ ተላቀቅን
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ደግሞ _ ደግሞ
ከርሞ _ ከርሞ
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ዃላ ዃላ _ ተናናቅን
መጨረሻ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.







#ሼን
101 views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:50:41
"ሳቄ አይበረክትም"
ሰላም ሂወቴ ውስጥ _ ድንገት ጓራ ብለህ
አርፎ የነበረን _ ያን ልቤን ቀስቅሰህ
በተስፍ ሞላሀኝ _ ምኞት አሳለምከኝ
ትናትናን እርሺው _ ነገን እኑር አልከኝ
እጄን አጥብቀህ ያዝክ _ አምኜኝ ተደገፍኩ
ቁስሌን እረስቼ _ አዲስ ጉዞ ጀመርኩ
ሁሉን ላንተ ተውኩኝ _ ሰጠሁህ እራሴን
አንተን ማቀፍ ጀመርኩ _ ተውኩና ትራሴን
በሀሴት ተሞላሁ _ ተነነ ብሶቴ
አርቄም አቀድኩህ _ ለቀጣይ ሂወቴ
ያን ጊዜ ጠብቀህ _ ድንገት እንደመጣህ
እንዲህ ሆንኩኝ ሳትል _ ከሂዎቴ ወጣህ
ጥያቄ ሰተኸኝ _ ለመልስ የሚቸገር
እላዬ ላይ ጭነህ _ የትዝታ ክምር
ለብቻዬ ተውከኝ _ ሄድክ ከጓኔ ስር
ለምን እንዴት ብዬ _ ከቶ አልጠይቅህም
እድሌ ነው እኔ _ ከድሮም አሁንም
ሀዘኔ ነው እንጂ _ ሳቄ አይበረክትም
#ሼን
103 views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:50:07
ፈርቻለሁ ......
ልቤ ውስጥ ለአንተ ያለኝ እምነት ብዙ ተሸረሸረ መሰል በወሬህ ውስጥ እውነት አልታይሽ ብሎኛል ፣ መለማመጥ ውስጤን አደከመኝ መሰል እንደበፊቱ አሁን ስታኮርፈኝ ብዙ እየጨነቀኝ አይደለም ፣ ነገሮችን ካንተ መጠበቅ ታከተኝ መሰል ኦላይን ገብተሀ እያየሁህ እንኳ ቴክስት ትልክልኛለህ ብዬ እንደ ሌላው ጊዜ አልጓጓም ፣ ደወልክም አልደወልክም ግድ እየሰጠኝ አይደለም እንጃ ተስፋ እየቆረጥኩብህ ነው መሰል ፈርቻለሁ
103 views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:49:41
"መስሏት ነበር እሷ"

ያኔ ጥላኝ ስትሄድ _ ከጎኔ ስትርቅ
ሁሌም የማለቅስ _ደግሜ የማልስቅ
መስሏት ነበር እሷ
ያኔ ስትገፋኝ _ ቀልዳ በፍቅሬ
ወድቄ የምቀር _ እዛው አቀርቅሬ
ቆይ ምኔ ሞኝ ነው
አንድ ሴት ብትሄድ _ ሊያውም የማትወደኝ
አንገቴን ደፍቼ _ ሁሌ እንባ ሚወርደኝ

ንገሯት ለዛች ሴት _ ለዛች ለማታውቀኝ
አንድ ተራ እንቅፋት
ከሂወት መንገዴ _ አይችልም ሊያግደኝ
#ሼን
102 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ