Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

የቴሌግራም ቻናል አርማ johnnyaleme — አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨  Johnny aleme
የቴሌግራም ቻናል አርማ johnnyaleme — አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨  Johnny aleme
የሰርጥ አድራሻ: @johnnyaleme
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.88K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 65

2022-08-28 13:09:14 shfenugn yekerewnm edayen kefye netisa sew hogne endmsker erdugn keber Hulu erson listen enatachnen listen le LEUL EGZIABHER yehun kedusan sematatn mlaktat endykebrachem yemsgenu Yene fetono derase enate abate temsgnulgn

=ሰላም ወንድሜ እንዴት አለህ ለአቡነ እጨጌ ዬኃኒስ ያደርጉልኝን መስክርልኝ ሁልጊዜም ጨንቆኝ ነግሬቸው እንደ ቅርብ ጓደኛ ነው ቶሎ ሚሰሙኝ የኔን የሀፄተኛዋን ልመና ፈጥነው ይሰሙኛል በስራ ቦታያ በሂወቴ የነገርኮቸውን ሁሉ ይፈትሉኛል አጥብቄ የለመንኮቸውንም ፈንጭ አስይተውኛል ጨርሰው አስየተውኝ ሙሉውን ታርክ ለመመስከር ያብቀኝ ፡፡የእግዜአብሔር ስሙ የተመሰገና ይሁን አባታችን የሰጠን እነቱ ድንግል ማርያም ቅዱስ ሚካኤል ፈጣኑ መላእክ ምሰጋነ ሚገባቸው መላእክታ ፃድቃን ሰማዕታት ሰማቸው የተመሰገነ ይሁን አሜን

=በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን የአቡነ እጨጌ ዬሐንስ ምስክርነት
ዛሬ እህቴ በረራ ነበራትና አየር መንገድ በጣም አርፍደን ደረስን በዛ ላይ ደግሞ ዋና አስፈላጊ ወረቀት ሳታሟላ ረሳች በዚህም ምክንያት ጉዞዋ ሊስተጓጎል ሆነ እኔም አቡነ እጨጌ ዮሐንስን;እመ ብርሀንን ; አቡነ ቄርሎስን አጥብቄ ተማፀንኳቸው ምስጋናዬ ይድረሳቸውና ሁሉ ነገር መስመር ያዘልን በሰላም ሄደች። ቅዱስ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው። አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ፍፁም ፈጣን አባት ናቸው ።

=ሰላም የእግዚአብሄር ቤተሰቦች የፃዲቁ አባታችን አቡነ እጨጌ ምስክርነት ለመስጠት ነው አባቴ ያደረጉልኝ ብዙ ብዙ ነው ባለፈው ሳምንታት ጉንፋን በጣም አሞን የኔ ቅዱስ ገብርኤል እመቤቴ ማርያም ማሩንሽአልኩኝ ወዲያው ለውጥ ነበረን አሁን ደሞ እግዚአብሄር ይመስገን በጣም ደህና ነን አባቴ በየ ቀኑ የሚያደርጉልኝ ብዙ ነው የረሳሁት ካለ አባቴ ይቅር ይበሉኝ መጨረሻውን ያሳምርልን በድጋሜ ለመመስከር ያብቃኝ ለኔ በሚረባውም በማይረባው ጠርቻቸው አሳፍረውኝ አያቁም በጣም ይቅር ባይ አባት ናቸው እኔን እንደሰሙኝ እናንተንም ይስሟቹ እሳቸውን አባት አድርጎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሄር ቸሩ መዳኒተአለም ይመስገን እንተንም ወንድሜ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ

=abune echigen lamsgen eji lay ende ekeke ngr wetobegn abaten sel adno ashchi ena thbelachwen kbechi teshlognal amsgnulgn

=ሠላም ጆኒ እንዴት ነህ ምስክርነት ለመስጠት ነበር ትላንት ጀርባዬን ብርድ ነክቶኝ መተንፈስ አቅቶኝ እየወጋኝ ነበር ማታ ላይ ስተኛ አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ዘጠገሮ እባኮትን ማሩኝ ስነሣ ደህና ሆኜ ከተነሣሁ ምስክርነት እሠጣለው ብዬ ነበር ምስጋና ይሁን ለአባቴ ድኛለው እሴተ ማርያም ።

=ወነድማችን እንደምንሠነበትህ ፀጋዉ ይብዛልህ ለእመብርሃን ለቅዱሥ ሚካኤል ለቅዱሥ ገብርኤል ለቅዱሥ ሩፋኤል ለአባታችን ለአቡነ እጨጌ ዮሐንሥ ለመጥምቁ ዮሐንሥ ለቅዱሥ ማርቆሥ ለሠማትዋ ቅዱሥት አርሴማ ለቅዱሥ ዑራኤል ትዳር ሥጡኝ ብየ ነበር ተዋዉቀናል ክብር ይድረሣቸዉ እንደየ ክብራቸዉ አሁንም መጨረሻዉን አሣምረዉ ለትዴር ያብቁን አፀደ ማርያም ነኝ በፀሎት አሥቡኝ

=Ye abune echegen dineq teamir lememesker new.gwadegna yemetenorew USA new ena ye 5 month erguz neberch ena setemeremer ye ayimiro wesnenet (down syndrome) alebet lijesh tebela betam techenka neber. Kezeyam yeabune echege tsebele teteta degami setemeremer negative tebalch.le selete dejachew eskebeqa jonny pls mesekerelegne. Kiber le medehaniyalem enehe dinqe abat leseten. Ellllllleeeeee

=ሰላም ጆኒ ምስክርነት ለመስጠት ነው አብነ እጨጌ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው አባቴን የትዳር አጋር እንዲሰጡኝ ጠይቄአቸው ብዙም ሳይቆይ ሰጡኝ ግን ባለ መመስከሬ በመሀል ግጭት ተፈጥሮ ተለያየን እንደገና አባቴን ይቅርታ ጠይቄ አባቴን ስሞትን ጠርቼ አልፈር ብዬ ተማጽኜ እንዲሁም የጌታዬን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ቅዱስ ሚካኤልን ቅዱስ ገብርኤልን እናቴን ቅድስት አርሴማን ተማጽኜ አሁን እንደገና ታርቀናል መጨረሻውን እንዲያሳምሩልኝ እየተማጸንኩኝ ነው 2,ውጭ ሀገር ያለውን የቤተሰብ ንብረታችንን ተቃጥሎ የነበረውን በኢንሹራንስ አማካኝነት እንደገና በአዲስ መልክ እንዲሰራ አደረጉልን አባቴን የሰጠኝን ልኡል እግዚአብሔርን አመስግኑልኝ

ገዳሙ ጉዞ አዘጋጅቷል
ሰሜንሸዋ መንዝ +++++(መዘዞ)አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ++++ ጉዞ 28\29/1/2015ተዘጋጅቷል።

መነሻ፦መስከረም28
መመለሻ፦መስከረም 29 ተባርከን መመለስ።
ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969

የሄደ ሁሉ በጻድቁ አባታችን መስቀላቸውና መቋሚያቸው ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ!አሜን!!!!

Share በረከት እናግኛ፦ንገሩ አሳውቁ የሰው ልጅ ይዳን Share Share Share!
[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ /መዘዞ ከተማ/ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ 2ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ
እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም ያስኪዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን

++++እመብርሃን ወላዲት አምላክ { ቅድስት ኪዳነ ምህረት } አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ
ይህን የእርስበርስ የወንድማማች ጦርነት ታቁምልን፤ ህዝብሽን የሚጠራሽን የሚወድሽን ከጦርነት ከረሃብ ከቸነፈር ጠብቂልን።

በቃልኪዳንሽ ሀገርሽ ኢትዮጵያን ሰላም ፍቅር አንድነት ስጫት ፤ከጠላቶቿ ጠብቂያት!ህዝቦችሽን አንድ አድርጌ ኢትያጵያን ሰላሟን ፍቅሯን አንድነቷን ስጫት ጠብቂያት፤ በቃሽ በይን።አሜን!!

እረ እንቃ እያለቀ ያለው አንድ እምነት ያለው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞ እና የአብርሃም ልጆች ወንድማማቾች ናቸው እረ እንቃ እመብርሃን በቃህ ትበለን።አሜን!

==== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...
970 views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:09:12 share share share ምስክርነት!
++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን
"አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
=ሠላም ጆኒ!! አባቴ አቡነ እጨጌ እመቤቴ ድንግልን ጠርቼ አፍሬ አላውቅም ሁሌም እመሠክራለው 1. ጓደኛዬ በስራ ቦታ ሰራተኞች ከአለቃ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ እሷ በቦታው ስለነበረች ከሁለቱም ወገን እሷን ምስክር እንድትሆንና አደረጓት መናገር ያለብኝ ትክክለኛውን ያየሁትንና የሰማሁትን ነገር እናገራለሁ ነገር ግን ከሁለቱም ወገን መጣላቴ አይቀርም ብላ በጣም ተጨነቀች ለማስማማት ሞከረች አልተሳካም በጣም ተጨነቀች እኔም ከጭንቀት እንዲያወጧት ይሄ ምስክር የሚለውን ነገር እንዲተዋት ከማንም እንዳትጋጭ ለእናቴ ለድንግል ማርያም አባቴ ለአቡነ እጨጌ ነገርኳቸው ይኸው ሁሉም ነገር ወደሷ ሳይመጣ ምስክርም ሳትሆን ቀርቶ እነሱም በራሳቸው መንገድ ሄደዋል፡፡
2. ጠዋት ወደ ስራ ስገባ አይኔ እየተርገበገበ በጣም አስጨነቀኝ ቆይ ይተወኛል ስል አልተወኝም ስልኬ ላይ ባለው የአቡነ እጨጌ ምስል አይኔን አሻሸሁት ወድያው ተወኝ፡፡
3. የታመመች ዘመዴ ነበረች ስደውል ምግብ አልበላ ብላ በጣም እተዳከመች እንደሆነ ነገሩኝ እግዚአብሄር ሆይ ድረስልን ስለ ቅዱሳኑ ስላ እናትህ ብዬ ስልኬ ላይ ባለ ምስል ሰውነቴን አሻሸሁት ወዲያው ስደውል ምግብም ቀመሰች ደህናም እንደሆነች ነገሩኝ እስከመጨረሻው ምሯት ለመመስከር ያብቃኝ፡፡ እባክህ መስክርልኝ አንተም እግዚአብሄር ይስጥህ።

=ዛሪም መማር መዳበስ የማይሰለቻችው አባቴ ምረውኛል መስክርልኝ ጉኔ ላይ አንድ 5ወር ይሁነዎል ያመኛል እንደ እጢ አብጡ አክንቤት ደጅ አልሄድም እርሱ ማሮኝ ብዬ እምነታችውን እየተቀባው እግዛብሄር ይመስገን ለውጥ አይቻለው ጨርሰው ከላዬ ላይ እንደሚያጠፎልኝ አልጠራጠርም በትንሹም በትልቁም ስጠራችው ይደርሱልኛል እናንተንም ጆን እግዛብሄር አምላክ ጉልበታችውን ይባርክላቹ በፀጋው በጤና ከቤቱ አይለያቹ በሌላ ምስክርነት ተመልሼ እመጣለው ሰላማቹ ይብዛልኝ መስክርልኝ አባቴ

=Beseme Ab Weweld Wemenfes qedus ahadu amlak amen...
MESEKERENET
1.Enate ena wechi yalech ehete tekwarfew neber le abate abune echege negere selam honewal
2.Sewnete eyeqosele eyasakekegn neber...semonun ke addis ababa abune echege betekerstiyan yemeta keba kedus teqebeche dehna hognalew chereso endemimregn amnalew
#Lela letsadequ yenegerkwachew negeroch alu bedegami lememesker yabqagn...AMEN

=በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።ል።ከእህቶቼ ጋር ሆኜ ትራንስፖርት አጥተን ስማቸው ስጠራ ወዲያው አገኘን። ሌላው የባለቤቴ ስልክ ተበላሽቶ ነበር አባታችን እንዲያስተካክሉት በምስላቸው አሻሽቼው ተማጽኛቸው መሥራት ጀመረ። በጠቅላላው አባቴ በጠራኋቸውና ባልጠራኋቸው ጊዜና ሠዓት ከጎኔ ተለይውኝ አያውቁም ብርታትና አቅም እየሆኑኝ ነውና ለጥያቄዬ ፈጣን ምላሻቸው እየሠጡኝ ነውና ምሰጋናና ሠላምታ ይድረሳቸው እልልልል።ጻድቁ አባታችን አቡነ ዮሃንስ ለእኛ የሠጠን የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይገባዋል እንዲሁም ለጻድቁ አባታችን ዮሃንስ ምስጋናክብር ይድረሣቸው ጸሎት ልመናቸው አይለየን አሜን።

=እንዴት አመሽህ ጆኒ እኔ ወለተ ገብርኤል እባላለሁ ለአቡነ እጨጌ ዮሀንስ ምስክርነት ለመስጠት ነው በጠና ታምሜ በለተ ቀናቸው ፀበላቸውን ጠጥቼ ከሞተ ተርፋለሁ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ ክብር ለመድሀኒለም።

=እንዴት አድርክ ወንድሜ ማታ በጣም አመኝ ስውነቴ ብርድ ብርድ ይላኛ በጣም የቀጠቅጠኛ ተጨንቆ የሙሞት መስሉኝ የአባታን የአቡነ እጨጌ ፀበላቸውን ጠጥቼ በገደላቼ ተሻሽቼ እንቅልፍ ወስዶ ጥዋት ስነሳ አደዛ ስያስጨቅነኝ የነበር ተሽሎኛ የአቡነ እጨጌ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን

=Selam Wendme Jonny,
Le Abatachn abune chege mskrnet neberegn, cheguarayen tamme mnm mgb meblat aktogn neber gn le Abatachn Abune Chege mhretun stugn slachew , mhretun setugn ena mskrnet lemestet new .
Egziabher ystlgn wendme .

=selam Jhone endet nk tsadiku abati abune echegi yadregelugm lememsker nw tlat neb yehun mehn ednefgn alkem eshok neky emnetachew teknch be sehle adnochew tedansh bzu almemegnm amlelake abune echegi yohannes le kidist degel mariyam lej kiber msgana ydresew. abati abune echegi kiber msgana ydresachew kidist degel mariyam msgana ydresat
Lilaw le wedmim yeteyeqwachew neger neber astekaklewletal be tnshum betlkum chgri besraim behiwoti hulu eredati nachew esachewn kagegnew dejafachew kergetku jemro bzu neger keyrewlgnal ahunr yaltefeto chgroch albugn tsadiku abatiy abune echgi yhohannes yegeft yetabroa mariyam kidist kerstos samra semahtwa kidist arsima semahtu kidus giorgies abati abune tekle haymanot abui gebremenfes kidus edemifetlgn amlanew msgana kiber ydresachew medaniyalem kerstos msgana ydresew hulu kidusan tsadikan semahtat msgana ydresachew amen

=Jony wondime indet aleh? zarem ye abaten dink sira limesekir new yene fetno derash tilant mata betam techenike akeraye sew lichemir bebetu chenkogn abate talka yigbu biye lemenkuachew sewochu wede lela bota hedu lemignachew minim alatawum amesginilign!

=Ellllll embete dengl maryam bltekenwa lmnayen asakachlgn borsaye west 10birr becha new yenbergn ketwat jemere embeten abaten eylmnku neber behone menged birr endstugn tesfa korche balhubt seat sew meto eka gezagn yelmnuten yemynsa yetykutn yemayresa amlake abune echge yohans zetigero cheru mdhanyalem keber yegbaw abate lene endhi fetnew endedersu lenantem ydrsulachw dengl hoy keljish slamaldshgn amsgnshalew abate kelelugn
558 views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:05:51 ++++እመብርሃን ወላዲት አምላክ { ቅድስት ኪዳነ ምህረት } አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ
ይህን የእርስበርስ የወንድማማች ጦርነት ታቁምልን፤ ህዝብሽን የሚጠራሽን የሚወድሽን ከጦርነት ከረሃብ ከቸነፈር ጠብቂልን።

በቃልኪዳንሽ ሀገርሽ ኢትዮጵያን ሰላም ፍቅር አንድነት ስጫት ፤ከጠላቶቿ ጠብቂያት!ህዝቦችሽን አንድ አድርጌ ኢትያጵያን ሰላሟን ፍቅሯን አንድነቷን ስጫት ጠብቂያት፤ በቃሽ በይን።አሜን!!

እረ እንቃ እያለቀ ያለው አንድ እምነት ያለው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞ እና የአብርሃም ልጆች ወንድማማቾች ናቸው እረ እንቃ እመብርሃን በቃህ ትበለን።አሜን!
498 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:01:04 ††† ጥር 22 ቀን ዓመታዊ ቅዱስ አባ እንጦንስ (የመነኮሳት አባት - የበርሐው ኮከብ /ልደቱና ዕረፍቱ)ነው።
የአባ እንጦንስ ጸሎት
እኔ አመድ ትቢያ ሳለው እንደቅዱስ ከሚቆጥረኝ ህዝብ ጠብቀኝ ይላል
አባ እንጦንስ ይህን ያለበት ውዳሴ ከንቱን ከመሸሽ እና ከመራቅ ነው
እኛ ደግሞ ገና ለጸሎት ስንቆም መወደዱን ሞገሱን ስጠን እንላለን እኛ ይህን የምንለው ከመወደድ ጋር የሚመጣውን ችግር ስለማናውቀው ነው አንዳንዶቻችን መንፈሳዊውም ስጋዊ ዓለም አልገባንም በዓለም እየተገለገሉ ያሉት በጣም ትንሾች ናቸው ሌላው ግን ገና የዓለም አገልጋይ ባሪያ ነው
ዓለምን የሚያውቁትን ትንሾችን ዓለም በጣም ተንከባክባ ትይዛቸዋለች ይህን የምታደርገው ሌላውን እንዳታነሳሳባቸው ነው አገልጋዮቿን ደግሞ ተስፋ እንዳይቆርጡ ብልጭልጭ መስታውት እያሳየች በተስፋ እንደ ሸንኮራ አገዳ ጉልበታቸውን መጥታ ትተፋቸዋለች
አባ እንጦንስ ዓለምን እስከ ክፋቷ ስለሚያውቃት ቅዱስ ብላ እንደትጠራው አይፈልግም ምክንያቱም እናንተ እኮ ቅዱሳን ናችሁ እያለች ያረከሰቻቸው ብዙ ናቸውና እንደ አባ እንጦስ ከዓለም ራሳችንን መጠበቅ የእያንዳንዳችን ሀላፊነት አለብን።
አንድ ወንድም ዓለምን በመናቅ ያለውን ሁሉ ሽጦ ለድሆች ካከፋፈለ በኃላ ለግል ፋጆታው እንድትሆነው ጥቂት ነገርን ያስቀራል። ከዚህ በኃላ አባ እንጦንስን ለማየት ወደ እርሱ ይሄድና ያደረገውን ሁሉ ይነግረዋል።
አባ እንጦንስም <<መነኩሴ ለመሆን ከፈለግህ ወደ መንደር ተመልሰህ ሂድና ሥጋ ከገዛህ በኃላ በዚያ ሥጋ ዕርቃንህን ሸፍነውና ወደዚህ ተመልሰህ ና!>> ይለዋል።
ሰውየውም የነገረውን አድርጎ ወደ አባ እንጦንስ ሲመለስ ውሾችና አሞራዎች ሰውነቱን ይዘነጣጥሉታል፡፡ ወደ ሽማግሌው መነኩሴ ተመልሶ ሲመጣ የታዘዘውን በትክክል መፈፀምና አለመፈጸሙን ይጠይቀዋል፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው የተነካከሰ ገላውን ገልጦ ሲያሳየው አባ እንጦንስ ዓለምን ንቀናል ካሉ በኃላ ለራሳቸው ፍጆታ የሚሆን ነገር የሚያስቀሩ ሰዎችም ልክ እንደዚሁ በእርሱ ላይ ውጊያ በሚከፍቱ ርኩሳን መናፍስት አማካይነት ይዘነጣጠላሉ!>> በማለት አስተምሮታል፡፡
የጻድቁ በረከት ይደርብን የጻድቁን ማስተዋል ይስጠን አሜን!
ቦታው።፦የአባ እንጦንስን ቤተ ክርስቲያናቸው በአዲስአበባ ቦሌ አራብሳ ጨርቆስ አደባባይ ወረድ ብሎ መድሐኒዓለም ቅዱስ ተክለሃይማኖት ዋሻ አካባቢ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቡነ እንጦንስ ዋሻ ።


+++++++ሰሜንሸዋ መንዝ መዘዞ(ጸገሮ) ምዕረፈ ቅዱሳን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ]
+++++ገዳሙ

ጉዞ___ መስከረም28/29ገዳሙ ጉዞ ያዘጋጃል
መነሻ፦መስከረም28
መመለሻ፦ መስከረም29
ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
የሄደ ሁሉ በጻድቁ አባታችን 500 ዓመት በያዙት መስቀላቸውና መቋሚያቸው እንዳበሳለን፤ ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ
ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።ቃልኪዳን፤ጣባቂ ያላት ሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም የማትሆነው ቀድሞ የነበራች ከሁሉም የተለየች ሃገራችንን የቃልኪዳኑዋ አስራት ሃገር እምየ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ከልጇ አስታርቃን እርዱችን ያለውን ርሃብ ታጥፋልን ህዝቦቿን ትጠብቅልን።አሜን!!!

======== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
+++Facebook page
አናዥጋ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ገዳም +Johnny akeme/ዮሐንስ አለመ/
https://www.facebook.com/አናዥጋ-ቅዱስ-እግዚአብሔር-አብ-ገዳም-Johnny-alemeዮሐንስ-አለመ-105994748632235/
+++facebook page
ግፍት ቅድስት ማርያም ገዳም +Johnny aleme/ዮሐንስ አለመ/
https://www.facebook.com/pg/%E1%8C%8D%E1%8D%8D%E1%89%B5-%E1%89%85%E1%8B%B5%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D-%E1%8C%88%E1%8B%B3%E1%88%9D-Johnny-Aleme%E1%8B%AE%E1%88%90%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%98-100618749180538/community/
የሄደ ሁሉ በጻድቁ አባታችን መስቀላቸውና መቋሚያቸው ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ!አሜን!!!!
Share በረከት እናግኛ፦ንገሩ አሳውቁ የሰው ልጅ ይዳን Share Share Share!
[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ /መዘዞ ከተማ/ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ 2ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ
እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም ያስኪዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን!
592 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:00:54 ~~~~SHARE ለመጀመሪያ ግዜ /አዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ጨርቆስ አደባባይ/መድሐኒዓለም ጻድቁ ተክለሐይማኖት ዋሻ ቅርብ ለቅርብ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቡነ እንጦንስ ቤተክርስትያናቸው በዋሻ ነው።
ጸበልም ከሾላ ውስጥ ፈልቆ ምዕመን እየተፈወሱ ነው፤ወራዊ በዓል 22 የመነኮሳት አባት/ አባ እንጦስ ገዳምህን የረገጠ ገድልህን ያነበበ 50ትውልድ እምረዋለሁ።
++++ በመሄድ እንፈወስ እንባረክ።

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
† አባ እንጦንስ †
† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል (የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት)" ተብለውም ይጠራሉ::
ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን (የካቲት 2 የሚከበሩ) ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት (የመነኮሳት አባት): ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት (ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ) ስትል ትጠራቸዋለች::
አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት 1,700 ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው::
ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል::
አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ252 ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው : አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::
በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::
ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው::
አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በሁዋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" (ማር. 10:17) የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማሕበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ::
ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ80 እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው::
በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::
ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በሁዋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ::
በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም:-
1.ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔን ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ::
2.በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ::
3.ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::
እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኩዋ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ372 ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው 120 ደርሶ ነበር::
††† ለአባታችን እንጦንዮስ /እንጦንስ/ እንጦኒ ክብር ይገባል!
819 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:23:06
322 views21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:22:42
324 views21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:21:18 ++++ወሎ {ራማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም}
ይህን የእርስበርስ የወንድማማች ጦርነት ታቁምልን፤ ህዝብሽን የሚጠራሽን የሚወድሽን ከጦርነት ከረሃብ ከቸነፈር ጠብቂልን።
በቃልኪዳንሽ ሀገርሽ ኢትዮጵያን ሰላም ፍቅር አንድነት ስጫት ፤ከጠላቶቿ ጠብቂያት!ህዝቦችሽን አንድ አድርጌ ኢትያጵያን ሰላሟን ፍቅሯን አንድነቷን ስጫት ጠብቂት በቃሽ በይን።አሜን!!

{ራማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም}
ራማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም በሰሜን ወሎ በቆቦ ወረዳ ውሰጥ የምትገኝና በ6ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ እንደተመሰረተች ይነገራል።
ብዙ መነኮሳት እናትና አባቶችም የሚገኙባት ነች፡፡ እንዲሁም የአብነት ተማሪዎች የሚገኙባት ነች።
በረከቷ በያላችሁበት ይደርባችሁ። አሜን!

ይህን የእርስበርስ የወንድማማች ጦርነት ታቁምልን፤ ህዝብሽን የሚጠራሽ የሚወድሽ ከጦርነት ከረሃብ ከቸነፈር ጠብቂልን።
በቃልኪዳንሽ ሀገርሽ ኢትዮጵያን ሰላም ፍቅር አንድነት ስጫት ከጠላቶቿ ፤ጠብቂያት!አሜን አሜን አሜን!!!
ይሁንልን ይደረግልን!አሜን!!

ቦታው+ ራማ ቅድስት ኪዳነምህረት ሰሜን ወሎ ራያ

==== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...
236 views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:20:53 ++++++አቡነ አሮን መንክራዊ ገዳም/ጣራው ክፍት ዝናብ የማያስገባው ገዳማቸው/
ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ የአቡነ አሮን ወላጆች
<አባት ገብረ መስቀል>
<እናትዓመተ ማርያም >የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ናቸው። ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡

አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው <በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል >እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡

በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ››አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡
ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን
አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡


<ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል >ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::
ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኩዋን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል::

በበዓል ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል፡፡

በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ::

በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ:: አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ::

~እረፉታቸው መስከረም 5
~የተወለዱት ነሐሴ 5

ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፣ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው"መዝ•118/119÷129

"ፃዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት
ይወስዳል።" ማቴ 10፥41

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል።" ማቴ 10፥40

" እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።"
ዮሐ 9፥12
"የአለም ብርሃን ናችሁ!"

"ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን "1ቆሮ6፥2

-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-"ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።" 88(89)፥3

" እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም።" ማቴ 10፥40-42

የአቡነ አሮን መንክራዊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣
በጸሎታቸው ይማረን!

ቦታ ~ ጻድቁ በተጋድሎ ወሎ መቄት ውስጥ ከአግሪት 1:40 ሰዓት ርቀት ላይ የሚገኘውን እና ጣራው ክፍት የሆነ ምንም አይነት የዝናብ ጠብታ የማያስገባ ገዳም በመቄት ወረዳ ከወልድያ 150km ርቀት ላይ ከአግሪት ቀበሌ በስተ ሰሜን በኩል ይገኛል።

==== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...
261 views21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:57:43 ==== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...
327 views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ