Get Mystery Box with random crypto!

++++++አቡነ አሮን መንክራዊ ገዳም/ጣራው ክፍት ዝናብ የማያስገባው ገዳማቸው/ ኢትዮዽያዊው ጻድቅ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

++++++አቡነ አሮን መንክራዊ ገዳም/ጣራው ክፍት ዝናብ የማያስገባው ገዳማቸው/
ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ የአቡነ አሮን ወላጆች
<አባት ገብረ መስቀል>
<እናትዓመተ ማርያም >የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ናቸው። ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡

አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው <በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል >እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡

በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ››አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡
ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን
አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡


<ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል >ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::
ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኩዋን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል::

በበዓል ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል፡፡

በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ::

በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ:: አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ::

~እረፉታቸው መስከረም 5
~የተወለዱት ነሐሴ 5

ምስክሮችህ ድንቅ ናቸው፣ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው"መዝ•118/119÷129

"ፃዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት
ይወስዳል።" ማቴ 10፥41

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል።" ማቴ 10፥40

" እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።"
ዮሐ 9፥12
"የአለም ብርሃን ናችሁ!"

"ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን "1ቆሮ6፥2

-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-"ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ።" 88(89)፥3

" እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም።" ማቴ 10፥40-42

የአቡነ አሮን መንክራዊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣
በጸሎታቸው ይማረን!

ቦታ ~ ጻድቁ በተጋድሎ ወሎ መቄት ውስጥ ከአግሪት 1:40 ሰዓት ርቀት ላይ የሚገኘውን እና ጣራው ክፍት የሆነ ምንም አይነት የዝናብ ጠብታ የማያስገባ ገዳም በመቄት ወረዳ ከወልድያ 150km ርቀት ላይ ከአግሪት ቀበሌ በስተ ሰሜን በኩል ይገኛል።

==== አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...