Get Mystery Box with random crypto!

መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ meazahaymanot — መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ meazahaymanot — መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር
የሰርጥ አድራሻ: @meazahaymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.56K
የሰርጥ መግለጫ

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡"
"በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"
                 መጽሐፈ ሰዓታት
የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-12 09:52:30 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ናሆም ጥያቄ

1. ናሆም ማለት ምን ማለት ነው

2. ትንቢተ ናሆምን የጻፈው ቅዱስ አባት ማነው

3. የነበረበት ዘመንም____ ዘመነ መንግሥት ነው

4. ትንቢተ ናሆም ስንት ምዕራፎች አሉት

5. አከፋፈሉ እንዴት ነው

6. ከትንቢተ ናሆም ምን እንማራለን?

7. የነቢዩ ናሆም ክብረ በዓል መቼ ነው

መልሱን እስከ ዛሬ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
169 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 08:39:53 #ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ !

"አገልጋይ ሆነህ ስትታዘዝ አትከፋ። ክርስቶስ የመጣው በባሪያ መልክ ነውና። እርሱ በጌትነት አርአያ ቢመጣ አይደንቅም ነበር። የዘላለም ጌታ በባሪያ መልክ መምጣቱ ግን ድንቅ ነው። አገልጋይነትን ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ የባረከው ተግባር ነውና ደስ ይበልህ። አንተ የሰው አገር ተሰድደህ ተመችቶህ እንኳ ከፍቶህ ከሆነ ክርስቶስ ግን ወደማይመቸው ወደ ሲና በረሃ እንደ ተሰደደ አስታውስ። አንተ ለምነህ እንጀራ ስታገኝ በእንባ ትጎርሰዋለህ ፣ ክርስቶስ ግን በመስቀል ላይ ተጠማሁ ብሎ ሆምጣጤ እንደ ሰጡት አስብና ትሑት ሁን። አንተ በራስህ መቃብር ስትቀበር ክርስቶስ ግን በተውሶ መቃብር እንደ ተቀበረ እወቅ።"

@meazahaymanot
159 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 07:50:28 አምላካችን ሆይ አምላክ ሆይ
ልጆችህን አስበን(2)
በክንፈ ረድኤትህ በረከትን ስጠን
በምህረት እጆችህ ጸጋህን አብዛልን (2)

ዓለም በወጥመዷ አምላክ ሆይ
ስባ እንዳትጥለን ''
ምራን ጌታችን ሆይ "
ከኃጢያት አድነን
የሰይጣን ምትኮኛ
ሆነን እንዳንቀር
የሰላም ባለቤት
በህይወታችን ኑር
እኛ ኃጥአን ነን አምላክ ሆይ
አንተን የበደልን "
መብራትና ዘይት "
የሌለን በእጃችን "
እባክህ ጌታ ሆይ
ከደጅ አታስቀረን
የጅህ ሥራዎች ነን
አቤቱ ራራልን
ምንም ብዙ ቢሆን አምላክ ሆይ
እዳ በደላችን "
ከፊትህ ለመቆም "
መልካም ግብር ባይኖረን
ስለ ቅዱሳኑ
ስለተመረጡ
ከጥፋት አድነን
ሰውረን ከእሳት

@meazahaymanot
195 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 07:49:46 ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሁለት(፪)
@meazahaymanot
174 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:35:16 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ናሆም ጥያቄ

1. ናሆም ማለት ምን ማለት ነው

2. ትንቢተ ናሆምን የጻፈው ቅዱስ አባት ማነው

3. የነበረበት ዘመንም____ ዘመነ መንግሥት ነው

4. ትንቢተ ናሆም ስንት ምዕራፎች አሉት

5. አከፋፈሉ እንዴት ነው

6. ከትንቢተ ናሆም ምን እንማራለን?

7. የነቢዩ ናሆም ክብረ በዓል መቼ ነው

መልሱን እስከ ነገ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
240 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:19:28 ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል (፪)
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሱሕ ሊቀ መላእክት (፪)
208 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 16:40:22 ማኅደረ ጥያቄ

የትንቢተ ዮናስ መልስ

1. ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው፡፡

2.ነቢዩ ዮናስ ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ወገን  ነው

3. አባቱ አማቴ እናቱም ሶና ይባላሉ፡፡ 

4. ነቢዩ ዮናስ በአገልግሎት የነበረበት ዘመን በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ሲሆን  ከ፰፻፳፭ እስከ ፯፻፹፬ ቅ.ል.ክ. ገደማ  ነው፡

5. ነቢዩ ቅዱስ ዮናስ

6. አራት ምዕራፎች

7. ምዕራፍ አንድን ስናነብ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ኼዶ እንዲያስተምር እንደታዘዘና 
ምዕራፍ ኹለትን ስናነብ ነቢዩ ዮናስ ወደ ባሕሩ ሲጣል ዓሣ አንበሪእንደተቀበለውና በከርሡም ሦስት ሌሊትና ሦስት መዓልት እንደተሸከመው
ምዕራፍ ሦስትን ስናነብ ዓሣ አንበሪው ነቢዩ ዮናስን እንደተፋውና ወደ ነነዌ እንደኼደ የነነዌ ሰዎችም በዮናስ የንስሐ ጥሪ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንተመለሱ
ምዕራፍ አራትን ስናነብ ደግሞ ነነዌ እንደዳነችና እግዚአብሔርም ዮናስን በአስደናቂ ጥበቡ የውስጥ ሰላሙን እንደመለሰለት

8. ትንቢተ ዮናስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅና የማይለካ ፍቅር የተገለጠበት መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፉ እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይኾን የኹሉም አምላክ እንደኾነ ተገልጧል፡፡ የሕዝብም የአሕዛብም ሠራዒና መጋቢ እንደኾነና የኹሉም ድኅነትን እንደሚሻ ተመልክቷል፡፡
፨     በመጽሐፉ የነቢዩን ድካም ተገልጧል፤ ይኸውም ነቢያት እንደኛ ሰዎች እንደነበሩና ድካም እንደነበረባቸው ግን ደግሞ እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጥበቡ ድካማቸውን ለታላቅ ተልእኮ እንደተጠቀመበት ተጽፏል፡፡
፨     እግዚአብሔር ከአእምሮ በላይ ጠቢብ እንደኾነ፣ ፈጣሪን አያውቁም ተብለው ለሚታሰቡ እንደ መርከበኞቹ ላሉ ሰዎች እንኳን የዕውቀት ብርሃንን እንደሚሰጣቸው ተገልጧል፡፡
፨     እግዚአብሔር ከጥበቡና ከጥልቅ ፍቅሩ የተነሣ ልጆቹን ለመገሠፅና ከእርሱ ጋር እንዲታረቁ ለማድረግ ግዑዛን ፍጥረታት እንኳን እንደሚጠቀም ተገልጧል፡፡ ለምሳሌ፡- መርከቢቱ ያናውፅ ዘንድ የተላከው ጽኑ ንፋስ፣ ዮናስን የዋጠው ዓሣ አንበሪ፣ ዮናስ ዋዕየ ፀሐይ እንዳይመታው የበቀለችው ቅል፣ ቅሊቱን እንዲበላ በማግሥቱ የታዘዘው ትል እግዚአብሔር ከዮናስ ጋር ለመታረቅ የተጠቀመባቸው ፍጥረታት ናቸው፡፡ ዛሬስ እግዚአብሔር በምን ዓይነት መንገድ እየጠራን ይኾን?

9. መስከረም ፳፭

የተሣተፉ

1. ፌቨን 9/9

2. ኤልሳቤጥ 9/9

3. ሜላተወርቅ 9/9

4. ፍሬው 8/9

5. ዮሐንስ 8/9

6. ያሬድ 9/9

7 አቤል 9/9

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
223 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 10:55:32 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

ትንቢተ ዮናስ ጥያቄ

1. ዮናስ ማለት ምን ማለት ነው

2. ነቢዩ ዮናስ ነገዱ ከነገደ ___ ወገን ነው

3. የነቢዩ ዮናስ አባት እና እናት ስም ጻፉ

4.ነቢዩ ዮናስ በአገልግሎት የነበረበት ዘመን____ ዘመነ መንግሥት ነው

5. ትንቢተ ዮናስን የጻፍው ቅዱስ አባት ማን ይባላል

6. ትንቢተ ዮናስ ስንት ምዕራፎች አሉት

7. አከፋፈሉ እንዴት ነው

8. ከትንቢተ ዮናስ ምን እንማራለን

9. ነቢዩ ዮናስ ክብረ በዓል መቼ ነው ጻፉ

መልሱን እስከ ዛሬ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
246 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 10:07:41 #ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ!

"በዝምታ ውስጥ አጢን፤ ትንሽ ተናገር፤ በጥልቀት ተመልከት፣ ስሜትህን ቆጥብ፤ ራስህን ተቆጣጠር፤ ለምላሽ አትቸኩል፤ አጣጥመው፤ ተመሰጥበት፤ እይታህን አንጽበት፤ ምልከታህን አድስበት። የበዛው ዝምታህ እንዳያስረሳህ፣ እንዳያሳንስህ፤ ገደብ አልባው ምላስህም እንዳያጠፋህ፣ እንዳያስገምትህ በአስተዋይ ልቦና፣ በመልካም ስብእና ከልብህ ተጠንቀቅ።"

@meazahaymanot
228 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 10:04:41 እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ (፪)
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናትየ ምስለ ሚካኤል (፪)
218 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ