Get Mystery Box with random crypto!

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ . . #ግዕዝ_ክብር_ይእቲ #ዘዘዮሐንስ (አለቃ) መፈወስ ነፍስ ወይነ ለም | ቅንጭብጭብ

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
#ግዕዝ_ክብር_ይእቲ
#ዘዘዮሐንስ (አለቃ)

መፈወስ ነፍስ ወይነ ለምንት ኢተኃሥሢ?
ዘታፈቅሪ ነፍስየጨቤተ መያሲ ትጊሢ
ወእንዘ ታነብቢ ዘልፈ ምዕዳነ ዳዊት ነጋሢ
እም እኩይ ግብር ለምንት ኢትትጋኀሢ?
.
.
.
ጠዋት በማለዳ
ወደ ጠጅ አደይ ቤት
የምትገሰግሺ አንቺ የኔ ነፍስ ሆይ!
ከጠጅ የተሻለ
ሕይወት የተሞላ ጥበብ የተሞላ
የሚፈዉስ ወይንን ለምን አትፈልጊም እሱ አይሻልም ወይ?
አዉቃለሁ ታዉቂያለሽ
የንጉስ ዳዊትን
ቅኔዉን ምክሩን ዞትር ታነቢያለሽ
ዞትር ትደግሚያለሽ።
ነገር ግን በተግባር
ወይንን ተጸይፈሽ እዛው ጠጅ ቤት ነሽ
ከማለዳ አንስቶ ጀንበር እስክትሸሽ።
ታዲያ!
ከቶ ምን ዋጋ አለው ቢያዉቁ ቢራቀቁ
ከመፅሐፍ ዉቂያኖስ ጫፍ ድረስ ቢጠልቁ
በሕይወት ካልታየ
የዕዉቀት ወሰኑ የዳዊት ድጋሙ
ጸሎትና ዕዉቀትሽ
ያለ'ካል የሚታይ ረጅም ጥላን ነው ሚሆነው ትርጉሙ
እባክሽ ነፍሴ ሆይ?

ዉርስ ትርጉም
#በኤፍሬም_ሥዩም_ተሰማ

ምንጭ #ተዋነይ_ብሉይ_የግዕዝ_ቅኔያት_ፍልስፍና_ከቀደምት_የኢትዮጵያ_ነገሥታት_እና_ሊቃዉንት

join join join join

@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset