Get Mystery Box with random crypto!

ራስን ማግኘት!!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasenmagyet3679 — ራስን ማግኘት!!!
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasenmagyet3679 — ራስን ማግኘት!!!
የሰርጥ አድራሻ: @rasenmagyet3679
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.16K
የሰርጥ መግለጫ

ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት።ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ለሌሎች መልካም አድርግ።በሙሉ ልብህ እመን።ስላለህ ነገር አመስግን።ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።
መልካም ዛሬ(ከዛሬም አሁን)!?

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-10 06:30:59 https://t.me/Enfelasefe10
2.2K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:15:09
ትርፍ ጃኬት ሁላችንም ዉጭ ለሚተኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች ለመስጠት እንዝመት

ከብርድ ቀድመን እንድረስላቸዉ!!
#share
2.5K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , edited  05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:55:43 ጊዜው መሄዱ አይቀርም!

በዚህ አለም ትልቁ ሽልማት ይሄ ቅፅበት ነው፤ ይቺ ቅፅበት ካለፈች አለፈች ነው፤ ማንም አይመልሳትም። የማይጠቅምህን ወሬ ስትሰማ ወይ ተራ ቪዲዮ ስታይ ከእድሜህ ላይ 10 ደቂቃም ቢሆን ቀንሰህ እየሰጠሀቸው መሆኑን አስታውስ።

እድሜህን እንዴት በነፃ ትሰጣለህ?! የምናደንቃቸው ታላላቅ ሰዎች ከፍታው ላይ የወጡት ዕድሜያቸውን ለሚጠቅማቸው ነገር ሰጥተው ነው። አንተ ብታነብ ባታነብ ጊዜው መሄዱ አይቀር፤ ብትሰራ ስራ ብትፈታ አመቱ ማለፉ አይቀር፤ ብትማር ባትማር ደቂቃው መክነፉ አይቀር፤ ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ! ነገ የተሻለ ቦታ ለሚያደርስህ ነገር ቅድሚያ ስጥ!
#Share
join us...
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
3.1K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , edited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:35:06 ያልተለወጠ ልብ
የለውጥ ሁሉ መጀመሪያ ልብ ነው፡፡ ባልተለወጠ ልብ ምንም አይነት ለውጥ ማማጣት አይችልም፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝ 50፡10 ‹‹ልበ ንጹሐ ፍጥር ሊተ እግዚኦ፤ መንፈሰ ርቱዐ ሐድስ ውስተ ከርሥየ፡- አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ›› በማለት አምላኩን በጸሎት የጠየቀው ያልተለወጠ ልብ ይዞ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ሲያስረዳን ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በሕዝ 36፡26 አዲስ ልብ እስጣችኋልሁ፤ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ በማለት ያስተማረን የድንጋ ልቡና ተሸክሞ ለለውጥ መዘጋጀት አይቻልም ሲለን ነው፡፡
ድንጋይ ፅኑዕ ነው ስለዚህ እንደድንጊያ ፅኑ፣ ጨካኝ የሆነውን ልቡናችሁን አርቄ ገር፣ የዋህና ትሑት የሆነ ልቡና እስጣችኋልሁ በማለት አምላካችን የተናገረው የሰው ልጅ ለውጥ የሚያመጣው ልቡናው ሲለውጥ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥልን ነው፡፡
በሕንድ አንድ የሚነገር ጥንታዊ ታሪክ እንዳለ ዳንኤል አለሙ እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡‹‹ አንዲት አይጥ ድመትን በጣም በመፍራቷ ወደ አንድ ተአምረኛ ሰው በመሔድ ወደ ድመት እንዲቀይራት ትጠይቀዋለች፡፡ እሱም ሀሳቧን ተቀብሎ ወደ ድመትነት ቀየራት፡፡
ነገር ግን አሁንም ከፍርሃት ስላልተላቀቀች ተኩላ እንዲያደርጋት ጠየቀች፡፡ አሁንም ነብርን በመፍራቷ ነብር እንዲያደርጋት ጠየቀች፡፡ እሱም ነበር አደረጋት፡፡ አሁን ከፍርሃት መውጣት ስላልቻለች ወደ ሌላ እንዲቀይራት ስትጠይቀው ተአምረኛው ሰው መልሶ ወደ ቀድሞ ማንነቷና ወደ አይጥነቷ›› ቀየራት፡፡ በዚህ ጊዜ ዐይጥ ለምንድነው ወደ ዐይጠነት የቀየርከኝ? ስትል ተአምረኛውን ሰው ጠየቀችው፡፡ እሱም ረጋ ባለ መንፈስ እንዲህ በማለት አስራዳት ‹‹ አንች ወደ ፈልግሽበት ብለውጥሽም ከፍርሃትሽ መላቀቅ አትችይም ምክንያቱም ልብሽ የዐይጥ ነው›› በማለት መለሰላት ይባላል፡፡
ከዚህ ታሪክ እንደምንማረው የአይጥ ልብ ይዞ ነብር መሆን አይቻልም፡፡ ባልተለወጠ ልቡና ለውጥ ማምጣት አይታሰብም፡፡ ውስጥህ ሳይለወጥ በውጫዊ መዋቅር ብቻ የምትፈልገውን መሆን አትችልም፡፡ ስለዚህ የለውጥ መጀመሪያ ቦታው ልብ መሆኑን ተረድተን እንደ ቅዱስ ዳዊት አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልን በማለት መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ ባልተለወጠ ልብ ለውጥ ለማምጣት መሞከር ከበሬ ወተት እንደመፈለግ ነው፡፡ አምላካችን ከውስጣችን ጨካኝ ልብን አርቆ ፍቅር ያለው፤ ሰላም ፈላጊ ልብን ያድለን!!
በፈንታነው አለልኝ
@RasenMagyet3679
2.6K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:33:17 ጠላታችን የተቀበልነውን ሁሉ እንደነበር ለማስቀጠል ያለን ችኮነት።

ጋሽ አለማየሁ ገላጋይ

@RasenMagyet3679
2.0K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 03:01:28 #ግሩም_አባባሎች

"ያለምክንያት የሚወድህን አምላክ እያሰብክ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው።"

"እያንዳንዱ ቀን ትንሽ ህይወት ነው ከእያንዳንዱ ህይወት ቀን ጀርባ አዲስ ህይወት አለ፣እያንዳንዱ ጠዋት ትንሽ ወጣት እያንዳንዱ የሌለት እንቅልፍ ትንሽ መሞት ነው።"
#አርተር_ሾፐን_ሀወር


"ዛሬን ለሰይጣን ነገን ደግሞ ለእግዚአብሔር አትስጡ።"
#ቅዱስ_ጎሮጎርዮስ

"ጥሩ ምላስ ስውር ማህተብ ያላት የዘመኑ ሰርተፊኬት ናት"

" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
#አቡነ_ሺኖዳ

"ህይወትህ ቀላል እንዲሆንልህ አትፀልይ፡፡ ጥንካሬ እንድታገኝ ፀልይ እንጂ፡፡ በአቅም ልትሰራው የምትችለውን ነገር ለማግኘት አትፀልይ፡፡ ልትሰራው ካሰብከው ነገር ጋር የሚመጣጠን ሀይልን እንድታገኝ ፀልይ፡፡ከዚያ አስደናቂው ነገር 'የሰራህው ስራ' ሳይሆን 'አንተ' ትሆናለህ፡፡"
#ፊሊፕ_ብረክስ

."በዓመቱ ውስጥ ምንም ሊከናወን የማይችልበት ቀን ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ አንደኛው ትናንት ሌላኛው ደግሞ ነገ ይባላል ፡፡ ዛሬ ለመውደድ ፣ ለማደግ እና ከሁሉም በላይ ለመኖር ትክክለኛው ቀን ዛሬ ነው።"
#ዳላይ_ላማ

join us...
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
2.7K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 00:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 02:07:09 የዋህነት ማለት ክፋትን በክፉ ለመመለስ ሙሉ ሀይል ይዞ ነገር ግን ሀይል ለክፋት ላለመጠቀምና እራስን መግዛት ማለት ነዉ።የዋህ ማለት ሞኝ ማለት ሳይሆን ሀይል እንዳለዉ እያወቀ ሀይሉን ለክፋት ሳይሆን ለመልካምነት ብቻ ለመጠቀም የወሰነ እራሱን የሚገዛ ማለት ነዉ፡፡

በየዋህነት ዉስጥ ደሞ ጥሩነት ወይም መልካምነት አለ።መልካምነት እንደወጥ ማጣፈጫ ጨዉ ማለት ናት ማንም ሰዉ በዉስጡ መልካምነት ሳይኖረዉ ደስተኛ መሆን፡መርካት፡ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፡ጤናማ መሆን አይችልም።ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለዉም ድንበር የለዉም ጥቁር ነጭ አይልም በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት ሁል ጊዜ ለሰዉ በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ እራስ ወዳድነት የማይሰማዉ ልዩ ነዉ መልካምነት።የሚገርመዉ መልካምነት ሁሌ በመስጠት በማድረግ የሚረካ ሲሆን ትርፉም የህሊና ሰላም ደስታ ፍቅር ጤና ብቻ ብዙ ነገር እናገኝበታለን ።

ታድያ ይሄ ደስ አይልም
መልካም ነገር ማድረግ ባንችል እንኳን ከመጥፎ ስራዎች እንቆጠብ

@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679
2.2K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 23:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 13:05:06 ይበልጥ ከፍ ለማለት !

የኔ ማደግ ትልቅ ድርሻ የሚኖረው ከአጠገቤ ያለው ወንድሜ ማደግ ሲችል ነው ! በዚህች አለም ላይ የብቻ ስኬት የለም ሌላውን እየጣሉ ከፍ ማለት የለም ፤ ይበልጥ ከፍ ማለት ከፈለግን መተባበር ለሌሎችም መንገድ መክፈት እና ከልብ መረዳዳት የግድ ነው። ያኔ ስኬቱ በራሱ ወዝ ለብሶ መጥቶ በእጃችን ይቀመጣል!

የተባረከ ቀን ይሁንላቹ።
2.6K views አዳምኤል ' .?¿.㋛︎.?. , 10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ