Get Mystery Box with random crypto!

Loserpool (ሼባዎቹ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ liverpool4321 — Loserpool (ሼባዎቹ) L
የቴሌግራም ቻናል አርማ liverpool4321 — Loserpool (ሼባዎቹ)
የሰርጥ አድራሻ: @liverpool4321
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
➟ @atsbaha12
➟ @YNWA_97

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 324

2022-05-13 19:09:48 የየትኛው ክለብ ደጋፊ ናችሁ የክለባችሁን ቻናል በመምረጥ ተቀላቀሉ
844 views ᴊᴏʙᴇʀ𝘴_የኪዲ ✞, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:05:06
ለትውስታ!

እነዚ ተጨዋቾች የክለባች ተጨዋች እንደነበሩ ያውቃሉ?

@liverpool4321 @liverpool4321
2.4K views Ⓥ︎Ⓐ︎Ⓝ︎ 🅜︎🅔︎🅢︎🅢︎🅘︎ , 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 17:50:54
ቶማስ ቱሄል የቼልሲው አሰልጣኝ፦ "በአሁኑ ሰአት ከአለማችን ምርጥ አሰልጣኞች እና ቡድኖች አንዱን ነው እየገጠመን ያልነው...እናም ለመፋለም ዝግጁ ነን"

@liverpool4321 @liverpool4321
2.5K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, 14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 17:39:28
#በዚህች_ቀን ከ 5 አመት በፊት በአንፊልድ ብራይተንን 4-0 ባሸነፍንበት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ አንዲ ሮበርትሰን ለክለባችን የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጠረ። ቀሪዎቹን ጎሎች ፣ ሞ ፣ ሎቭረን እና ሶላንኬ ከመረብ አሳርፈዋል።

@liverpool4321 @liverpool4321
2.5K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, edited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:54:55
ክሎፕ ከነገው ጨዋታ በፊት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።

ክሎፕ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን በማሸነፍ ላይ፦

"ያለ ጥርጥር የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ማሸነፍ እንፈልጋለን። ይህንን ክብር ከ2006 ጀምሮ አላሳካነውም ቼልሲ 3-4 ጊዜ አሳክቶታል ስለዚህ እኛ ዋንጫውን እንፈልገዋለን። ለማሸነፍ በጣም እንሞክራለን"

ክሎፕ ስለ ኤፍኤ ካፕ ዋንጫ ትልቅነት፦

"ኤፍኤ ካፕ የአለማችን ትልቁ የቤት ውስጥ ውድድር ነው። ይህ ውድድር ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ መረዳት ይቻላል"

ክሎፕ ኤፍኤ ካፕ ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ፦

"የኤፍኤ ካፕ ፍፃሜ ለእኔ ልዩ ግጥሚያ እና ለአንዳንዶች ደግሞ በስራው ትልቅ ውድድር ነው። እየተዝናናን ለደጋፊዎቻችን ድሉን ማብሰር እንፈልጋለን"

ክሎፕ፦ "ይህንን እድል በጉጉት እየጠበቅን ነው። እናም ለእኛ በጣም ትልቅ ፍፃሜ ነው የዚህ ውድድር አካል በመሆኔ ደስተኛ ነኝ"

ክሎፕ፦ "ከዚህ በፊት ለፍፃሜ ለመድረስ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ነበር ግን አልተሳካልንም። በግልፅ ስትጓዝ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ሊኖርህ አይችልም"

ክሎፕ ስለ ቼልሲ፦

"ይህ ከቼልሲ ጋር የሚደረግ ጨዋታ እና ግጥሚያ ፍፁም የተለየ ነው። ቼልሲ የተደራጀ እና በሁሉም ሜዳ የጠራ ሀሳብ ያለው ምርጥ ቡድን ነው። እነሱ በተከላካይ የተደራጁ ቡድኖች ናቸው። እና ቼልሲ እንዴት እንደሚጫወት የምናውቀው ትክክለኛ ነገር የለንም። ብዙ አማራጮች አሉን አንዳድ ጊዜ ሲጫወቱ ከአንዳድ ክለቦች ጋር ተመሳሳይ ስታይ አላቸው። ግን እነሱ በተለየ ጥራት ነው ሚጫወቱት"

@liverpool4321 @liverpool4321
1.1K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, 12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:39:52
የ2021/22 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ይፋ ሲሆኑ ከክለባችን ትሬንት የአመቱ ምርጥ በመባል በእጩነት ቀርቧል።

 ለአርኖልድ ድምፅ ይስጡ
https://www.premierleague.com/news/2612178
1.2K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:03:02
ክሬግ ፓውሰን ነገ በዌምብሌይ ከቼልሲ የምናደርገው የኤፍኤ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ተረጋግጧል።

@liverpool4321 @liverpool4321
1.6K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, edited  12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:59:00
ናቢ ኬይታ፡-

"የስኮውስን አክሰንት (የሊቨርፑል ከተማ አክሰንት)ን እወደዋለሁ! ናቢ ላድ ይሉኛል። ያንን ስም ወድጄዋለሁ!"

@Liverpool4321
@Liverpool4321
1.6K viewsαհตҽժ, edited  11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:50:53
ቲሞ ወርነር ስለ የርገን ክሎፕ፡-

"እሱ በጀርመን ካሉን ምርጥ አሰልጣኞች አንዱ ነው። የኛን ስራ አስኪያጅ ለማጣጣል ሳይሆን ባለፉት አመታት ብዙ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እሱ በጣም ጥሩ ባህሪ አለው ፣ ይህ የጀርመን ሰዎች የሚወዱት ስብዕና ነው። ምክንያቱም እሱ አስደሳች ይመስላል። ጀርመኖች እንደ ቶማስ ሙለር እና የርገን ክሎፕ ያሉ ዓይነት ሰዎችን ይወዳሉ ርኅራኄ አላቸው ፣ እነሱ የሚያስቡትን ይናገራሉ ፣ እና በዚህ ንግግር ውስጥ ሌላ ነገር አለማሰብ በጣም አስፈላጊ ነው። ላይፕዚግ በነበርኩበት ጊዜ ወደ ፕሪምየር ሊግ የመምጣት እድል ነበረኝ። ሊቨርፑሎችም በሃሳቤ ውስጥ ነበሩ እናም ለእኔ ትልቅ እድል ነበሩ ፣ ግን በመጨረሻ ለቼልሲ ለመፈረም ወሰንኩ እና ባለፈው አመት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፌያለሁ። ከሁሉ የከፋው ውሳኔ አልነበረም"

@liverpool4321 @liverpool4321
1.7K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 14:24:23
ክሎፕ፦ "በዚህ ታላቅ የውድድር ዘመን ካልተደሰትክ ልረዳህ አልችልም።"

@liverpool4321 @liverpool4321
1.8K viewsMOHAMMED LIVERPOOL, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ