Get Mystery Box with random crypto!

ራስን ማግኘት!!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasenmagyet3679 — ራስን ማግኘት!!!
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasenmagyet3679 — ራስን ማግኘት!!!
የሰርጥ አድራሻ: @rasenmagyet3679
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.16K
የሰርጥ መግለጫ

ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት።ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ለሌሎች መልካም አድርግ።በሙሉ ልብህ እመን።ስላለህ ነገር አመስግን።ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።
መልካም ዛሬ(ከዛሬም አሁን)!?

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 09:12:37 “ለምን?” ብለህ ጠይቅ

ለመሻሻልና ለመለወጥ ከፈለክ፣ “ለምን?” ብለህ ከመጠየቅ አትረፍ!

•  “አሁን የምኖረውን ኑሮ በዚህ መልኩ የምኖረው ለምንድን ነው?”

•  “ገቢዬ ለምን በዚህ ብቻ ተወሰነ?”

•  “አምኜ የተቀበልኩትን የሕይወቴን ሂደት ለምን ተቀበልኩት?”

•  “የማደርገውን ነገር በዚህ መልኩ የማደርገው ለምንድን ነው?”

•  “በሕይወቴ መሻሻል የሚችል ነገር አለ ወይ? ካለስ ለምን
አላሻሽለውም? እንዴትስ ላሻሽለው እችላለሁ?”

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይህ ነው የማይባል የአእምሮ መነቃቃት ያመጣል፡፡ የተለመደውን የኑሮውን ሂደት “ለምን?” በማለት የማይጠይቅ ሰው በአንድ ቦታ ለመርጋትና ሃውልት ለመሆን ራሱን ያዘጋጀ ሰው ነው፡፡

አንድ ሰው ለመሻሻልና ለመለወጥ አእምሮውን ሊያነቃቃና የተለመደውን የየእለት የኑሮውን ዑደት “ለምን?” ብሎ ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ይህ ከተነቃቃ አእምሮ የሚነሳ ራስን የማሻሻልና የመለወጥ ጉዞ ባሉበት ሳይረኩ ከዛሬ ሁኔታ የተሻለ ነገር ውስጥ ለመግባት አስፈላጊውን ነገር ወደማድረግ ይወስደናል፡፡

እንዲሁ የመጣውን ሁሉ በመቀበልና በማስተናገድ በእድል ለመሻሻል ከመሞከር፣ አእምሮዬ እንዲሻሻል ማንበብ፤ የገቢዬ ምንጭ እንዲሻሻል ሙያዬንና ብቃቴን ማዳበር፣ ማሕበራዊ ኑሮዬ እንዲሻሻል ደግሞ ባህሪዬን ማጤንና ማሻሻልን ይጠይቃል፡፡

አንድን እውነታ መዘንጋት የለብኝም፣ የእኔነቴና የብቃቴ መሻሻል ዙሪያዬንና ሁኔታዎቼን ሁሉ ለመልካም የመለወጥ ብርታትና ተጽእኖ አለው፡፡ ስለዚህም፣ ማንነቴ፣ ብቃቴና ችሎታዎቼ መድረስ የሚችሉበት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ መጠየቅና መንቀሳቀስን አለማቆም ተገቢ ነው፡፡

አንዳንድ ዝም ብለህ ልትቀበላቸው የሚገቡህ ነገሮች የመኖራቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሁሉንም ነገር ግን ዝም ብለህ በጭፍንነት አትቀበል - “ለምን?” ብለህ ጠይቅ!!!

https://t.me/Lemen_Lemen
607 views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 20:24:39 መኖርን ለምን መረጥክ ?
የሰው ልጅ የመሞቱን ያህል መኖሩን አይፈራውም። እውነት ሳስበው ያስገርመኛል። መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ እርግጠኛ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች እንኩዋን ሞትን አብዝተው ይፈሩታል። መኖር እኮ እንደውም ያስፈራል። ምክንያቱም መሞታችን አንዴ እኛነታችን የሚቋረጥበት ሲሆን መኖራችን ግን ሁሌም በኛነት ጥያቄ ውስጥ ተይዘን የምንባዝንበት ነው። ትልቁ ጥያቄ ታድያ ይሄ ነው፦ ከመሞት ይልቅ መኖርህን ለምን መረጥከው? ጠዋት ከእንቅልፍክ ስትነሳ ምንድነው ያስነሳህ? ምንድነው እንድትኖር ያደረገህ ?ለምንስ መኖርክ ይሄን ያህል ዋጋ ተሰጠው? አየህ ይሄንን ነው መመለስ ያለብህ። ለምን ? ስለዚህ መኖርን መርጠህ እየኖርክ እስካለህ ድረስ የተሻለውን ምርጡን እና ትልቁን ህይወት ኑር። አለበለዚያ ግን መኖርህም መሞትህም ዋጋ የለውም። የምትኖረው ኖረህ ለማለፍ ነው ወይስ ሌሎችን ለማኗኗር ነው? አብዛኛው ሰው ኗሪ ሳይሆን አኗኗሪ ነው። የህዝብ ቁጥርን ሚጨምር ብቻ አለ። ስለዚህ ስትኖር ለምን? እድሜ ሲጨመርልህ ለምን ? አለዚያ ብዙ አበርክተው መሞት ሚፈልጉ አሉ ለነሱ ቦታ መልቀቅም ፅድቅ ነው። ስለዚህ የዘመንህ ጥያቄ ይሁን። ለምን እኖራለው ? ምን ልሰራ ? ምን ላበረክት? ምን ልሰጥ ነው የምኖረው ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። አለበለዚያ ግን ህይወት ላንተ ትርጉም የላትም ስለዚህ ሞትን አትፍራው። ምክንያቱም ለመኖር ሚያጓጓ ነገር የለህም።

https://t.me/Lemen_Lemen
2.0K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 11:36:35 "ራስህን አታታል"
፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩
በእውነት ራስህን ኹን እንጅ በመምሰል ራስህን አታታል። ብዙዎች ራሳቸውን ትተው መሰላቸውን መስለው ይኖራሉ። ራስህን መኾን ለበርካቶች ያልተቻለ ከባድ ሲኾን መምሰል፡ግን ለብርካቶች የቀለለ ለጥቂቶች ብቻ ያልተቻለ ጉዳይ ነው።
ወዳጀ
ከኹሉ አስቀድመህ ራስህን ኹን፣ ራስህን ተመልከት፣ ራስህን ዕወቅ። የት ቦታ እንደቆምክ መርምር። ምን አልባት የቆምክ መስሎህ ግን እየሰመጥክ እንዳይኾን። በታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ሲል ያስጠነቅቃል።
ብዙዎች የቆምን ሲመስላቸው ወድቀዋል፣ የጽናን ሲመስላቸው፡ሰምጠዋል፣ የበረታን ሲመስላቸው ተንኮታኩተዋል። የዕውነት የኖርን መስሏቸው በማስመሰል ገደል፡ተዘቅዝቀው ተገኝተዋል።
ስለዚኽ ወዳጀ
የቆምክበትን መሠረት፡መርምር፣ ከማስመሰል ወጥተህ በዕውነት ተገለጥ። በመሸፋፈን የተገኘ ትርፍም፡ኾነ ጽድቅ የለም። ስኬት በትግል እንጅ በመድበስበስና በማታለል ወይም በማስመሰል አይገኝም።
ስለዚኽ ከዛሬ ጀምርና በምን መልኩ ዕውነት እየኖርክ በምን ጉዳይ ደግሞ እያስመሰልክና ራስህን እያታለልክ እንደኾነ ራስህን መርምር።

#share
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
2.4K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 02:39:16 ትዝታዬ ... !

ለኔ ሁሉ ነገር ትዝታ ሆነና
አሁን ምለው አልፎ
ከዛሬው ተሸርፎ
በምናቤ ከንፎ
ነገ ላይ ጠበቀኝ
ትዝታን ታቅፎ,...

/አዳምኤል/ዳንኤል/
2.4K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 23:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 02:39:16 ****

ነገ ይቀርባል
ነገ ይርቃል፣
የቃላትን ሚስጥር ኧረ እስኪ ማን ያቃል፣

ጥቂት ይበራል ደግሞ ይጨልማል፣
የማይከፈትን በር ማንኳኳት ያደክማል፣

በጭላንጭል ተስፋ ረጅም ጎዳና፣
በደመነ ሰማይ
ባኮረፈ ሰማይ መውጣት ለፈተና፣

ጉልበትን ያዝላል ጥንካሬ ያርዳል፣
ይደጋገም እንጂ
የበረታም እንጨት በካፊያ ይረታል፣
አዎ!!
ጠብታ ጎርፍ ነው በጊዜ ሲሰፈር በጊዜ ሲለካ፣
ረጅሙ መንገድ እንዲ ያጥራል ለካ፣

የለም የለም!!
የለም አጥሮ አይደለም፣
አጭሩ መንገድ ነው ረዝሞ የከረመ፣
የቆመ ሚመስል ጥንቱን ያዘመመ፣

የሆሄያት ድርድር
ቃልነትን ይዞ ከቃላት ከጠፋ፣
እስኪ ፍቺ ስጠኝ
ከዚ በላይ ሚስጥር ምንአለ የሰፋ፣

ነገ ይቀርባል
ነገ ይርቃል፣
የቃላትን ሚስጥር ኧረ እስኪ ማን ያቃል?

ዲቦራ

@RasenMagyet3679
2.3K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 23:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 05:33:04 ቃል
ሮፍናን

@RasenMagyet3679
2.3K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , edited  02:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:36:36 እግዚአብሔር አለ ጊዜው ደርግ ማለትም ወታደራዊ መንግስት በኢትዮጵያ በሚገዛበት ወቅት ነው። አንድ በጥበቃ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ሰው ነበሩ። የእኒህ ሰው አሰሪያቸው ከወቅቱ ባለስልጣናት አንዱ ናቸው። ምስኪኑ ጥበቃ ለእንጀራ ብለው ስርዓቱን ቢጠጉም የወቅቱን ርዕዮተ ዓለም የማይቀበሉ ጠንካራ ክርስቲያን ነበሩ። ሰዉየው የባለስልጣኑን የመኖሪያ ገቢ በዘበኝነት ተቀጥረው እየጠበቁ እዚያው ውለው እዚያው ሲያድሩ በየጊዜው ለሚመላለሰው መኪና ቁጭ ብድግ እያሉ በር ከመክፈት ጀምሮ በቤትና ከቤትም ዉጭ በመላላክ ወዲህ ወዲያ ይላሉ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ባለቻቸው ሰዓት ዳዊታቸውን ሳይደግሙ አይውሉም ነበር። ሲበዛ ጸሎተኛ ናቸው። ባለስልጣኑ ግን ይሄንን አልወደደላቸውም። ይልቁንም ዳዊታቸውን በእጃቸው ይዘው ማሕደሩን በትክሻቸው አንግተው ጸሎት ላይ ሆነው ሲያያቸው አርድ እንቀጥቅጡ ይነሳበታል። በላዩ ላይ ያለው የጥርጥርና ክህደት መንፈስ እያስጨነቀ ያስቆጣዋል፣ ያሳብደዋል፣ ያስጮኸዋል ስለዚህ በወጣ በገባ ቁጥር ጸሎት እንዳይጸልዩ ይከለክላቸዋል። ደግሞ ደጋግሞ እግዚአብሔር የሚባል የለም ይላቸዋል። አንድ ቀን ግን አምርሮ "አንተ ሽማግሌ ከዛሬ ጀምሮ ይህንን ዳዊትህን ስትደግም ባይህ አብዮታዊ እርምጃ ነው የምወስድብህ" ብሎ አስጠነቀቃቸው። ሰዉየው ግን ጸሎታቸውን በፍጹም አላቋረጡም። ስለዚህ በሌላ ጊዜ ሲጸልዩ ስላያቸው በጣም ተበሳጭቶና ተቆጥቶ ዳዊታቸውን ቀምቶ በጥፊ ከመታቸው በኋላ "አንተ ሽማግሌ ነግሬህ ነበር እኮ እግዚአበሔር የለም..." ብሎ ጮኸባቸው። ሰዉየው የዋዛ አልነበሩም እንኳንስ ሊፈሩት ከፊታቸው ወዲያ ገፈተሩትና ለጥበቃ ስራ የተሰጣቸውን መሳሪያ አቀባብለው ከደቀኑበት በኋላ "እኔ እኮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲያ ስታንቋሽሸኝ ታግሼ ዝም ማለቴ፣ ስሰድበኝ ያልሰደበኩህ፣ ስትመታኝም ያልመታሁህ እግዚአብሔር አለ ብዬ ስለማምንና እግዚአብሔርን ስለምፈራ ነው አሁን አንተ እንዳልከው እግዚአብሔር ከሌለማ ምን አለፋኝ?" ብለው ያቀባበሉትን መሳሪያ ተኮሱና ግንባሩን ብለው ጣሉት ይባላል።
ምንጭ "ምጥን ቅመም ቁጥረ 4" መጽሐፍ

@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
2.3K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , edited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:25:48 +++ "በስሙ ጥራው" +++

ሰይጣን የሰው ልጆችን የክፋት እስረኛ ከሚያደርግበት ዘዴው አንዱ ኃጢአትን "ኃጢአት" ብለን እንዳንጠራት ማለሳለስ ነው። ከዚያ ይልቅ መልካም በሚመስልና ቢሰማም ብዙ በማይቆረቁር ስም እንድንጠራው ያደርገናል። ለምሳሌ በትዳር ሳይወሰኑ እንዲሁ ከአገኙት ጋር በዝሙት መውደቅ "ነጻ ፍቅር" ("free love")፣ በሚስት እና በባል ላይ መሄድ ደግሞ "ባለጉዳይ"ነት (affair) ተሰኝተዋል። ይህን የሚያደርጉትም ኃጢአቱን ያለ ምንም መሳቀቅ መሥራት እንዲችሉ ስሙን ያሳምሩታል።

ሰው የትኛውንም ኃጢአት ከመስራቱ በፊት ኃጢአቱን የሚጠራበት ስም ይለያል። ኃጢአትን የምንጀምረው በጎ ዓላማ እና ጥሩ ስም ያለው አስመስለን ነው። የሚሰክረው ከስካሩ በፊት ምን ልታደርግ ነው? ቢሉት "ልዝናና ነው" ይላል። የሚሳደበውና የሚራገመውም ከስድቡ በፊት ምን ልታደርግ ነው? ቢሉት "ልመክር" ወይም "እርማት ልሰጥ ነው" ይላል፤ ሌሎቹንም እንዲሁ። ጌታችን በመሰለው የጠፋው ልጅ ምሳሌ ላይ ያለውን ልጅ ከአባቱ ቤት ከመውጣቱ በፊት አግኝተን "ለምን ንብረት ተካፍለህ ከአባትህ ቤት ርቀህ ትሄዳለህ?" ብለን ብንጠይቀው፣ "ዓለምን ለማየት" ይላል እንጂ "ኃጢአት ስላማረኝ" እንደማይል ጥርጥር የለውም።

ከኃጢአት መራቅ ትፈልጋለህ? እንግዲያስ ልታደርግ ያሰብከውን ክፋት በስሙ ጥራው። አታድበስብስ፣ አታለስልስ፤ በቃ ኃጢአት ነው። ስለዚህ አትጀምረው። ገብተኽበትም እንደሆነ ስሙን እያሽሞነሞንክ ራስህን አትዋሸው። በደል እንደ ሆነ አምነህ በትክክለኛው ስሙ እስክትጠራውና እስክትጋፈጠው ድረስ መድኃኒት የለህም። መዝሙረኛው ዳዊት በኦርዮ ሚስት ተሰነካክሎ ከወደቀ በኋላ ዳግመኛ የተነሣው "አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ" ብሎ መጸለየ በጀመረ ጊዜ ነው።(መዝ 51፥4)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 2፣ 2014 ዓ.ም.
ሻሸመኔ

@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
2.3K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:42:17 ዛሬ ማየት የጀመረ ሰው ትናንት ማታ ጨለማ እንደነበር ሊናገር አይችልም።
1.7K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:58:05 በፍቅር ማሸነፍ!

ሰዎችን ሁሉ አሳምናለው ካልክ ከድካም ውጪ ምንም አታተርፍም፤ ዝቅ ማለት ካለብህ ዝቅ ትላለህ፣ ያንን ጊዜ አጎንብሰህ ማለፍ ካለብህ አጎንብሰህ ታልፋለህ።

አንዳንዴ ታሪክ የምትሰራው በማሸነፍ ብቻ አይደለም፤ ለፍቅር ስትል ዋጋ በመክፈልና በመሸነፍም ነው። ይሄን የምታደርገው ለጊዜው ተሸንፈህ ለዘላለም ለማሸነፍ ነው!
1.9K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ