Get Mystery Box with random crypto!

ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kotebebirhanehiywotschool — ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kotebebirhanehiywotschool — ኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @kotebebirhanehiywotschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 481

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-05 21:37:09
ቀን 26/8/2015 ዓ.ም

አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የግብረገብ (Barnoota safuu )ትምህርት ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ በመተርጎም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የትርጉም ስራው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላለው የትምህርት እርከን የተዘጋጀውን የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍ፤የመምህር መምሪያ እንዲሁም መርሀ ትምህርቱን የሚያካትት መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዜግነት ትምህርት ባለሙያው አቶ መለሰ ዘለቀ ገልጸው በትርጉም ስራው ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው የእንግሊዘኛ እና ሲቪክስ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

አቶ መለሰ አክለውም የግብረገብ ትምህርት መጽሀፍ የመተርጎም ስራው ሲጠናቀቅ በየደረጃው ከመምህራን እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት የሚስተካከሉ ሀሳቦች ተካተው ወደህትመት እንደሚገባ ጠቁመው በአዲስ አበባ በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች የግብረገብ ትምህርት(Barnoota safuu ) እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:


TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
123 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 18:03:57 በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የግብረገብ መሰጠት ይጀመራል ፡፡
አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በእንግሊዘኛ ቋንቋ  የተዘጋጀውን የግብረገብ ትምህርት ወደ አማርኛ ቋንቋ እና  አፋን ኦሮሞ በመተርጎም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የትርጉም ስራው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላለው የትምህርት እርከን የተዘጋጀውን የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍ፤የመምህር መምሪያ እንዲሁም መርሀ ትምህርቱን የሚያካትት መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ገልጸው በትርጉም ስራው ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተመረጡና ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው የእንግሊዘኛ እና ሲቪክስ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም የግብረገብ ትምህርት መጽሀፍ የመተርጎምም ሆነ ከአዲስ አበባ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማስማማት ስራው ሲጠናቀቅ በየደረጃው ከመምህራን እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት ብቃቱ ተረጋግጦ ወደህትመት እንደሚገባ በመግለጽ በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የግብረገብ ትምህርት እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡
119 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 06:21:07
124 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:19:13 ስድስት የፈጣራ ሃሳብ የማዳበሪያ መንገዶች

1ኛ፦እንደሚቻል እመን፦አንድን ነገር ለማድረግ እንደምትችል ስታምን አዕምሮህ ተግባራዊ የምታደርግባቸውን መንገዶች ትፈልጋለህ። በመፍትሔ ማመን ወደ መፍትሄ ያደርሳል። "የማይቻል ነው"የማይሆን ነው" ምንም ጥቅም የለውም"የሚሉ ቃላትን ከአስተሳሰብ ውስጥ አስወግድ።

2ኛ፦በዘልማድዊ አሰተሳሰብ እንዳትተበተብ፦ለአዳዲስ ሀሳቦች ክፍት ሁን። አዳዲስ አማራጮችንና መንገዶችን ሞክር።በምትሠራው ነገር ሁሉ መሻሻልን አልም።

3ኛ፦በየእለቱ ራስህን እንዴት ነው ላሻሽለው የምችለው?ብለህ ጠይቅ፦ራስህን ለማሻሻል ምንም ገደብ የለም።ራስህን ስትጠይቀው መልሶች ይጎርፉልሀል።ሞክርና እይ

4ኛ፦ራስህን ከዚህ በበለጠ እንዴት ልሠራ እችላለሁ?ስትል ጠይቀው፦

ብቃት ማለት አሰተሳሰብ ስሆን የበለጠ መሥራት እንደት እንደሚቻል ራስህን መጠየቅ አዕምሮህ በአጭር ጊዜ በቅልጥፍና በርካታ ሥራ ማከናወን የሚያስችሉህን ዘዴዎች እንዲፈልግ ያደረገዋል።

5ኛ፦የመጠየቅና የማዳመጥ ባሕል ይኑርህ፦ስትጠይቅና ስታዳምጥ ከምርጥ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችልህን ግብዓት ያሰገኝልሃል።ታላቅ ሰዎች ማዳመጥ የሚያዘወትሩ ሲሆኑ ትንንሽ ሰዎች ደግሞ ማውራት የሚያበዙ መሆኑን አስታውስ።

6ኛ፦የአዕምሮህን አድማስ አስፋው፦ከተለያዩ ሰዎች ጋር መገናኘትና ሐሳቦችን በመለዋወጥ ራስህን አነቃቂ።

መልካም ሀሙስ ተመኘሁላችሁ::
36 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:59:54 በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ይሰጣል:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን) ሚያዚያ 19/2015 ዓም

በመዲናዋ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ በሆነው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ቢሮው ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎችን በስነ-ልቦና ከማዘጋጀት ባሻገር በትምህርት ቤቶች ቅዳሜና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የተማሪዎችን ስነ-ልቦና ለማዘጋጀት የሚያግዝ የሞዴል ፈተና መሰጠቱን ጠቅሰው፤ በፈተናው አበረታች ውጤት ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ተጨማሪ የሞዴል ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ነው የተናገሩት፡፡

ይህን ተከትሎ ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ዶክተር ዘላለም የገለጹት።

የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ለመውሰድ 75ሺህ 102 ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር በቂ ዝግጅት መደረጉን  ገልጸው በመጀመሪያ ዙር የሞዴል ፈተና ወቅት ኩረጃ እንዳይኖር የሚያስቸሉ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ የስምንተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 19 እና 20 ቀን 2015 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ 78ሺህ 78 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
46 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 06:13:55
ቀን 19/8/2015 ዓ.ም

"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው ዓመት በኹለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡


ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን አብራርተዋል።


ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡


በመጨረሻም በ2016 የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!


You Tube:



TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau


Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
66 views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 05:00:24 General Science second semester First model answer for G8 hare for your friends
@ShewaferaGetaneh
@ShewaferaGetaneh
@ShewaferaGetaneh
75 views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 07:38:33
ቀን፡ 18/08/2015 ዓ/ም

ማስታወቂያ

በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ ለተከታተይና ርቀት ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ

በተከታታይና ርቀት ትምህርት በማታ እና ቅዳሜና እሁድ ለምትማሩ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም በቀን 21/08/2015 እና 22/08/2015 ዓ.ም በሁሉም ካምፓሶች ትምህርት የማይኖር መሆኑን እየገለጽን፤ በተጠቀሱት ቀናት ለተቃጠሉት የትምህርት ክፍለ ጊዜያት ወደፊት ማካካሻ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት
117 views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 06:44:22
113 views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 16:41:24 ዛሬ ፊርማ ያልፈረማችሁ መ/ራን ማለትም የስብሰባውን ነገ አቴንዳንሱ 2:30 ላይ ስለሚላክ ተገኝታችሁ መፈረም ይኖርባችኃል ሲል ት/ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል።
141 viewsedited  13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ