Get Mystery Box with random crypto!

ቅንጭብጭብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ kinchebchabi — ቅንጭብጭብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ kinchebchabi — ቅንጭብጭብ
የሰርጥ አድራሻ: @kinchebchabi
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.26K
የሰርጥ መግለጫ

ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ
እነሆ #ቅንጫቢ
ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።
ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-07 13:58:25 ጉዞ ትወዳላችሁ?

በየወሩ አዲስ ቦታ ማየት ትፈልጋላችሁ?

በመላው ኢትዮጵያ አብራችሀለ መጓት ትጀልጋላችሁ?

ከከተማ ግርግር፣ ጫጫታ፣ ከመኪና ጭስ ገለል ብላችሁ ንፁህ አየር መሳብ መተንፈስ ትፈልጋላችሁ?


አሁኑኑ ተቀላቀሉ - በየወሩ በየ15 ቀኑ አዲስ ቦታዎችን እናስጎበኛችኋለን።

@ibexevents
+251945965456

T.me/IbexEvents
304 viewsIbex Photography, 10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 00:18:43 ጉዞ ትወዳላችሁ?

በየወሩ አዲስ ቦታ ማየት ትፈልጋላችሁ?

በመላው ኢትዮጵያ አብራችሀለ መጓት ትጀልጋላችሁ?

ከከተማ ግርግር፣ ጫጫታ፣ ከመኪና ጭስ ገለል ብላችሁ ንፁህ አየር መሳብ መተንፈስ ትፈልጋላችሁ?


አሁኑኑ ተቀላቀሉ - በየወሩ በየ15 ቀኑ አዲስ ቦታዎችን እናስጎበኛችኋለን።

@ibexevents
+251945965456

T.me/IbexEvents
38 viewsB Crazy Kid, 21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 16:13:01 ንጥል ፥ ተጓዥ አዳም
.
ሲራክ ወንድሙ
.
ነብሴ የግጥም ድርድር
ልቤ የ' ዋ ባህር
ስሜ አፈር ገፊ - ኮስታራ ፏፏቴ
አደዬን አክስሜም - አልደርስም ከቤቴ
°°°°°°°°°
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
-------------
https://t.me/kinchebchabi
228 viewsC-ራክ, 13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 12:01:14 ይመስላል ፍለጋ

@siraaq
.

ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
ሲራክ ወንድሙ
https://t.me/kinchebchabi
315 viewsC-ራክ, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 20:49:18 #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#አበባ_አየሁ

ሲራክ ወንድሙ

እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር

አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ

ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።

የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ

የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
ሲራክ @siraaq
https://t.me/kinchebchabi
948 viewsC-ራክ, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 17:25:03
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
"በልቤም ሆነ በአዕምሮዬ አላፈቅርሽም። እንዲያው ምንአልባት ልብም መምታቱን ስለሚያቆም አዕምሮም ስለሚረሳ። በነብሴ አፈቅርሻለሁ። ነብስ በፍፁም አትቆምም ወይም አትረሳምና።"

Rumi

join and share
@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
611 viewsAman YTZ, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 03:16:40 ይህን ለምታዩ ኹሉ ሰላም ይሁን #ሰላም!
#ኢትዮጵያ @Bcrazykid
1.7K viewsB Crazy Kid, 00:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 19:58:06 #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ


#ሰው_ከመሆን_ሰውሩኝ! ፬
.
.
"..ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት ሲባል ሰምቻለሁ፤ ሰው ሆኘ ለሰው ካላዘንኩ ሰው ሆኘ ሰው ሲሞት ከእነገሌ ስለሆን የማይገደኝ ከሆነ ሰው ከመሆን ሰውሩኝ፤ ከሰው ተራ አውጡኝ።"

Unknown
(ከነፃ ሃሳብ ጋዜጣ ላይ የተወሰደ)

join join join join

@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
2.4K viewsAman YTZ, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 22:13:12
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
.
ካሜራ ማን ነኝ..!
ሁሌ ባጋጣሚ በመንገድ ላይ ሳያት
እድልም ብሎልኝ በድንገት ሳገኛት
ስትስቅ ነው ማስተዉላት
ስትስቅ ነው እምቀርፃት
በካሜራየ አይን በአልበም እማሰፍራት
ሰርክ አዲስ ፈገግታዋን በፎቶ ምይዛት
በአካል ግን በቅርበት
አልነካት አላቅፋት..
ዛሬም ከርቀት በጎዳናው ሽር ስትል
ካሜራየን አነጣጥሬ ልክ ልስላት ስል
አይኔን አላመንኩም ፈገግታዋ የለም
መልኳ ደማምኗል ዝም ብላለች ዝም..?!?
.
.
Aman YTZ
@amanYTZ23

join join join join

@YelbeDrset @YelbeDrset @YelbeDrset
3.2K viewsAman YTZ, edited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 21:49:01
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
.
"..አመታት ከሚመስሉ ወር ከማይሞሉ ቀናት በኋላ አየኋት፣ ቀረብኳት፣ የምትተነፍሰዉን አየር እኩል ተነፈስኩኝ፣ ደግሞ እጆቿን ያዝኩ በስስት ተሳለምኩ አክየም አቀፍኳት ትንፋሽ እስከሚያጥራት ከንፈሯን ጎረስኩኝ አንገቷ ስር ገባሁ ጠረኗ አወደኝ! ሰከርኩ! ሰከርኩ! ሰከረኩ! ይባስ ናፈቀችኝ!..ከጎኔ እንዳትርቅ ካይኔ ሰር እንድትኖር ቃልኪዳን አሰብኩኝ..አስቤ አልቀርም..!!

Aman YTZ
@amanYTZ23

join join join join

@YelbeDrset
@YelbeDrset
@YelbeDrset

3.0K viewsAman YTZ, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ