Get Mystery Box with random crypto!

ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kotebebirhanehiywotschool — ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kotebebirhanehiywotschool — ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @kotebebirhanehiywotschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 481

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-01-25 06:47:13
172 views03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:45:22
316 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:45:22
260 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:09:40 እናመሰግናለን
በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራው የከተማችን ካቢኔ እናመሰግናለን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባዉ በአዲሱ እና ብዝሃ ቋንቋን ማዕከል ባደረገዉ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ስርዓት ላይ በመወያየት የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሰጠው አስተያየት መሠረት በማድረግ ባለፉት ጊዜያት ሲያስጠናው የቆየዉን እና ለከተማ አስተዳደሩ ት/ት ቤቶች የሚሆን የብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ባጠረ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ይፋ አድርጓል!

ለዜጎች ማሰብ፣ ህዝብን ማድመጥ እና ፈጣን ምላሽ መስጠትን በተግባር አሳይታችኋልና በድጋሚ እናመሰግናለን
113 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 09:10:18 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከብዘሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዘሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔው በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ )ቋንቋ እንዲሰጥ

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ

4ኛ:- ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች አረብኛና ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፡፡

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን

6ኛ:- በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የስራ እና ቴክኒክ ትምህርት በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ በሚያስቀምጠዉ መስረትና ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና በተጠናው ጥናት መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ

7ኛ:- የግል ት/ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ 250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል።
155 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 20:06:51
79 views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 15:31:33 ውድ የትምህርት ቤታችን መ/ራን ሰራተኞችና ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

በዓሉ ሠላም፣ ፍቅር እና ደስታ በቤታችን የሚሞላበት በዓል እንዲሆንልንና በከተማ ደረጀ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የምናስፈትናቸውና በተቋማችን የሚፈተኑ
ተማሪዎቻችን ውጤት ከፍ አድርገን የምናጠናቅቅበት ዓመት እንድሆን እንመኛለን!!
መልካም የገና በዓል ይሁንልን!
173 viewsedited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 23:11:10
31 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 11:55:41
65 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 06:32:05 ትምህርት ቤቶች የበጎ ስራ ተሳትፏቸውን ቀጥለዋል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የካ ወረዳ12 ኮሙኒኬሽን፦ ታህሳስ27/2015ዓም

በየካ የወረዳ12 አስተዳደር ስር የሚገኙ የግልና የመንግስት ት/ቤቶች የገና በዓልን ተከተሎ የሚደረገውን የበጎ ስራ በማካሄድ የማዕድ ማጋራት በማድረግ አርዓያነታቸውን እየገለጹ ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በትናንትናው ዕለት የኖኤል አንደኛ ደረጃ የግል ት/ቤት ለገና በዓል የማዕድ ማጋራት ማድረጉ የሚታወስ ነው። ይህ ተገባር በዛሬው ዕለትም በኮተቤ ብርሃነ ህይዎት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና ሰራተኞች ከኪሳቸው ግምቱ ከ20,000 ብር በላይ የሚገመቱ የበዓል ግብዓቶችን በመግዛት አቅመደካማ ለሆኑ የት/ቤቱ የተማሪ ወላጆች ማዕድ አጋርቷል።

በየካ የወረዳ12 ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢዶሳ ፈቃዱ እንደገለጹት ት/ቤቶች ከመደበኛ መማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ የበጎነት ስራ በመስራት ዓርዓያ በመሆናቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል። አያይዘውም የማዕድ ማጋራት ስራችን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ በጎ ተግባር በመሆኑ የኮተቤ ብርሃነ ህይዎት ት/ቤት የፈጸመውን በጎ ተግባር ተስፋፍቶ በሌሎች የት/ት ተቋማትም መቀጠል የሚገባው ነው በማለት ምስጋናቸውን ለመምህራኑና ለሰራተኞች አቅርበዋል።

የት/ት ቤቱ ርዕሰመምህር አቶ ዘሪሁን እንደገለጹት አቅመ ደካማ የሆኑ የተማሪ ወላጆችን በመለየት በመምህራኑና ሰራተኞች በጎ ፈቃድ የገና በዓልን አስመልክቶ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
80 views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ