2023-04-13 07:19:22
ዘንድ ፈቃድ ያገኘንበት የነፃነት አዋጅ የታወጀበትም ዕለት ነው። ክቡር ሥጋው ቅዱስ ደሙን ቀምሶ ለሐዋርያቱ የሰጠበት ፣ የሰው ልጅ ነጻነት የተሰበከበት፣ ያጣናት ዕጸ ሕይወት(ሥጋ ወደሙ) ዳግም በስምዖን ቤት በተግባር የተሰጠችበት፣ ትህትና የተሰበከበት ፣ አዳምን በግዕዛን (በነጻነት) የፈጠረ አምላክ ከሐዋርያቱ (ከሐዋርያት ጋር ሕብረታችን አንድ ስለሆነ የሐዋርያትን እጅ እጅ አድርጎ "ከእርሱም ጋር በላን ጠጣን" አባ ሕርያቆስ እንዳለ)ከእኛም ጋር የበላበት ዕለት በመሆኑ የነጻነት ሐሙስ ትባላለች። ዮሐ(15፤15) (1ኛጴጥ2፤10)
በተዋሕዶ ሞትን፣ የሞት ፍርድንም ተቀበልን። ሰይጣን ዲያብሎስ እባብን ተዋሕዶ እባብን መስሎ ገነት በመግባት አዳምና ሔዋንን አሳስቶ አስፈረደባቸው። እኛም በተዋሕዶ ብንጠፋም በተዋሕዶ ዳንን። እግዚአብሔር ሰው ሆኖ አዳነን። " በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። #ቃልም_ሥጋ_ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ። " ዮሐ፣ 1፥1 እና 14።
6 የትዕዛዝ_ሐሙስ_ይባላል የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እኔን ጌታና መምህር ትሉኛላችሁ፣እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገ፟ባ፟ችኋል .... ።"አድርጉ ብሎ ያዘዘበት ዕለት በመሆኑ ትዕዛዝ ሐሙስ ይባላል ። ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ ፣ መታሰብያየን አድርጉ ብሎ ያዘዘበት ዕለትም ነውና ትዕዛዝ ሐሙስ ይባላል ።
7 አረንጓዴው_ሐሙስ_ይባላል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጌተሴማኒ በአተክልቱ ቦታ ረዘም ላለ ሰዓት ስለጸለዬ ያንን ሥፍራ ለምለም ስለነበረ ለማስታወስ ሲባል ዕለቱን አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል ። አንዲም በዲያብሎስ እስራት ደርቀን የነበርን እኛን የአዳም ልጆች ክርስቶስ ከእስራት ነፃ አውጥቶን ማንነታችን ያለመለምልን በመሆኑ አረንጓደው ሐሙስ ይባላል ።
8 የአገልግሎት_ሐሙስ_ይባላል በዚህ ስያሜ የተጠቀሰው ጌታችን በፍጹም ፍቅር ፣በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ዝቅ ብሎ ያጠበበት የአገልግሎትን ነገር ያስረዳበት ስለሆነ የአገልግሎት ሐሙስ ይባላል ።
"እኔ ለእናንተ እንዳደረግኹ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለኹና።እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ባሪያ ከጌታው አይበልጥም።መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።ይህን ብታውቁ፥ብታደርጉትም ብፁዓን ናችኹ። "ዮሐ ፲፫÷፲፭_፲፯
በዚህም ስናስተውል ሲያስተምረን አሳልፎ የሚሰጠው ጠላቱን ይሁዳንስ እንኳን እራሱን ዝቅ አድርጎ በፍጹም ፍቅር አጠበው ከምሥጢር ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁ ብሎ እንዳያመካኝ ከምሥጢር ሁሉ አላጎደለውም።
ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ደግነትህን የምንገልጥበት ቋንቋ የለንምና ወደ ዝምታ ውቅያኖስ ገብተን እንሸሸጋለን።
ራስህን ፈትተህ (ቆርሰህ) እንካችሁ ብሉ ትለናለህ። ከራስህ ቀድተህ እንካችሁ ጠጡ ትለናለህ። እንደሞትህ ኾነህ ምሥጢረ ቁርባንን ትመሠርታለህ። አንተው ቀድሰህ አንተው መሥዋዕት ትኾናለህ። ሞተሀል ብለን እንዳንወሰን ሕያው ነህና መሥዋዕቱን ራስህ ትቀበላለህ። ከጎንህ በፈሰሰው ውኃ ልጆችህ ታደርገናለህ። ዝቅ ብለህ እግራችንን ታጥባለህ።
በደግነትህ ታስደምመናለህ። ስላንተ ምን ብለን እንናገር ዘንድ እንችላለን? ደግነትህ ከባሕር አሸዋ ከሰማይ ከዋክብት ከቁጥራቸው እልፍ ወትእልፊት ጊዜ በላይ ይበዛል። በዚህ ላይ አልተጠየፍኸንምና እናመሰግንሀለን።
እግዚአብሔር የዓለማት ሁሉ መጋብ ገዥ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የሐዋርያትን እግር ማጠቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ አባቶች መምህራን ምዕመና እኔ የበላይ ኃላፊ ነኝ መስራት አይገባኝም፣ እነርሱ ይስሩ ማለት ሳይሆን እኛ ለሌሎች አርአያ እንድንሆን ለአባቶቻችን እንዲንታዘዝ ፣ በቅንነት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲናገለግል፣ በፍጹም ፍቅር ፣የዋህነት ለምዕመናን ወንጌሉ እንድደርስ እንዲናገለግል ምሳሌ ሆኖ አስተማረን።
የፋስካ_ዝግጅት_በተደረገበት_በዚህች_ዕለተ_ሐሙስ_ጌታችን_መዲኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ:-
❖ ለደቀ መዛመርቱ የማጠቃልያ ትምህርት የሰጠበት
❖ ከፋስካ ጋር ሥርዓተ ሐዲስን የመሰረተበት
❖ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ አብሮ የነበረበት
❖ ስለ ሁሉ ራሱን በፊቃዱ አሳልፎ በመስጠት ፍቅሩን የገለጠበት
❖ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ፍጹም ትህትናውን የገለጠበት
❖በአስቆሮቱ ይሁዳ ተላልፎ የተሰጠበት
❖ወታደሮቹ የያዙበት ዕለት በመሆኑ ይነገራል።
( ማቴ 26÷46 ማር 14÷42_52
ሉቃ 22÷ 1 ዮሐ 18÷1_12 )
"ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በህማማቲሁ ........"
አምላካችን ከዕለቱ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን ።
እንበለ_ደዌ_ወሕማም
እንበለ_ጻም_ወድካም
አመ_ከመ_ዮም_ያብጽአነ_ያብጽአክሙየተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ለመቀላቀል
┏━━° •❈• ° ━━┓
@mezmurochh
@mezmurochh
@mezmurochh
┗━━° •❈• ° ━━┛
339 views••●◉ Estifanos ◉●••, 04:19