2023-04-14 07:08:49
ዕለተ ዓርብ ስቅለተ ክርስቶስ (የድህነት ቀን) ይህች ዕለት አዳም ኋላም ሔዋን የተፈጠሩባት፡ ከገነትም ተሰደው የወጡባት ዕለት ናት፡፡ ጌታም ቀደም የሥነ ፍጥረት ሥራውን እንደፈፀመበት። አሁንም የድህነት ሥራውን ፈጸመባት በዚች ዕለት በአምላካችን ላይ የተፈጸመው መከራ እጅግ አሰቃቂና በፍጡር ሊገለጹ የማይችሉ ናቸው፡፡
የክብርን ባለቤት ጭፍሮች ይዘው በሊቀ ካህናቱ ፊት አቀረቡት፡፡ሊቀ ካህናቱም ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደሆንክ ንገረኝ›› አለው ጌታም ‹‹ አንተ አልህ…የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ ›› ሲለው ሊቀ ካህናቱ ‹‹ ተሳደበ›› በማለት ፊቱን ነጨ ልብሱን ቀደደ፡፡በኦሪት ሕግ እንዲህ ያደረገ ሊቀ ካህን ይሻር ትል ነበር፡፡ጌታ እንደተሸመበት እርሱ እንደተሻረበት ለማጠየቅ፡፡( ማቴ26፥57-65. ማር14፥47-54፣ ሉቃ22፥47-54፣ ዮሐ18፥1-24 )
✞ ጌታ እንደተናገረው ጴጥሮስ ደሮ እስኪ ጮህ ሦስተ ጊዜ ካደው በዚህም ጊዜ ደሮ ጮኸ፡ ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም። ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው። ጴጥሮስም ጌታ ያለውን አስታውሶ እንዲህ ሲል
አለቀሰ ‹‹ ከሁሉ ይልቅ እወደው ከሁሉ አስቀድሞ እኔ ልካደው››ብሎ ከልቡ ስላለቀሰ ንስሐውን ተቀብሎለታል፡፡ (ማቴ26፥6
9-75፣ ማር14፥67-72፣ ሉቃ22፥55-62፣ ዮሐ18፥25-27 )
❖ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ የተያዘባት ምሽት ሐሙስ ሦስት ስዓት ማታ ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት። አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ። (ማቴ 26 ፥ 47 )
✿ ስለዚህ ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ሎሌዎችን ተቀብሎ በችቦና በፋና በጋሻ ጦርም ወደዚያ መጣ። ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና። ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው።
✿ የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ። እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።
እንግዲህ። እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ፡፡ (ዮሐ 18 ፥ 3 - 6)
❖ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የታሰረበት ጊዜ መንፈቀ ሌሊት (ሐሙስ ምሽት ስድስት ሰዓት) እንግዲህ የሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን። ይዘው አሰሩት፥(ዮሐ 18፥12) ❖ አስራ ሁለት ስዓት ጊዜ ነግህ (ዓርብ ጠዋት) ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ። ፈት በፍርድ አደባባይ ቆመ
✞ ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት በፍጥረታት ሁሉ ላይ የሚፈርደው ሰማያዊ ንጉስ ለፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡
✞ ጲላጦስም መርምሮ ለሞት የሚያበቃ አንዳች አጣበት ሕዝብ ግን ስቀለው ስቀለው እያሉ አብዝተው ጮኹ፡፡ የተባለችው የጲላጦስ ሚስት ክፉ እንዳያደርግበት ለባለ መልዕክት ላከች ስለእርሱ በህልሟ ስትሰቃይ አድራለችና፡፡
✞ ጲላጦስም ክርስቶስ የገሊላ ሰው መሆኑን ሲረዳ የገሊላ ገዥ ወደ ሆነው ሄሮድስ ሰደደው፡፡ጲላጦስና ሄሮድስ በግዛት እና በዳኝነት ይጣሉ ነበር አሁን ግን በጌታ ሞት ታረቁ፡፡
ሄሮድስም ገርፎ ለጲላጦስ መለሰለት፡፡( ማቴ 27፥1-14 ፤ ማር 15፥1-5 ፤ ሉቃ 23፥1-56፤ ዮሐ18 ፥28-38 )
❖ #አርብ #ሦስት #ስዓት(#ጊዜ #ሰለስቱ)፡- ጌታችን ከጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ስዓት በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው።
ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤
✞ ሦስተኛም። ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው። እነርሱ ግን እንኳን ሊራሩ " ጀርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፥ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።"(ኢሳ 50 : 6) እንዳለ ነብዩ አርባ ጅራፍ ብቻ መግረፍ ሲኖርባቸው እየተፈራረቁ ክንዳቸው እስኪዝል ስፍር ቁጥር የሌለው ጅራፍ 6666 ጊዜ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት፡፡ጲላጦስም ለስልጣኑ በመፍራት ንጹህ እንደሆነ እጁን በመጣጠብ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ( ማቴ 27 ፥ 24-26፤ ማር15፥6-15፤ ሉቃ23፥13-26፤ ዮሐ 19፥1ዮሐ 18፥28-38 )
❖ #አርብ #ስድስት #ስዓት (ጊዜ ስድስቱ ሰዓት)፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጁና እግሩን ተቸንክሮ በቀራኒወ አደባባይ የተሰቀለበት ስዓት ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት። ከባዱን ዕፀ መስቀል መሸከሙ ከባዱን ኃጢአታችንን እንደተሸከመ የሚያጠይቀ ነው፡፡ቅ.ጴጥሮስ ‹‹ ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ›› እንዳለ (1ጴጥ2፥22)፡፡
✞ ስምኦን የተባለ የቀሬና ሰው ነገር ፈርቶ ተሰውሮ ውሎ ነገር ተፈጽሞ ይሆናል ብሎ ሲመለስ አገኙትና አንተም የእርሱ ወገን
ነህ መስቀሉን ተሸከም ብለው አሸከሙት ምስጢሩ ግን ጌታ ከበረከተ መስቀሉ ሊያሳትፈው ስለፈለገ ነበር፡፡( ማቴ27፥27-31
፤ማር15፥16-20፤ ሉቃ23፥26-30፤ዮሐ19፥17 )
✞ ወንበዴ እንዲመስላቸው ‹‹ ደግ አደረጉ የስራውን ነው እንዲሉ›› በግራና በቀኝ ወንበዴዎችን አድርገው ሰቀሉት፡፡ ኢሳኢያስ በትንቢት‹‹ ከአመጸኞች ጋር ተቆጠረ››ያለው ተፈጸመ፡፡( አኢሳ 53፥12 )
✞ ጌታችን በፍጹም ያፈቀረውን የሰውን ልጅ ሊክስ መጥቷልና ወደ ዕጸ በለስ የገሰገሱ የአዳምን እግሮች ለመካስ እግሮቹ ተቸንክረው ዋሉ፣የበለስን ፍሬ የቀጠፉ እጆቹን ለመካስ እጆቹ ተቸንክረው ዋሉ፣ጣፋጩን የበለስን ፍሬ መቅመሱን ለመካስ መራራ ሐሞት ቀመሰ፡፡
✞ ጲላጦስ አይሁድ ተመቅኝተው ለሞት አሳልፈው እንደሰጡት ያውቅ ነበርና ‹‹የአይሁድ ንጉስ የናዝሬቱ ኢየሱስ ›› የሚል ጽሁፍ
በሦስት ቋንቋ በጽርዕ ግሪክ፣ በዕብራይስጥ፣ በሮማይስጥ በመጻፈ መስቀሉ ላይ አኖረ፡፡[ ማቴ26፥37፤ ማር15፥27፤ ሉቃ23፥38፤ ዮሐ19፥19-22 ]
☞ ቅዱስ ማርቆስ በምዕ.15፥25 ላይ ጌታችንን ‹‹በሰቀሉት ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበር፡፡›› ይበል ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በምዕ.19፥14 ላይ ስድስት ሰዓት መሰቀሉን ገልጦልና፡፡ በዚህ የተለያዩ አይደሉም፡፡ ነገር እንደ ዮሐንስ ነው ቅዱስ ማርቆስ ግን 3 ሰዓት ማለቱ የጌታችን የመስቀሉ ነገር የተበየነው (የተወሰነው) በ3 ሰዓት በመሆኑ ነው የተወሰነበት ሰዓት ይዞ
ከተወሰነ መሰቀሉ እንደማይቀር አውቆ 3 ሰዓት አለ፡፡
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
3.4K views••●◉ Estifanos ◉●••, 04:08