Get Mystery Box with random crypto!

መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ meazahaymanot — መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ meazahaymanot — መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር
የሰርጥ አድራሻ: @meazahaymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.56K
የሰርጥ መግለጫ

"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡"
"በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"
                 መጽሐፈ ሰዓታት
የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-13 09:22:29 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ዕንባቆም ጥያቄ

1. ዕንባቆም ማለት ምን ማለት ነው

2. ነቢዩ ዕንባቆም የነበረበት ዘመን መቼ ነው

3. ትንቢተ ዕንባቆም ስንት ምዕራፎች አሉት

4. አከፋፈሉ እንዴት ነው

5. ከትንቢተ ዕንባቆም ምን እንማራለን

6. የነቢዩ ዕንባቆም ክብረ በዓል መቼ ነው

መልሱን እስከ ዛሬ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
8 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 08:56:27 #ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ

"አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡ በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሃል። ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው። አንተን ሁለት ነገሮች ይገልጹሃል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው። በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው። ወንዝ ድንጋይ ጥሶ የሚገባው ኃይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው። ሕልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ሕልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም። ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው።"

@meazahaymanot
31 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 08:22:31 #አዲስ_ዝማሬ "ናሁ ንዜኑ"
46 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 08:20:26 ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት ሦስት(፫)
@meazahaymanot
45 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 17:02:14 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ዕንባቆም ጥያቄ

1. ዕንባቆም ማለት ምን ማለት ነው

2. ነቢዩ ዕንባቆም የነበረበት ዘመን መቼ ነው

3. ትንቢተ ዕንባቆም ስንት ምዕራፎች አሉት

4. አከፋፈሉ እንዴት ነው

5. ከትንቢተ ዕንባቆም ምን እንማራለን

6. የነቢዩ ዕንባቆም ክብረ በዓል መቼ ነው

መልሱን እስከ ነገ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
210 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 16:17:41 #ምዕረ_በዘባንኪ

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ /2/ 
በአዚለ ሕፃን /4/ ማርያም ደከምኪ/2/ 

#ትርጉም:-
አንድ ጊዜ በጀርባሽ
አንድ ጊዜ በጎንሽ/2/ 
ሕፃኑን በማዘል /4/ ማርያም ደከምሽ/2/
173 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 15:49:57 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ናሆም ጥናት መልስ

1. ናሆም ማለት መጽናናት ማለት ነው፡፡

2. ነቢዩ ናሆም

3. የነበረበት ዘመንም በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስተምሩናል

4. ሦስት ምዕራፎች አሉት

5. እግዚአብሔር የፍርድና የበቀል አምላክ እንደኾነ /ምዕ.፩/፤

የነነዌ ጥፋት /ምዕ.፪/፤

ለነነዌ ጥፋት ምክንያቱ ምን እንደኾነ /ምዕ.፫

6. ነነዌ በነቢዩ ዮናስ ስብከት ንስሐ ገብታ ነበር፤ እግዚአብሔርም ይቅር ብሏት ነበር፡፡ ነገር ግን ደግማ በደለች፡፡ ዳግመኛ በንስሐ መመለስም አልወደደችም፡፡ በመኾኑም ጠፋች፡፡ የእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ከቋንቋ በላይ ስለኾነ ከኃጢአታችን እንድንመለስ በተለያየ መንገድ ይጠራናል፡፡ በተለያየ መንገድ ይገሥፀናል፡፡ አልመለስ ካልን ግን ቅዱስ እንደመኾኑ ከኃጢአት ጋር ኅብረት የለውም፤ እኛም የዘራነውን እናጭዳለን፡፡

ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ 

         የእግዚአብሔር ትዕግስቱን ና ምሕረት
          የእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ
          የእግዚአብሔር በመንግሥታት ና ሕዝቦች ላይ ያለው የበላይ ተቆጣጣሪነት።

7. ታኅሣሥ ፭

የተሳተፉ

1. ፌቨን 7/7

2. ኤልሳቤጥ 6/7

3. ፍሬው 7/7

4. ዮሐንስ 7/7

5. ሜላተወርቅ 6/7

6. ያሬድ 7/7

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን
165 viewsወንጌለ ዮሐንስ, edited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 14:12:56 ማኅደረ ጥያቄ

#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ጥናት

የትንቢተ ናሆም ጥያቄ

1. ናሆም ማለት ምን ማለት ነው

2. ትንቢተ ናሆምን የጻፈው ቅዱስ አባት ማነው

3. የነበረበት ዘመንም____ ዘመነ መንግሥት ነው

4. ትንቢተ ናሆም ስንት ምዕራፎች አሉት

5. አከፋፈሉ እንዴት ነው

6. ከትንቢተ ናሆም ምን እንማራለን?

7. የነቢዩ ናሆም ክብረ በዓል መቼ ነው

መልሱን እስከ ዛሬ 9:00 ሰዓት በ @mahiderteyak_bot አድርሱን

#ከበጎ_ነገር_ጋር_ተባበሩ
165 viewsወንጌለ ዮሐንስ, 11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 12:02:14 ሊቁ አባ ሕርያቆስ +"+

=>ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል:: አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል:: ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት::

+አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ብየ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብደኛል:: ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን 4ኛው: ወይ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል::
+ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው:: ገና ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን: የዋህና ገራገር ነበረ:: መቼም እመቤታችን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን:: ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ: ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ::
+የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር:: ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም:: የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ::
+ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው:: ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን: አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር::
+በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ: መላልሶ ያመሰግንበት ነበር:: ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝ. 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር:: ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው:: የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው::

+አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ: ቁሞም ተቀምጦም: ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቁዋረጥ ይላት ነበር:: እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር:: በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ::
+ምንም አለመማሩ ቢያሰጋችቸውም "በጸሎቱ: በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል" ብለው ሾሙት:: ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት: ይንቁትም ነበር:: እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው: እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር::

+አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::

+በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር::
+"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::
+የሚገርመው ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር:: እመቤታችን አነጋገረችው: ባረከችው:: ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ: ምግብም ሳይበላ: እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ1 ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል::
+በሁዋላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በሁዋላም አንድ ፈተና ገጠመው:: አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት 1 ቀን ቅዳሴ "ማን ይቀድስ" ሲባል ሰዎቹ "አባ ሕርያቆስ ይሁን" አሉ::
+እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም: እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ" አላቸው:: "አይሆንም" ብለው እርሱኑ አስገቡት:: ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር:: ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ እርሱ "እግዚእን (የጌታ ቅዳሴን) ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት::

+ይህንን ያሉት እርሱ የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው:: እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት:: አባ ሕርያቆስ ግን እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ:: ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን: መገፋቴን ተመልከች" አላት::
+ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ ቀጸበችው (ጠራችው):: በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው:: ደጉ ሰው ደስ ብሎት "ጐሥዐ ልብየ" ሲል 2ቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ:: እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው::

+ሕዝቡና ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ: አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ:: ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ መካከል ድውይ ፈወሰበት:: እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ::
+መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር 1 ሊቅ ሆነ:: ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ (10,000) ናቸው:: ሊቁ እንዲህ በንጹሕ ተመላልሶ ዐርፏል:: ይህቺ ቀን ለቅዱሱ የልደቱና ዕረፍቱ መታሰቢያ ናት::
ከቅዱሱ ረድኤት በረከት ያካፍለን በጸሎቱ ይማረን
178 viewsNeway Yemaryam, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 12:02:02
ታላቁ ሊቅ እና የእመቤታችን ወዳጅ አባ ሕርያቆስ
153 viewsNeway Yemaryam, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ