Get Mystery Box with random crypto!

#ምክር_ለወዳጅ ወዳጄ ሆይ ! 'አገልጋይ ሆነህ ስትታዘዝ አትከፋ። ክርስቶስ የመጣው በባሪያ መ | መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

#ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ !

"አገልጋይ ሆነህ ስትታዘዝ አትከፋ። ክርስቶስ የመጣው በባሪያ መልክ ነውና። እርሱ በጌትነት አርአያ ቢመጣ አይደንቅም ነበር። የዘላለም ጌታ በባሪያ መልክ መምጣቱ ግን ድንቅ ነው። አገልጋይነትን ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ የባረከው ተግባር ነውና ደስ ይበልህ። አንተ የሰው አገር ተሰድደህ ተመችቶህ እንኳ ከፍቶህ ከሆነ ክርስቶስ ግን ወደማይመቸው ወደ ሲና በረሃ እንደ ተሰደደ አስታውስ። አንተ ለምነህ እንጀራ ስታገኝ በእንባ ትጎርሰዋለህ ፣ ክርስቶስ ግን በመስቀል ላይ ተጠማሁ ብሎ ሆምጣጤ እንደ ሰጡት አስብና ትሑት ሁን። አንተ በራስህ መቃብር ስትቀበር ክርስቶስ ግን በተውሶ መቃብር እንደ ተቀበረ እወቅ።"

@meazahaymanot