Get Mystery Box with random crypto!

አምላካችን ሆይ አምላክ ሆይ ልጆችህን አስበን(2) በክንፈ ረድኤትህ በረከትን ስጠን በምህረት እ | መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

አምላካችን ሆይ አምላክ ሆይ
ልጆችህን አስበን(2)
በክንፈ ረድኤትህ በረከትን ስጠን
በምህረት እጆችህ ጸጋህን አብዛልን (2)

ዓለም በወጥመዷ አምላክ ሆይ
ስባ እንዳትጥለን ''
ምራን ጌታችን ሆይ "
ከኃጢያት አድነን
የሰይጣን ምትኮኛ
ሆነን እንዳንቀር
የሰላም ባለቤት
በህይወታችን ኑር
እኛ ኃጥአን ነን አምላክ ሆይ
አንተን የበደልን "
መብራትና ዘይት "
የሌለን በእጃችን "
እባክህ ጌታ ሆይ
ከደጅ አታስቀረን
የጅህ ሥራዎች ነን
አቤቱ ራራልን
ምንም ብዙ ቢሆን አምላክ ሆይ
እዳ በደላችን "
ከፊትህ ለመቆም "
መልካም ግብር ባይኖረን
ስለ ቅዱሳኑ
ስለተመረጡ
ከጥፋት አድነን
ሰውረን ከእሳት

@meazahaymanot