Get Mystery Box with random crypto!

ቆይ ግን አንተ ማን ነህ? የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመ | ቅንጭብጭብ

ቆይ ግን አንተ ማን ነህ?


የማንነት ጥያቄው እየተመላለሰ ሲያቃጭልበት ለፌ ወለፌ ወመሆኑን ለመንገር በግድ ጆሮው ላይ ተለጥፈው ሲያንሾካሹን ግንርታቸው እያስተጋባ ሲሰማው ያስጨንቀዋል።

ወደዚች በከቻ አለም ፈልጎ እንዳልመጣ ሁሉ ተፈልጎ እንደሚሄድ ለማሳበቅ አፋቸውን ያሾሉ እልፍ የኢብሊስ ወዳጆች አሉ የሁካታቸው ማፍገምገም
የሲቃቸው ሲርሲርታ ለሱ ጥዑም የነፍስ ምግብ ሆኖታል

ነፍሳት ሲቃጠሉና ግግር በረዶ ሰርተው በቁማቸው ጋንድያ ሲሆኑ የሚደሰተው
ሰይጣን ሁሉንም ነፍሳት ተራ በተራ መቅጣቱን ተያይዞታል

እሱም ተራው ደርሶት ግግር በረዶ ውስጥ ነፍሱን ተጣለች

የሲኦልን ሙቀትና ቅዝቃዜ ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና ስቃዩ ሲበዛበት ከሲኦል ለማምለጥ መላ ይዘይድ ጀመር

ከብዙ ጥረትና ልፋት በኃላ ልጁ ከሲኦል ታወጣኛለች ያላትን ሻማ ሰራ
በድቅድቁ ጨለማ በሻማይቱ ብርሀንነት ሶስት እርምጃዎችን ወደፊት ተራመደ
ነገር ግን ጨለማውን ተገን አድርገው የከበቡት ብዙ ነፍሳቶች አሰፍስፈው ነበር ሻማይቷን ሊቀሙት

የተጨነቀች ነፍስ .....

ሻማይቱን ለቀቃት...

ሻማዋንም ለመያዝ እልፍ ነፍሶች ተራኮቱ
ተሻሙባት

እሱግን ሊሻማባት ሊሻቀጥባት አልፈቅድምና አፈገፈገ...
ወደ መጨረሻው ጨለማ ወደሚባለው የሲኦል ክፍል ራሱን አሽቀንጥሮ ጣለ



ከወደቀበት ሲነሳም ሰይጣኑ ለእግዜር ፀሎት የሚያደርስበት የገነት መስኮት ታየችው ወደ መስኮቷ ተጠጋ

"እግዚአብሄር እረኛዬ ነው
በለመለመች መስክ ያሳድረኛል"

የሚለው ፀሎት እውነት መሆኑን አመነ
ያመነውም ሲኦል ውስጥ ሆኖ ነው ያውም ሰይጣኑና እግዜሩ በሚገናኙበት በመስኮታቸው ቀዳዳ ተመልክቶ

ወቅቱ ፀደይ ነበርና የገነት ደጃፎች በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠዋል

ወደ አበቦቹ አማተር
ከአበቦቹ መሀል ግን አይኑ ውስጥ የገቡት ስራቸው አንድ ቅርንጫፋቸው ለየቅል የሆኑትን ዕቡጦች ላይ አይኑ ተተክሎ ቀረ

ያለመታደል እጣ ፈንታዋ ሆነና አንድኛዋ መንታይቱ አበባ ከሰመች

በመክሰሟ ልጁ አዘነ

አንዷ አበባ አበበች
አንድኛዋ ከሰመች

እነሆ ርግብም በአክናፏ አየሩን ቀዝፋ መታ የቆረችጠውን አበባ በማንቁሯ ቀጠፈቻት ቀጥፋትም እሱ ሲኦል ውስጥ ሆኖ በሚያያት መስኮት በኩል በራ አረፈች። በማንቁሯ የያዘችውን አበባ እንዲቀበላት አንገቷን ወሱ ስክክ አድርጋ በተቀመለኝ አይነት ልምምጥ አይን አይኑን ታየዋለች

ይቀበላት ይሆን?

የኑሮን ውትፍትፍ ቀዳዳ መሙላት ባይችል እንኳን ሊሞላ የሚችል ደንዳና ጫንቃ እንዳለው ያወቀችው

ግን እሷ ማን ናት?

ሻማይቱ?
መንትያ አበቦቹ?
ወይስ ርግቢቱ?


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።። ።።።።።
t.me/sufafel
t.me/sufafel
t.me/sufafel