Get Mystery Box with random crypto!

ይመስላል ፍለጋ @siraaq . ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላ | ቅንጭብጭብ

ይመስላል ፍለጋ

@siraaq
.

ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
ሲራክ ወንድሙ
https://t.me/kinchebchabi