Get Mystery Box with random crypto!

ማኅደረ ጥያቄ የትንቢተ ዮናስ መልስ 1. ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው፡፡ 2.ነቢዩ ዮናስ ነ | መዓዛ ሃይማኖት የበጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር

ማኅደረ ጥያቄ

የትንቢተ ዮናስ መልስ

1. ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው፡፡

2.ነቢዩ ዮናስ ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ወገን  ነው

3. አባቱ አማቴ እናቱም ሶና ይባላሉ፡፡ 

4. ነቢዩ ዮናስ በአገልግሎት የነበረበት ዘመን በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ሲሆን  ከ፰፻፳፭ እስከ ፯፻፹፬ ቅ.ል.ክ. ገደማ  ነው፡

5. ነቢዩ ቅዱስ ዮናስ

6. አራት ምዕራፎች

7. ምዕራፍ አንድን ስናነብ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ኼዶ እንዲያስተምር እንደታዘዘና 
ምዕራፍ ኹለትን ስናነብ ነቢዩ ዮናስ ወደ ባሕሩ ሲጣል ዓሣ አንበሪእንደተቀበለውና በከርሡም ሦስት ሌሊትና ሦስት መዓልት እንደተሸከመው
ምዕራፍ ሦስትን ስናነብ ዓሣ አንበሪው ነቢዩ ዮናስን እንደተፋውና ወደ ነነዌ እንደኼደ የነነዌ ሰዎችም በዮናስ የንስሐ ጥሪ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንተመለሱ
ምዕራፍ አራትን ስናነብ ደግሞ ነነዌ እንደዳነችና እግዚአብሔርም ዮናስን በአስደናቂ ጥበቡ የውስጥ ሰላሙን እንደመለሰለት

8. ትንቢተ ዮናስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅና የማይለካ ፍቅር የተገለጠበት መጽሐፍ ነው፡፡ በመጽሐፉ እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይኾን የኹሉም አምላክ እንደኾነ ተገልጧል፡፡ የሕዝብም የአሕዛብም ሠራዒና መጋቢ እንደኾነና የኹሉም ድኅነትን እንደሚሻ ተመልክቷል፡፡
፨     በመጽሐፉ የነቢዩን ድካም ተገልጧል፤ ይኸውም ነቢያት እንደኛ ሰዎች እንደነበሩና ድካም እንደነበረባቸው ግን ደግሞ እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጥበቡ ድካማቸውን ለታላቅ ተልእኮ እንደተጠቀመበት ተጽፏል፡፡
፨     እግዚአብሔር ከአእምሮ በላይ ጠቢብ እንደኾነ፣ ፈጣሪን አያውቁም ተብለው ለሚታሰቡ እንደ መርከበኞቹ ላሉ ሰዎች እንኳን የዕውቀት ብርሃንን እንደሚሰጣቸው ተገልጧል፡፡
፨     እግዚአብሔር ከጥበቡና ከጥልቅ ፍቅሩ የተነሣ ልጆቹን ለመገሠፅና ከእርሱ ጋር እንዲታረቁ ለማድረግ ግዑዛን ፍጥረታት እንኳን እንደሚጠቀም ተገልጧል፡፡ ለምሳሌ፡- መርከቢቱ ያናውፅ ዘንድ የተላከው ጽኑ ንፋስ፣ ዮናስን የዋጠው ዓሣ አንበሪ፣ ዮናስ ዋዕየ ፀሐይ እንዳይመታው የበቀለችው ቅል፣ ቅሊቱን እንዲበላ በማግሥቱ የታዘዘው ትል እግዚአብሔር ከዮናስ ጋር ለመታረቅ የተጠቀመባቸው ፍጥረታት ናቸው፡፡ ዛሬስ እግዚአብሔር በምን ዓይነት መንገድ እየጠራን ይኾን?

9. መስከረም ፳፭

የተሣተፉ

1. ፌቨን 9/9

2. ኤልሳቤጥ 9/9

3. ሜላተወርቅ 9/9

4. ፍሬው 8/9

5. ዮሐንስ 8/9

6. ያሬድ 9/9

7 አቤል 9/9

ለተሣተፉት ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን