Get Mystery Box with random crypto!

Jan Tech - ጃን ቴክ 📱

የቴሌግራም ቻናል አርማ jantech24 — Jan Tech - ጃን ቴክ 📱 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jantech24 — Jan Tech - ጃን ቴክ 📱
የሰርጥ አድራሻ: @jantech24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.83K
የሰርጥ መግለጫ

🔰Welcome To Jan Tech - ጃን ቴክ TG Channel.🔰
We Sharing All types of information, refer n earning apps/software...if u like to than join our channel
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
© 2023
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💪Powered By @tom_abe

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-08 15:13:35 ህልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ " አይሳካልኝም " የሚል ፍርሃት ።

ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ !

ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና ።

አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው ።

ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ ።

የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው ።

በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቛንቛ አለ " ፍቅር " !

ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ !

አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል ።


@jantech24
163 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 14:56:03 እኚህ 3 ቻናሎች ሁሉንም የ#ኮርስ አይነት አላቸው #ታዋቂ የሆኑ ኮርስ ሰጪ ከሆኑ ዌብሳይቶች ላይ ነው ሚለቀቁት።
በብዚ ሺ
#ዶላር ሚሸጡ ናቸው እነዚህ ላይ በነጻ ያሉት ፡ በሁሉም ዘርፍ ምትፈልጉትን ብቻ ወስዳችሁ መጠቀም ነው።
ይጠቅማቹሃል ብዬ ስላሰብኩ ነው ።
Sport ,acting,storytelling,filmmaking,coding, cooking, .......ሁሉንም

@skillshare_udemy_masterclass
@MasterClass0
@SkillShareClass

@jantech24
136 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 21:24:00 በምን ታድጋለህ ?

አሁን ያለህ ማንነት በዉርስ ያገኘኸው አይደለም ፤ በትምህርት ብቻም የዳበረ አይደለም እንዲህ ሆነህም አልተፈጠርክም ታድያ በምን ገነባኸው ?
በልማድህ!

በየቀኑ በምታደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ራስህን እየገነባኸው ነው አንተን አንተ የሚያረግህ ያለህበትን ቦታ የምትሄድበትን መንገድ የሚወስንልህ ፦

ዛሬ የምትውለው ውሎ እና ማድረግ የለመድካቸው ነገሮች ናቸው ስለዚህ አሁን ወደ ቀንህ ስታመራ ትንሽ ጊዜ ለራስህ ስጥና የምታደርገውን ወስን !

@jantech24
154 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:41:32 " 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " በ14 ሳምንታት ውስጥ 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " ብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአዳዲስ እና ነባር ለሆኑ ደንበኞቹ " ተረክ በጉርሻ " በሚል የሽልማት  መርሐግብር መጀመሩን አስታውቋል። በዚህ መርሐግብር አንድ ሚሊዮን ደንበኞችን ሸልማለው ብሏል።

የሽልማት መርሐግብሩ በየሁለት ሳምንቱ እና በየወሩ የሚካሄድ ሆኖ ከመጋቢት 27 እስከ ሰኔ 27 እንደሚቆይ ተገልጿል።

ሽልማቱ ምንድን ነው ?

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አትዮጵያ 3 መኪኖች ፣ 7 ሞተር ሳይክሎች ፣ 7 ባጃጆች፣ ስማርት ስልኮችና ነጻ የአየር ሰዓት ለሽልማቱ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

- መኪኖቹ በየወሩ ለባለ ዕድለኞች የሚተላለፉ ይሆናል።

- በየሁለት ሳምንቱ አንድ ባጃጅ እና አንድ ሞተር ሳይክል ለዕድለኞች ይደርሳል።

- በየሁለት ሳምንቱ 3 ሳምሰንግ S-21 እንዲሁም 3 ሳምሰንግ ታብ 8 ለባለ ዕድለኞች ይወጣል።

- ሳፋሪኮም በራሱ ብራንድ የሚያስመጣቸው " ቅመም " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማቱ ያዘጋጀ ሲሆን ከቅመም ስልኮች ውስጥ " ቀረፋ " እና " ናና " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማት አቅርቧል። እነዚህም በየሁለት ሳምንቱ ለ100 እድለኞች በሽልማትነት ይቀርባሉ፤

- በየቀኑ የ50 ብር፤ የ100 ብር፤ የ200 ብር የአየር ሰዓት ሽልማቶችም ተዘጋጅተዋል።

የዕጣው ዕድለኛ ለመሆን ምን ማድረግ ይጠበቃል ?

- በዕጣው ተሳታፊ ለመሆን ለአዲስ ደንበኞች ሲም ካርድ ገዝተው በ24 ሰዓት ውስጥ ካርድ የሚሞሉ ከሆነ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይችላሉ።

- የሳፋሪኮምን የ10 ብር አየር ሰዓት መሙላት አንድ የእጣ ቁጥር እንዲደርሶ ያስችላል። ይህም ደንበኞች በሚገዙት የአየር ሰዓት መጠን የዕጣ ቁጥሮቹ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

- የድምጽ፣ የአጭር መልዕክት፣ የዳታ፣ የሁሉም ኔትወርክ ወይንም የኮምቦ ጥቅሎችን መግዛት፤ በ1ዐ ብር ጥቅል አንድ ኮድ፤ በ20 ብር ሁለት ጥቅል ሁለት ኮድ ማገኘት ይቻላል ተብሏል። የአየር ሰዓት በስጦታ መልክ መላክም የዕጣ ቁጥር ያሰጣል።

በተጨማሪም ደንበኞች WhatsApp ላይ ብቻ የሚገለገሉበት የኢንተርኔት ጥቅል እያቀረበ መሆኑን የገለጸው ሳፋሪኮም የ 1GB ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞቹ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣው ዕጣ በብሔራዊ ሎተሪ አማካኝነት የሚወጣ ሲሆን አሸናፊዎች እድለኛ መሆናቸውን በ 0700 700 700 ተደውሎ የሚገለፅላቸው ይሆናል ተብሏል።

ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር ከ2.8 ሚሊዮን መሻገሩን አስታውቋል።

ምንጭ
@tikvahethiopia

@jantech24
136 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:40:14 የስልጥኛ ቋንቋን በቀላል መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ መዝገበ ቃላት ተመርቋል።

መተግበሪያውን በስልክ አፕልኬሽን እና በኢንተርኔት በድረ ገጽ መጠቀም የሚቻል መሆኑ ተገልጿል።

መተግበሪያው ስልጥኛን በስልጥኛ፣ ስልጥኛን በአማርኛ፣ ስልጥኛን በእንግሊዝኛ እና ስልጥኛን በስልጥኛ የሚተረጉም መዝገብ ቃላት ይዟል።

የመተግበሪያው ዝግጅት 3 ዓመታትን የወሰደ ሲሆን በስልጤ ልማት ማህበር የገንዘብ ድጋፍ መሠራቱ ተመላክቷል።

መዝገበ ቃላቱ የስለጥኛ ቋንቋን ተደራሽነት ለማስፋት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው መተግበሪያውን ያበለጸጉት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተናግረዋል።

መዝገበ ቃላቱን ለማግኘት ➧
www.sld.org.et

ምንጭ፦ ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን


ሌሎችንም ወደቻናላችን ይጋብዙ JOIN

@jantech24
104 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:41:40
"አውሮፕላኖች አየር ላይ እንዴት ሊንሳፈፉ ቻሉ?"
"How do airplanes float in the air?‌‌" በቅርብ ቀን ከበቂ ማብራሪያ ጋር....Coming soon!! #share ይደረግ!!
ሳይንስኛ

@jantech24
135 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:33:15 ዲፕ ፌክ (#deep_fake) እና ሊፕ ሲንክ (#lip_synch) ምንድን ናቸው?

አሁን አሁን እጅግ በረቀቀ መልኩ የሚሠሩ የምስል፣ የቪድዮ እና የድምፅ ቅንብሮች መታየት እየጀመሩ ነው። አንዳንዶቹ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (#AI) ጭምር በመታገዝ የሚሠሩ ሲሆን እውነት ይሁኑ ሐሰት መሆናቸውን ለመለየት አዳጋቾች ናቸው።

ፊት መቀያየር (face swap)፣ ፊት ቆርጦ ቀጥል (#re-face) እና ምስሎችን ማናገር (#talking faces) የተወሰኑት የዲፕ ፌክ አይነቶች ሲሆኑ የአይነታቸው ስፋት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፣ ይህም ከሶፍትዌሮች መዘመን እና ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መዘመን ጋር እንደሚገናኝ የዘርፉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።

ይህ ምስልን እና ድምፅን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት በማቀናበር የሚሠራ ቴክኖሎጂ ያልተባለን እንደተባለ፣ ያልተደረገን እንደተደረገ አርጎ ለማቅረብ ያስችላል።

ይህ ማለት የመሪዎችን፣ የሚድያ ሰዎችን፣ የታዋቂ ግለሰቦችን ወዘተ ምስል በመውሰድ እና የድምዕ ቅጣዮችን (#sound bites) በሊፕ ሲንክ በመጨመር ለማቀናበር ያስችላል። ሊፈጥር የሚችለውን ችግር ማሰብ ቀላል ነው፣ ለምሳሌ የሀገሪቱ መሪ መግለጫ ሳይሰጡ ነገር ግን እንደሰጡ ተደርጎ ለመለየት በሚያስቸግር የምስል እና ድምፅ ቅንብር ሊቀርብ ይችላል።

በተለይ አሁን ላይ #Generative Adversarial Networks (#GANs) የተባለውን እና ሁለት የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ስልተ-ቀመሮችን (#algorithms) በአንድ ላይ በማጣመር የሚሠራውን የቅንብር ሥራ ከእውነተኛው ለመለየት ለዘርፉ ባለሙያዎች ጭምር እጅግ ፈታኝ ሆኗል።

ይህን ችግር በመረዳት የቻይና እና የአሜሪካ መንግስታት ዲፕ ፌክን እንደ ትልቅ የስጋት ምንጭ በደህንነት ፕሮግራሞቻቸው ላይ ቀርፀው አስቀምጠዋል። በተለይ #ቻይና በጃንዋሪ 2019 ዲፕ ፌክን ሰርቶ ማሰራጨትን በግልፅ ከልክላለች።

አሁን ላይ #ዲፕ ፌክ በራችን ላይ ነው፣ ግን አሁንም ቀላል የፎቶ ቅንብሮችን የሚለየው እና በመተግበርያዎች አማካኝነት የሚያጣራው ሰው በጣም ጥቂቱ ነው። #ፌስቡክ ላይ የተፃፈ እና #ዩትዩብ ላይ የተወራ ሁሉ እውነት የሚመስለውን ማንቃት የሚገባቸው ሚድያዎች በዚህ ዙርያ ሲሠሩ አይታይም፣ እንደውም ራሳቸው ሐሰተኛ ምስሎችን እና መረጃዎችን አንዳንዴ እያጋሩ እንደሆነ እናያለን።

በዚህ ዙርያ ለመስራት የሚሞክሩት የመረጃ አጣሪ ተቋማት እና ግለሰቦች ደግሞ በመረጃ እጦት፣ ባልተገባ ፍረጃ እና ውንጀላ፣ በድጋፍ ማጣት እንዲሁም በእውቀት ማነስ ሲቸገሩ ይታያል።

ይህን ችግር በተወሰነ መልኩ ለመከላከል መፍትሄው መረጃዎች ሲሰራጩ ከትክክለኛ አካል የወጡ እንደሆነ ማረጋገጥ ዋነኛው ነው። ለዚህ ደግሞ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆችን፣ ድረ-ገፆችን እና የመልቲሚድያ ቻናሎችን አውቆ መከተል አስፈላጊ ነው።

Via ሳይንስኛ

@jantech24
120 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 19:29:29
ቴሌቪዥን ላይ #ጥቁር_ጥላ ለምን ይፈጠራል?

LCD ቴሌቪዥኖች በተለያየ ምክንያት ጥቁር ጥላ/dark shadow ሊፈጥሩ ይችላሉ። ከነዚህም ምክንያቶች መካከል ስክሪን ውስጥ የሚገቡ ቆሻሻዎች፣ ከላይ ስክሪኑ ሲቆሽሽ፣ የሞቱ ፒክስሎች (dead pixels) አሊያም የማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች (stuck pixels) የተወሰኑት ናቸው። ከነዚህ መካከል የቀደሙት ሁለቱን በቀላሉ መፍታት ሲቻል በሞቱ እና በማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች አማካኝነት የሚፈጠሩ ጥቁር ጥላዎችን ማጥፋት ግን ቀላል የሚባል አይደለም።

ምክንያቶቹ ምንድናቸው?

የማይንቀሳቀሱ እና የሞቱ ፒክስሎች በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከነዚህም መካከል
“burn in” አንዱ ነው። ይህም ቴሌቪዥኖች ላይ የማይንቀሳቀሱ ምስሎች ለረዥም ሰዓት ሲቆዩ የሚፈጠር ነው። የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (still image) ቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለረዥም ጊዜ በሚቆዩ ጊዜ የቴሌቪዥኑ ስክሪን የምስሎቹን ቀለም የመያዝ እና የማስቀረት እድል ይኖረዋል። ይህም በረዥም ጊዜ የቴሌቪዥናችን ስክሪን ጥቁር ጥላ(black shadow) እና ጥቁር ነጥብ(black spot) እንዲያመጣ ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ ቴሌቪዥናችንን ማንም በማይጠቀምበት ጊዜ መዝጋት ይመከራል።

በተጨማሪም የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (ለምሳሌ ያቆመነው ቪዲዮ) ከግማሽ ሰዓት በላይ ቴሌቪዥኖች ስክሪን ላይ መቆየት የለበትም።

                  
#Share
Via
Ethio tech

@jantech24
107 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 19:21:00 የቦት ጥቆማ

ይህ ቦት የፈለጋችሁትን ሙዚቃ ስሙን ብቻ ስፋቹ በመላክ ያመጣላቹሀል

@Allmusic_abdhkr_bot
94 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 19:18:22
#China vs #America

የቲክቶክ እናት ኩባንያ ባይትዳንስ በአሜሪካ ኢንስታግራምን የሚፎካከር “ሌመን 8” የተሰኘ መተግበሪያውን ይፋ አድርጓል

አሜሪካ በቻይና የቴክኖሎጂ ወረራ እየተፈጸመባት መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች፤ ይህንኑ "ወረራ" ይቀለብሳሉ ያለቻቸውን እርምጃዎችንም ስትወስድ ቆይታለች።

በቲክቶክ የተጀመረው “ወረራ” አሁን ደግሞ ወደ “ሎሚ አቢዮት” ተሸጋግሯል እያለች ነው።

የሜታ ንብረት የሆነውና ጎግል ፕሌይ ላይ ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ያወረዱት ኢንስታግራም፥ በ”ሌመን 8” ከባድ ፉክክር ገጥሞት ከገበያ ይወጣል ወይ የሚለውን ጊዜ የሚፈታው ቢሆንም የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ግን ትልቅ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡት ነው።

የቻይናው ባይትዳንስ አዲሱን መተግበሪያውን ለሚያስተዋውቁ በርካታ ተከታይ ላላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሜዎችም ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ መሆኑን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል።

በአሜሪካ ከ150 ሚሊየን በላይ የቲክቶክ ተጠቃሚ ያለው ባይትዳንስ፥ አዲሱ የፎቶግራፍ እና አጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ መተግበሪያው ከኢንስታግራም ጋር በብዙ መልኩ እንደሚመሳሰል ተገልጿል።

እንደ ቲክቶክም “Follow” እና “For You” የሚሉ አማራጮችና እንደየፍላጎታችን የመዝናኛ፣ ፋሽን፣ ዜና፣ ስፖርት የመሳሰሉ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን ለማቅረብ አስቀድሞ ያስመርጠናል።

ከጉዞ እና ከውበት ጋር የተያያዙ ምክሮችን የሚሰጡ ባለሙያዎችም በ“ሌመን 8” የራሳቸው ገጽ ይኖራቸዋል ተብሏል።

Via ሳይንስኛ

@jantech24
119 viewsτємєѕgєи αϐєϐє τοм, edited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ