Get Mystery Box with random crypto!

' 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ ' - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ' በ14 ሳምንታት | Jan Tech - ጃን ቴክ 📱

" 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " በ14 ሳምንታት ውስጥ 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " ብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአዳዲስ እና ነባር ለሆኑ ደንበኞቹ " ተረክ በጉርሻ " በሚል የሽልማት  መርሐግብር መጀመሩን አስታውቋል። በዚህ መርሐግብር አንድ ሚሊዮን ደንበኞችን ሸልማለው ብሏል።

የሽልማት መርሐግብሩ በየሁለት ሳምንቱ እና በየወሩ የሚካሄድ ሆኖ ከመጋቢት 27 እስከ ሰኔ 27 እንደሚቆይ ተገልጿል።

ሽልማቱ ምንድን ነው ?

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አትዮጵያ 3 መኪኖች ፣ 7 ሞተር ሳይክሎች ፣ 7 ባጃጆች፣ ስማርት ስልኮችና ነጻ የአየር ሰዓት ለሽልማቱ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

- መኪኖቹ በየወሩ ለባለ ዕድለኞች የሚተላለፉ ይሆናል።

- በየሁለት ሳምንቱ አንድ ባጃጅ እና አንድ ሞተር ሳይክል ለዕድለኞች ይደርሳል።

- በየሁለት ሳምንቱ 3 ሳምሰንግ S-21 እንዲሁም 3 ሳምሰንግ ታብ 8 ለባለ ዕድለኞች ይወጣል።

- ሳፋሪኮም በራሱ ብራንድ የሚያስመጣቸው " ቅመም " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማቱ ያዘጋጀ ሲሆን ከቅመም ስልኮች ውስጥ " ቀረፋ " እና " ናና " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማት አቅርቧል። እነዚህም በየሁለት ሳምንቱ ለ100 እድለኞች በሽልማትነት ይቀርባሉ፤

- በየቀኑ የ50 ብር፤ የ100 ብር፤ የ200 ብር የአየር ሰዓት ሽልማቶችም ተዘጋጅተዋል።

የዕጣው ዕድለኛ ለመሆን ምን ማድረግ ይጠበቃል ?

- በዕጣው ተሳታፊ ለመሆን ለአዲስ ደንበኞች ሲም ካርድ ገዝተው በ24 ሰዓት ውስጥ ካርድ የሚሞሉ ከሆነ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይችላሉ።

- የሳፋሪኮምን የ10 ብር አየር ሰዓት መሙላት አንድ የእጣ ቁጥር እንዲደርሶ ያስችላል። ይህም ደንበኞች በሚገዙት የአየር ሰዓት መጠን የዕጣ ቁጥሮቹ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

- የድምጽ፣ የአጭር መልዕክት፣ የዳታ፣ የሁሉም ኔትወርክ ወይንም የኮምቦ ጥቅሎችን መግዛት፤ በ1ዐ ብር ጥቅል አንድ ኮድ፤ በ20 ብር ሁለት ጥቅል ሁለት ኮድ ማገኘት ይቻላል ተብሏል። የአየር ሰዓት በስጦታ መልክ መላክም የዕጣ ቁጥር ያሰጣል።

በተጨማሪም ደንበኞች WhatsApp ላይ ብቻ የሚገለገሉበት የኢንተርኔት ጥቅል እያቀረበ መሆኑን የገለጸው ሳፋሪኮም የ 1GB ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞቹ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣው ዕጣ በብሔራዊ ሎተሪ አማካኝነት የሚወጣ ሲሆን አሸናፊዎች እድለኛ መሆናቸውን በ 0700 700 700 ተደውሎ የሚገለፅላቸው ይሆናል ተብሏል።

ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር ከ2.8 ሚሊዮን መሻገሩን አስታውቋል።

ምንጭ
@tikvahethiopia

@jantech24