Get Mystery Box with random crypto!

'ራስህን አታታል' ፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩ በእውነት ራስህን ኹን እንጅ በመምሰል ራስህን አታታል። ብ | ራስን ማግኘት!!!

"ራስህን አታታል"
፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩፩
በእውነት ራስህን ኹን እንጅ በመምሰል ራስህን አታታል። ብዙዎች ራሳቸውን ትተው መሰላቸውን መስለው ይኖራሉ። ራስህን መኾን ለበርካቶች ያልተቻለ ከባድ ሲኾን መምሰል፡ግን ለብርካቶች የቀለለ ለጥቂቶች ብቻ ያልተቻለ ጉዳይ ነው።
ወዳጀ
ከኹሉ አስቀድመህ ራስህን ኹን፣ ራስህን ተመልከት፣ ራስህን ዕወቅ። የት ቦታ እንደቆምክ መርምር። ምን አልባት የቆምክ መስሎህ ግን እየሰመጥክ እንዳይኾን። በታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ሲል ያስጠነቅቃል።
ብዙዎች የቆምን ሲመስላቸው ወድቀዋል፣ የጽናን ሲመስላቸው፡ሰምጠዋል፣ የበረታን ሲመስላቸው ተንኮታኩተዋል። የዕውነት የኖርን መስሏቸው በማስመሰል ገደል፡ተዘቅዝቀው ተገኝተዋል።
ስለዚኽ ወዳጀ
የቆምክበትን መሠረት፡መርምር፣ ከማስመሰል ወጥተህ በዕውነት ተገለጥ። በመሸፋፈን የተገኘ ትርፍም፡ኾነ ጽድቅ የለም። ስኬት በትግል እንጅ በመድበስበስና በማታለል ወይም በማስመሰል አይገኝም።
ስለዚኽ ከዛሬ ጀምርና በምን መልኩ ዕውነት እየኖርክ በምን ጉዳይ ደግሞ እያስመሰልክና ራስህን እያታለልክ እንደኾነ ራስህን መርምር።

#share
@RasenMagyet3679
@RasenMagyet3679