Get Mystery Box with random crypto!

Konso News

የቴሌግራም ቻናል አርማ konsonews — Konso News K
የቴሌግራም ቻናል አርማ konsonews — Konso News
የሰርጥ አድራሻ: @konsonews
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.30K
የሰርጥ መግለጫ

በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ አስተያየቶቻችሁን ላኩልን፡ konsonews@gmail.com

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-20 08:27:09 ስለ አካል ጉዳተኞች በኮንስኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ በደቡብ ራድዮ የቀረበ መርሃ ግብር
357 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 08:22:31
359 views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 21:45:53 የዕለተ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡

1. በሐዋሳ የሚኖሩ የኮንሶ ተወላጆች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 18 ኩንታል የበቆሎ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ

2. በኮንሶ ዞን የመጀመሪያው የአካል ጉዳተኞች ማበልጸጊያ ማህበር መቋቋሙ ተገለጸ

3. አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ከዛሬ ጀምሮ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ

4. የብሪታኒያ ንግስት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ የቀብር በዛሬው ዕለት በልዩ ክብር ተከናወነ
361 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 11:08:52 የዕለተ ሐሙስ መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡

1. በኮንሶ ዞን የሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ

2. “አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው

3. የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተገለፀ

4. የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው ተባለ
606 views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 12:00:30 የዕለተ ረቡዕ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡

1. “ኮንሶን እናስተዋውቅ” በሚል መሪ ሐሳብ በዘመን መለወጫ ቀን የተዘጋጀው የቁንጅናና ባህልን የማስተዋወቅ ውድድር በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ

2. በብልፅግና ጉባዔ፣ ዕጩ ተመራጭ አስመራጭ ሆኖ መሰየሙ ትክክል እንዳልነበር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

3. ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈፀሙ
578 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 16:59:10 ሕወሐት ለሰላም እደራደራለሁ እያለ ነው። እኛም እንደ ዜጋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ድሉን እያረጋገጠ ሰላሙን እያጸና መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት የሚከተሉት ተግባራት እንዲያከናውን እንደ ሕዝብ ግፊት ማድረግ አለብን።

1. የትግራይ ክልል ለሀገራችን ጠላቶች የመግቢያ በር መሆኑ ሊያበቃ ይገባል። ለሰላም እየተባለ የመከላከያ ኃይላችንን ከትግራይ ሙሉ በሙሉ በማስወጣታችን የአየር ክልላችንን ለመጠበቅ አልቻልንም። በተደጋጋሚ የአየር ክልላችን መጣሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የሌሎች ሀገሮችን የአየር ክልል ትጠብቅ የነበረች ሀገር ዛሬ በአሸባሪው ሕወሐት ምክንያት የራሷን የአየር ክልል ለመጠበቅ መቸገሯ አሳዛኝ ነው። የአየር ክልልን መጠበቅ ደግሞ ለፌዴራል መንግሥት የተሰጠ ኃላፊነት ነው። በሰሜን በኩል የአየር ክልላችንን ለመጠበቅ እንዲቻል የመከላከያ ኃይላችን በትግራይ ክልል ወታደራዊ ቤዙን እንደቀድሞው አጠናክሮ መቀጠል አለበት። የፌዴራል መንግሥትም ይሄንን ለድርድር ማቅረብ የለበትም ብለን እናምናለን።

2. በሌሎች ክልሎች እንደምናየው የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ዲፖዎች፣ ታላላቅ ተቋማት፣ ግድቦች መጠበቅ ያለባቸው በፌዴራል ፖሊስ ነው። ስለሆነም እነዚህን ተቋማት ፌዴራል ፖሊስ መጠበቅ እንዳለበት መንግሥት ለድርድር ማቅረብ የለበትም።

3.በአንድ ሀገር ሁለት የመከላከያ ሠራዊት እንዲኖር የሚፈቅድ ሕግ በዓለም ላይ የለም። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም አይፈቅድም። ሕወሐት አንድ የፖለቲካ ኃይል እንጂ የታጠቀ አሸባሪ እንዲሆን ሕግም ሞራልም አይፈቅድለትም። አሸባሪው ሕወሐት ዕብሪት በተሰማው ቁጥር ከፍተኛ ጦር እያሠለጠነና እያስታጠቀ ወረራ የሚፈጽምበት ሁኔታ ጨርሶ ማብቃት አለበት። ክልሉ ወታደራዊ ትጥቁን ፈትቶ ለፌዴራል መንግሥት በማስረከብ በሕግ የተፈቀደለት የጸጥታ ኃይል ብቻ ሊኖረው እንደሚገባ መንግሥት ከድርድሩ በፊት መግለጥ አለበት።

4. ሕወሐት ራሱን እንደ አንድ ሀገር መንግሥት ማየቱን እንዲያቆም ሊነገረው ይገባል ብለን እናምናለን። ከሰሞኑ "የትግራይ መንግሥት" እና " የውጭ ጉዳይ ቢሮ" የሚሉት በየመግለጫ የሚያወጧቸው ነገሮች ከሕገ መንግሥታችን ጋር የሚጋጩ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።
የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪው ሕወሐት ትጥቁን ፈትቶ፣ ጦሩን በትኖ እንደማንኛውም የፖለቲካ ኃይል በሰላማዊ መንገድ ችግሩን ለመፍታት ከፈለገ ብቻ ነው መደራደር ያለበት። ከዚያ ውጭ፤ ወደ ውጭ።

https://t.me/mesayesattv
557 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 12:09:14 የዕለተ ሰኞ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡

1. ሄስ ትራቭል ኢትዮጵያ በኮንሶ ዞን በ180 ሚሊዮን ብር የእንቨስትመንት ተቋማት እየገነባ ነው ተባለ

2. ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ

3. የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ

4. ኤምባሲዎች በግቢያቸው ስብሰባ ከማድረጋቸው በፊት ለመንግሥት እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ ተላለፈ
490 views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:27:13
558 views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 20:25:33 የዕለተ ሐሙስ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ልዩ አንኳር ዜናዎች፡

1. የኮንሶ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ መከረ

2. ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ከለከለ

3. ሩሲያ፤ በቁጥጥሯ ስር ባሉ የዩክሬን ግዛቶች በመጪው ህዳር ወር “ህዝበ ውሳኔ” ልታካሂድ ነው

4. አፕል ኩባንያ በአደጋ ወቅት ኔትዎርክ ከሌለበት ስፍራ በሳታላይት አማካይነት መልዕት የሚልክ አይፎን 14 የተሰኘን ይፋ አደረገ
663 views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ