Get Mystery Box with random crypto!

ቅንጭብጭብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ kinchebchabi — ቅንጭብጭብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ kinchebchabi — ቅንጭብጭብ
የሰርጥ አድራሻ: @kinchebchabi
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.26K
የሰርጥ መግለጫ

ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ
እነሆ #ቅንጫቢ
ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።
ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-01-21 20:40:43 #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ግዕዝ_ክብር_ይእቲ
#ዘዘዮሐንስ (አለቃ)

መፈወስ ነፍስ ወይነ ለምንት ኢተኃሥሢ?
ዘታፈቅሪ ነፍስየጨቤተ መያሲ ትጊሢ
ወእንዘ ታነብቢ ዘልፈ ምዕዳነ ዳዊት ነጋሢ
እም እኩይ ግብር ለምንት ኢትትጋኀሢ?
.
.
.
ጠዋት በማለዳ
ወደ ጠጅ አደይ ቤት
የምትገሰግሺ አንቺ የኔ ነፍስ ሆይ!
ከጠጅ የተሻለ
ሕይወት የተሞላ ጥበብ የተሞላ
የሚፈዉስ ወይንን ለምን አትፈልጊም እሱ አይሻልም ወይ?
አዉቃለሁ ታዉቂያለሽ
የንጉስ ዳዊትን
ቅኔዉን ምክሩን ዞትር ታነቢያለሽ
ዞትር ትደግሚያለሽ።
ነገር ግን በተግባር
ወይንን ተጸይፈሽ እዛው ጠጅ ቤት ነሽ
ከማለዳ አንስቶ ጀንበር እስክትሸሽ።
ታዲያ!
ከቶ ምን ዋጋ አለው ቢያዉቁ ቢራቀቁ
ከመፅሐፍ ዉቂያኖስ ጫፍ ድረስ ቢጠልቁ
በሕይወት ካልታየ
የዕዉቀት ወሰኑ የዳዊት ድጋሙ
ጸሎትና ዕዉቀትሽ
ያለ'ካል የሚታይ ረጅም ጥላን ነው ሚሆነው ትርጉሙ
እባክሽ ነፍሴ ሆይ?

ዉርስ ትርጉም
#በኤፍሬም_ሥዩም_ተሰማ

ምንጭ #ተዋነይ_ብሉይ_የግዕዝ_ቅኔያት_ፍልስፍና_ከቀደምት_የኢትዮጵያ_ነገሥታት_እና_ሊቃዉንት

join join join join

@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset

3.0K viewsAman YTZ, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 13:22:24 ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
http://t.me/kinchebchabi
4.0K viewsC-ራክ, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 21:00:51 ሰላም ሰላም ወዳጆች በልዩ መልኩ በሚድያ ልንመጣ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ሰብስክራይብ በማድረግ እንድትከተሉን ጋበዝን

https://youtube.com/channel/UCoYix1CBO2zTpdEbrF1D7Ow
2.9K viewsB Crazy Kid, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 07:01:20 ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት... ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ እንዴት አደርሽ
#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
3.3K views የግማሽ አለም ጣኦት , 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-06 22:09:05 ወፈፍታ


አንድም ወፍ አንድምታ
የአክናፍ ከፍታ፣
የቃል ሽሙንምታ
ሽልብ ሽልብታ፣
ቀልብን የሚሰውር
በጥበብ እርካታ፣

አካልን የሚሰልብ
ሰላቢ ወፈፍታ።

አንድም ወፍ
አንድምታ
እፍ'ታ ወፈፍታ።



ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት




@sufafel
@sufafel
@sufafel
3.0K views የግማሽ አለም ጣኦት , 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-05 21:11:02

እናት ስትረገም
በምጥ በሲቃ ደም፣


የርግማኗ ፍሬ
ከሷ ተፈጥሬ፣


ሌላ ዘር እሻለው...


ዘውትር መፀፀት
በዛች ባንዲቴ ቅፅበት
እናቴ የሳተች ለት።


ሳል'ፈለግ መጣሁ....


መንገድ ልያዝ ደሞ


ጉዞ በጨለማ
ከሱ እኔ ልስማማ።


እ ና ማ....







ሲጥ!!


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
2.7K views የግማሽ አለም ጣኦት , 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-05 14:06:40
ደሞ እንኩ አጭሬ ግጥም!!!

ረድኤት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
2.2K views የግማሽ አለም ጣኦት , 11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-03 20:13:41 ቆይ ግን አንተ ማን ነህ?


የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመንገር በግድ ጆሮው ላይ ተለጥፈው ሲያንሾካሹን ግንርታቸው እያስተጋባ ሲሰማው ያስጨንቀዋል።

ወደዚች በከቻ አለም ፈልጎ እንዳልመጣ ሁሉ ተፈልጎ እንደሚሄድ ለማሳበቅ አፋቸውን ያሾሉ እልፍ የኢብሊስ ወዳጆች አሉ የሁካታቸው ማፍገምገም
የሲቃቸው ሲርሲርታ ለሱ ጥዑም የነፍስ ምግብ ሆኖታል

ነፍሳት ሲቃጠሉና ግግር በረዶ ሰርተው በቁማቸው ጋንድያ ሲሆኑ የሚደሰተው
ሰይጣን ሁሉንም ነፍሳት ተራ በተራ መቅጣቱን ተያይዞታል

እሱም ተራው ደርሶት ግግር በረዶ ውስጥ ነፍሱን ተጣለች

የሲኦልን ሙቀትና ቅዝቃዜ ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና ስቃዩ ሲበዛበት ከሲኦል ለማምለጥ መላ ይዘይድ ጀመር

ከብዙ ጥረትና ልፋት በኃላ ልጁ ከሲኦል ታወጣኛለች ያላትን ሻማ ሰራ
በድቅድቁ ጨለማ በሻማይቱ ብርሀንነት ሶስት እርምጃዎችን ወደፊት ተራመደ
ነገር ግን ጨለማውን ተገን አድርገው የከበቡት ብዙ ነፍሳቶች አሰፍስፈው ነበር ሻማይቷን ሊቀሙት

የተጨነቀች ነፍስ .....

ሻማይቱን ለቀቃት...

ሻማዋንም ለመያዝ እልፍ ነፍሶች ተራኮቱ
ተሻሙባት

እሱግን ሊሻማባት ሊሻቀጥባት አልፈቅድምና አፈገፈገ...
ወደ መጨረሻው ጨለማ ወደሚባለው የሲኦል ክፍል ራሱን አሽቀንጥሮ ጣለ



ከወደቀበት ሲነሳም ሰይጣኑ ለእግዜር ፀሎት የሚያደርስበት የገነት መስኮት ታየችው ወደ መስኮቷ ተጠጋ

"እግዚአብሄር እረኛዬ ነው
በለመለመች መስክ ያሳድረኛል"

የሚለው ፀሎት እውነት መሆኑን አመነ
ያመነውም ሲኦል ውስጥ ሆኖ ነው ያውም ሰይጣኑና እግዜሩ በሚገናኙበት በመስኮታቸው ቀዳዳ ተመልክቶ

ወቅቱ ፀደይ ነበርና የገነት ደጃፎች በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠዋል

ወደ አበቦቹ አማተር
ከአበቦቹ መሀል ግን አይኑ ውስጥ የገቡት ስራቸው አንድ ቅርንጫፋቸው ለየቅል የሆኑትን ዕቡጦች ላይ አይኑ ተተክሎ ቀረ

ያለመታደል እጣ ፈንታዋ ሆነና አንድኛዋ መንታይቱ አበባ ከሰመች

በመክሰሟ ልጁ አዘነ

አንዷ አበባ አበበች
አንድኛዋ ከሰመች

እነሆ ርግብም በአክናፏ አየሩን ቀዝፋ መታ የቆረችጠውን አበባ በማንቁሯ ቀጠፈቻት ቀጥፋትም እሱ ሲኦል ውስጥ ሆኖ በሚያያት መስኮት በኩል በራ አረፈች። በማንቁሯ የያዘችውን አበባ እንዲቀበላት አንገቷን ወሱ ስክክ አድርጋ በተቀመለኝ አይነት ልምምጥ አይን አይኑን ታየዋለች

ይቀበላት ይሆን?

የኑሮን ውትፍትፍ ቀዳዳ መሙላት ባይችል እንኳን ሊሞላ የሚችል ደንዳና ጫንቃ እንዳለው ያወቀችው

ግን እሷ ማን ናት?

ሻማይቱ?
መንትያ አበቦቹ?
ወይስ ርግቢቱ?


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
2.4K views የግማሽ አለም ጣኦት , 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-01 21:29:54 #ፍለጋ

ገጣሚ ሮቤል አለማየው
ዝምተኛው_ሲርሎስ


#አንባቢ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
2.1K views የግማሽ አለም ጣኦት , edited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-31 21:35:13


ከምንጭሽ ውሀ ስር
ለመቅዳት ስታትር፣

አንገቴ ሲል ዘንበል
በደጃፍሽ በኩል፣

ተጠምቼ ስግት
የተፈጥሮን ፍንክት፣


ሰው ሆኖ ሰው መስራት
ነፍሴን ከስጋዬ ነጥለሽ ሰወርሻት።


አወይ መታደልሽ!!

ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel
2.2K views የግማሽ አለም ጣኦት , 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ