2023-04-15 08:56:00
" ሁሉን የያዘውን ያዙት : ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት: የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት : በቁጣ ጎተቱት : በፍቅር ተከተላቸው : በሚሸልተው ፊት እንደማይነገር እንደ የዋህ በግ በኃላቸው እየተከተለ ወሰዱት ::
ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊት የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት : ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጢአተኛ አሉት ::
በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት ::
ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጀውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት ::
ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት ::
የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ ::
ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው ?
ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው "
መጽሐፈ ቅዳሴ
86 views05:56