Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85.94K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2024-04-18 16:41:21 ዛሬም ገደሏቸው…
==============
(ምን ይሻል? ለማን አቤት ይባል? እስከ መቼ?)
||

ዛሬ ጎንደር ዙሪያ እንፍራንዝ አካባቢ ልዩ ስሙ "ውሻ ጥርስ" በተባለ ቦታ አራት ደረሳዎች በጥይት ተደብድበው በጽንፈኛው ኃይል መገደላቸውን ሰምተናል።
የአማራ ክልል ሙስሊም ማኅበረሰብ በራሱ ክልል ውስጥ «ሙስሊም» በመሆኑ ሳቢያ ይገደላል።
ከራሱ ክልል ውጭ ደግሞ «አማራ» በሚል ሰበብ ይገደላል።

ነገሩ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በክልሉ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥሎ ማገትና ግድያ በቀላሉ ማስቆም ከባድ ይመስላል። ምክንያቱም ያለው የክልሉ ፖለቲካዊ ተጨባጭ ብዙም ለዚያ የሚጋብዝ አይደለም።

ምናልባት የሚያዋጣ ከሆነ የፌዴራል መጅሊስ ሰዎች ከክልሉ መጅሊስ ጋር ጉዳዩን በሰፊው ይወያዩበትና፤ ገዳዩ ኃይል ባለባቸው የስጋት አካባቢዎች ከሚገኙ የክርስትና እምነት የኃይማኖት አባቶች ጋር ተወያይቶ በነርሱ በኩል በሽምግልና ግድያውን ማስቆም ሳይሻል አይቀርም።

ባላፈ ባህር ዳር ላይ 5 ወንድሞቻችንን ቀበርን፣ ጎንደር ላይ ገድለዋል፣ ዛሬም ደገሙ። እንዲህ እንዲህ እያልን ሙት እየቆጠርን ጨርሰው እስከሚጨፈጭፏቸው ድረስ መጠበቅ የለብንም። መስጅዶችና ሐሪማዎችንም አውድመዋል። ጉዳዩ እንደያኔው ግልፅ የኃይማኖት ጥቃት ነውና አሁን ካለው ተጨባጭ አንፃር በራሳቸው ሰው በኩል ሽምግልና ከመሞከር የተሻለ ነገር አይታይም።

ራሳቸውን እንኳ እንዳይከላከሉ ከጽነፈኛው ዘረፋ የተረፈውን ህጋዊ መሳሪያቸውን መከላከያ ወስዶባቸዋል። መከላከያ መሳሪያቸውን ከወሰደ ደህንነታቸውን ማስከበር ግደታው ነበር። ግን ወይ ራሳቸውን እንዲከላከሉ አላደረገ፣ ወይ ራሱ አልተከላከለ፣ ባዶ እጃቸውን ለገዳይና ለዘራፊ አጋልጧቸዋል። አሁንም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

ሌላው ቢያንስ በመልካም ዱዓችን አንርሳቸው።

||
t.me/MuradTadesse
16.5K viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 16:19:48 አስተማሪና መሳጭ ታሪክ
===================

«በስዑዲ የሚኖር የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5000 ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳን-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡
ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2000 ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”
“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡
ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡
“ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡
ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡
ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡
“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡
ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡
በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡
“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡»
የተተረጎመ
: ኢብኑ ሙነወር፤ መጋቢት 25/2010]
16.8K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 13:24:52
ውሸት ጥሩ አይደለም፤ አጉል ብልጣ ብልጥነት ለጊዜወው ያዋጣ ቢመስልም ሩቅ አያስሄድም።
አሁን ችግሩ'ኮ፤ የሁላቸውም መልስ አንድ አይነት መሆን አለበት ማለቱ እንጂ እንደለመዱት ዋሽተው ይመልሱ ነበር፤ እንዳይኮራረጁም አፍጥጧል። ሽግርግር ያለ ነው ነገሩ¡
17.5K views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 07:54:52
19.4K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 07:54:51
18.8K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 07:12:09
የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ

[Part: ⓵⑤⑦⑤]


#ቁርኣን
17.9K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 23:36:11
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ

[Part: ⓵⑤⑦④]


#ቁርኣን
18.2K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 23:35:03
ሙስሊሞች በሙሉ -                     እውነቷን እንወቅ ከሐቋ እንግጠም -                    ሌላን እንጠንቀቅ ማስረጃን እንውደድ -                      ይቅር መረበሹ ለሸዋል ፍቺ                   በዓሉን  ለሚሹ የዒድ ትልቅ              እንጂ- የለውም ትንሹ! መፈብረክ አንወድም -                    ከሱናው ነን…
17.9K views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 22:29:49 ሙስሊሞች በሙሉ -
                    እውነቷን እንወቅ

ከሐቋ እንግጠም -
                   ሌላን እንጠንቀቅ

ማስረጃን እንውደድ -
                     ይቅር መረበሹ

ለሸዋል ፍቺ
                  በዓሉን  ለሚሹ

የዒድ ትልቅ 
            እንጂ- የለውም ትንሹ!

መፈብረክ አንወድም -
                   ከሱናው ነን እኛ

መመሪያ ደርሶናል -
                      ከሰማዩ ዳኛ

   ሐቁን እንሰብካለን -
                    ሂዳያን አንሰርቅም

ዒዳችን ታላቅ ነው -
               ትንሽ ዒድ አናውቅም!

: @tezkiraChannel
18.9K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 22:01:25
መልካም ሚስት!
18.8K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ