Get Mystery Box with random crypto!

**** ነገ ይቀርባል ነገ ይርቃል፣ የቃላትን ሚስጥር ኧረ እስኪ ማን ያቃል፣ ፡ ጥቂት ይበራል ደ | ራስን ማግኘት!!!

****

ነገ ይቀርባል
ነገ ይርቃል፣
የቃላትን ሚስጥር ኧረ እስኪ ማን ያቃል፣

ጥቂት ይበራል ደግሞ ይጨልማል፣
የማይከፈትን በር ማንኳኳት ያደክማል፣

በጭላንጭል ተስፋ ረጅም ጎዳና፣
በደመነ ሰማይ
ባኮረፈ ሰማይ መውጣት ለፈተና፣

ጉልበትን ያዝላል ጥንካሬ ያርዳል፣
ይደጋገም እንጂ
የበረታም እንጨት በካፊያ ይረታል፣
አዎ!!
ጠብታ ጎርፍ ነው በጊዜ ሲሰፈር በጊዜ ሲለካ፣
ረጅሙ መንገድ እንዲ ያጥራል ለካ፣

የለም የለም!!
የለም አጥሮ አይደለም፣
አጭሩ መንገድ ነው ረዝሞ የከረመ፣
የቆመ ሚመስል ጥንቱን ያዘመመ፣

የሆሄያት ድርድር
ቃልነትን ይዞ ከቃላት ከጠፋ፣
እስኪ ፍቺ ስጠኝ
ከዚ በላይ ሚስጥር ምንአለ የሰፋ፣

ነገ ይቀርባል
ነገ ይርቃል፣
የቃላትን ሚስጥር ኧረ እስኪ ማን ያቃል?

ዲቦራ

@RasenMagyet3679