2022-12-26 21:15:27
ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ሂዳትን ለማስፈን ቁርጠኛ መሆናቸውን መምህራን ገለጹ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካ ወረዳ12 ኮሙኒኬሽን፦ ታህሳስ17/2015ዓም
በየካ የወረዳ12 አስተዳደር የሚገኙ ት/ቤቶች መምህራን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በወረዳው የሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች ከመምህራን ጋር በተደረገው ውይይት ትምህርት ቤቶች የዕውቀትና የክህሎት ማበልጸጊያ ተቋማት መሆናቸውን የገለፁት መምህራኑ ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማወክ የተደረጉ ሙከራዎች መምህራንና ተማሪዎችን የማይወክሉ የጽንፈኞች ተልኮ የነበረና በሁሉም ርብርብ መክሸፋን ተናግረዋል።
በዚህም መምህራን ትምህርት ቤቶችን የዕውቀት፣ የስነምግባርና የክህሎት ማበልጸጊያ ተቋማት በማድረግ የነገ አገር ተረካቢ ትውልድን የሚፈጠርበት በመሆናቸው በቀጣይ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል በሙሉ ዝግጅትና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የክ/ከተማና የወረዳው አመራሮች የተገኙ ሲሆን በየካ ክ/ከተማ የወረዳ12 የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አድስ ዘውዴ ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት አስጠብቆ ማስቀጠል ለማንም የማይተው የሁላችንም ድርሻ ነዉ ሲሉ በውይይቱ ላይ ለተሳተፋ በወረዳው ከሚገኙ ሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች መምህራን አሳስበዋል። በመቀጠልም ሰላም የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም የየግል ሚናችንን በመወጣት ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደቱ ሳይቆራረጥ ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።
በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ መምህራንም ተልኳቸውና ስራቸው ትውልድን መቅረጽ በመሆኑ የፖለቲካ ነጋዴዎችን ሴራ ባለማስተናገድ ት/ቤቶች የዕውቀት ማዕከላት እንዲሆነ እንሰራለን ብለዋል። ለዚህም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርዓቱን ለማስቀጠል ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ህብረብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን መሰረት ያደረገ አንድነትን በማጎልበት መምህራን ለተማሪዎቻቸው ምሳሌ በመሆን ት/ቤቶች ያላቸውን ድርሻና ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አጠቃላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።
69 views18:15