Get Mystery Box with random crypto!

ሕወሐት ለሰላም እደራደራለሁ እያለ ነው። እኛም እንደ ዜጋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ድሉን እያረጋገጠ | Konso News

ሕወሐት ለሰላም እደራደራለሁ እያለ ነው። እኛም እንደ ዜጋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ድሉን እያረጋገጠ ሰላሙን እያጸና መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት የሚከተሉት ተግባራት እንዲያከናውን እንደ ሕዝብ ግፊት ማድረግ አለብን።

1. የትግራይ ክልል ለሀገራችን ጠላቶች የመግቢያ በር መሆኑ ሊያበቃ ይገባል። ለሰላም እየተባለ የመከላከያ ኃይላችንን ከትግራይ ሙሉ በሙሉ በማስወጣታችን የአየር ክልላችንን ለመጠበቅ አልቻልንም። በተደጋጋሚ የአየር ክልላችን መጣሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የሌሎች ሀገሮችን የአየር ክልል ትጠብቅ የነበረች ሀገር ዛሬ በአሸባሪው ሕወሐት ምክንያት የራሷን የአየር ክልል ለመጠበቅ መቸገሯ አሳዛኝ ነው። የአየር ክልልን መጠበቅ ደግሞ ለፌዴራል መንግሥት የተሰጠ ኃላፊነት ነው። በሰሜን በኩል የአየር ክልላችንን ለመጠበቅ እንዲቻል የመከላከያ ኃይላችን በትግራይ ክልል ወታደራዊ ቤዙን እንደቀድሞው አጠናክሮ መቀጠል አለበት። የፌዴራል መንግሥትም ይሄንን ለድርድር ማቅረብ የለበትም ብለን እናምናለን።

2. በሌሎች ክልሎች እንደምናየው የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ዲፖዎች፣ ታላላቅ ተቋማት፣ ግድቦች መጠበቅ ያለባቸው በፌዴራል ፖሊስ ነው። ስለሆነም እነዚህን ተቋማት ፌዴራል ፖሊስ መጠበቅ እንዳለበት መንግሥት ለድርድር ማቅረብ የለበትም።

3.በአንድ ሀገር ሁለት የመከላከያ ሠራዊት እንዲኖር የሚፈቅድ ሕግ በዓለም ላይ የለም። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም አይፈቅድም። ሕወሐት አንድ የፖለቲካ ኃይል እንጂ የታጠቀ አሸባሪ እንዲሆን ሕግም ሞራልም አይፈቅድለትም። አሸባሪው ሕወሐት ዕብሪት በተሰማው ቁጥር ከፍተኛ ጦር እያሠለጠነና እያስታጠቀ ወረራ የሚፈጽምበት ሁኔታ ጨርሶ ማብቃት አለበት። ክልሉ ወታደራዊ ትጥቁን ፈትቶ ለፌዴራል መንግሥት በማስረከብ በሕግ የተፈቀደለት የጸጥታ ኃይል ብቻ ሊኖረው እንደሚገባ መንግሥት ከድርድሩ በፊት መግለጥ አለበት።

4. ሕወሐት ራሱን እንደ አንድ ሀገር መንግሥት ማየቱን እንዲያቆም ሊነገረው ይገባል ብለን እናምናለን። ከሰሞኑ "የትግራይ መንግሥት" እና " የውጭ ጉዳይ ቢሮ" የሚሉት በየመግለጫ የሚያወጧቸው ነገሮች ከሕገ መንግሥታችን ጋር የሚጋጩ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።
የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪው ሕወሐት ትጥቁን ፈትቶ፣ ጦሩን በትኖ እንደማንኛውም የፖለቲካ ኃይል በሰላማዊ መንገድ ችግሩን ለመፍታት ከፈለገ ብቻ ነው መደራደር ያለበት። ከዚያ ውጭ፤ ወደ ውጭ።

https://t.me/mesayesattv